ሰውየው በጭጋጋማዋ ደሴት ክፍል -1

 

መጀመሪያ ቀን ያየሁትና አንድ የስራ ባልደረባቸን ያስተዋወቀን የሠራተኞች ካፌቴሪያ እራት እየበሉ ነበር፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት ግን የቡና ሰዓት ላይና በኮሪደሮች ላይ ስንተላለፍ ሰላምታ እንለዋወጣለን፡፡

 

ከሰዓት ጋር ይችኩላል፡፡ በቻለው እያንዳንዷን ደቂቃ በሚፈልገው ሁኔታ ቢያጠፋት ደስታው ወሰን የሚኖረው አይመስልም፡፡ ጣደፍጣደፍ ይላል አካሄድ ልክ ለፍልሚ እንደተዘጋጁ ቴክሳሶች እጅን ዘርጋ አድርጎ ሚሚኑን በሚጠበቅበት ሁኔታ ነው፡፡

 

መካከለኛ ቁመት፣ ጽዱ፣ አጫሽና ቃሚ፡፡ ወደ እርዳይታ በመጣበት ሰሞን መብራት ስላልነበረ ምሳ ለላጤዎች አውቶበስ ይመደብና አሳሳ ወይንም ዶዶላ ይወጣል፡፡ ከነኝህ ቀናት በአንዱ ነበር ከቢሮ ወደ ምሳ ለመሄድ በአጋጣሚ የተገኝነው ቀኑ ነፋስ የበዛበት ስለነበር ንፈሱን ለመካላከል ጃኬቱን እየቆለፈ ምን አይነት ተአበኛ አገር ነው፡፡ ሰው ተአበኛ፣ አገሩ ተአበኛ ግንባሩን ቋጠር አድርጎ መልክት አደረግኝ፡፡ አገላለፁ በሳቅ የሚንከተክት ስለ ነበር ሳቄን እንደምን ተቆጣጥሬ አገሩ ደግሞ ምን አጠፋ?  አልኩት፡፡ ጨዋታ ለመፍጠር ያህል፡፡

 

መብራት የለም ምሳ የለም፡፡ ስለዚህ ከተማ ውጡና ብ የባላል፡፡ ከተማ ምሳችንን በልተን ስንመለስ ልክ እዚህ ስንደርስ የቦላ ነው ምግብ ተፈጭቶ አልቀይርበናል፡፡ ይሄ ተአብ አይደለም? አለና መልክ ሳይጠብ ምን አንተ እሱን ትላለህ፡፡ ለበዓል ቤሰብ ጋር ሄሄ ስለሀገሩ ሲጠይቁኝ በአይኖፕላን ሄዳቸሁ አዛብታርፉ ከኢትዮጵያ የወጣችሁ ይመልላችኋል፡፡ በመኪና ከሄዳችሁ ግን ያው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሆነ ታውቁታላችሁ፡፡ ብያችዋለሁ፡፡ አሁን ይህን የመሰለ ህንፃ፣ እኚህን የመሰሎ የመኖሪያ ቤቶች ከከተማ ርቀው መሠረት ይገባቸዋል? ከዚህ በላይ ተበከ ምን ይኖራል? በማለት እጁን አወናጨፈ፡፡

 

አገላለፁ እየገረመኝ ርዕስም ለመቀየር ስለፈለግሁ ቤተሰብ ደህና ነው? በዓልስ እንዴት አለፈ? ብዬ ጠየቅሁት ሁሉም ደህና ናቸው፡፡ የሄድኩት እኮ ልጆቼ አራቱም ሌሊት በህልሜ ልክ እርዳታ ማስተባበሪ ቢሮ ያለሁ ይመስል ተሰልፈው በተራ በተራ እየመጡ ሲያስቸግሩኝ ጊዜ ነው፡፡ እሱን ጋር ስደርስ ደግሞ ገና አንዳዬኝ ሊሰሙኝ እየተወረወሩ ሲመጡ እኔ ለራሴ መንገድ ላይ ጫት እየቃምኩ ስነበር አቤት ስደርስ ምርቃና ላይ ነኝ፡፡ እንግዳ በግ ሆኜ ቁጭ፡፡ በኋላ ባለቤቴ ምርቃናው ልጆችህን በአግባቡ ሰላም እንዳትላቸው አደረግህ በማለት በጆረዬ ሹ ስትለኝ ነው አንድ በአንድ እየጠራሁ ሞቅ ያለ የናፍቆት ሰላምታ የሠጠኋቸው፡፡ ሲል እኔ ያለማቋረጥ የእጁን መወናጨፍና የፊቱን አገላለፅ ከንግግሩ ጋር እያስተዋልኩ እንከተከታለሁ፡፡

 

እነድደነገረኝ ከሆነ ቤተሰቡ ጋር በሳምንት ሁለት ቀን ነው፡፡ የሚቅመው እርዳይታ ከመጣ ለትምህርት ጽሑፎች ዝግጅትና ለማንበብ በሳምንት ሶስት አራት ቀን መቃሙና መምሯል፡፡ ከቀልድ ለዛው ጋር የሰው መውደድም ተጨምሮ ቤት በማንኛውም ሰዓት እሱ ያለበት አካባቢ የተለያዩ ሰዎች በዛብለው ይታያሉ፡፡ በእረፍት ጊዜ ደግሞ ዛሬ እኛ ጋር ዋል፡፡ የሚለው ጋባዥም ወይ ጉድ የሚያሰኝ ነው፡፡ እንደኔ ዓይነት ሙጅሪም እንኳን ተጠይቆ ሊጋበዝ ለምኖም የሚችል አይመስለኝመና ነው ጉድ ያሰኘኝ፡፡

 

አብዱቄ ሙሉ ስሙ አብዱር ቃድር ዑመር ሲሆን በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች አብዱቄ ስላሉት ብቻ ዋናው ስሙ እየተረሳ መጥቷል የግቢያችንን ጫት ነጋዴዎች በመጣበት ሳምንት ሽርክ አድርጓቸዋል፡፡ ዋናው ነጋዴ ፈጣኑ ነው አብዱቄ እንዳጫወተኝ ም እየበላ ስለፈጣኑ ይንጉደዳል አብዱቄ ቀና በስኪልለት፡፡ ቀና ብ አይቶት የአውራ ጣቱን ምልክት ካሳየው እንደ ራሺያ ሮኬት እየተምዘገዘጋ ሄዶ ጫቱን ያመጣታል፡፡ ያኔ በቃ ተዝናንቶ አቤት ይጠብቃል፡፡

 

አንዳንድ ቀን አለ ጫት ከግቢ በሚጠፋበት ጊዜ አልፎ አልፎ ብቅ የሚሉ ነጋዴዎች እንሰሉ አባባል እናቴ ትሙት ያለዛሬ ጫት ሽጬ አላውቅም፡፡ እያሉ በውድ ዋጋ የሚሸጡ አንድ ቃሚ ከተማ ይዞ መጥቶ ካልገላገለው በስተቀር በነዚህ ከርፋፎች መነጃስ ላይ ቀርለት ነው፡፡

 

ፈጣኑን ነጋዴ ታዲያ ይወድዋል፡፡ አኗኗሩ፣ አነጋገሩ ህይወቱ ራሱ ይመሰጠዋል፡፡ አንድ ቀን ብቻ ከጓደኞቼ ፈጣኑ ሁልጊዜ ካርታ እንደሚለ ሲሰማ በሽቋል፡፡ ምንድን ነው የምትሉኝ አንድ ቀን እንኳን ተሳስቶ አይበላም ሁሌም ትበሉታላችሁ? ብሎ ለማረጋገጥ ይጠይቃቸዋል የፈጣኑን ጓደኞች፡፡ ሁል ጊዜ እንደተበለ ነው፡፡ ብለው ሲመልሱለት ቆዩ ቆዩ ካርታውን እየገለበጣችሁ ነው እንዴ የምትሰጡት? በማለት በአጠገባቸው የነበሩትን ሰዎ ሁሉ አስቋቸዋል፡፡

 

ያንንም ከሰማ በኋላ ፈጣኑን ነጋዴ ይወደዋል፡፡ እንዲውም ያዝንለታል፡፡ የከሰዓት በኋላ ክፍል ካለው ደግሞ ምሳውን እንደበላ ትንሽ ጫት ከፍጥነት ጋር ፈጣኑ ያመጣለትና ያችን ቃም ቃም አድርጉ ሊያስቀምር ይግባል፡፡ አቤት ተማሪዎች እንዴት ይሆን የሚናፍቁት? አለኝ፡፡ በጭንቅላቴ አዎንታዬን መለስኩለት፡፡ ወዲያውኑ ጨዋታውን በመቀጠል መጀመሪም ልሳችሁ ባርኩት፡፡ ከዛ ጥንቃቄ ሳይጓዳል ትላቸዋለህ፡፡ ንግግሬ ደረቅ ሣይንስ ከሆነ ምኑን ተማሩት፡፡ ትኩረት ሰጥተው ያዳምጡኛል፡፡ አቦ እኛ ሀገር ለማስተማር ዘዴው አመቺ ሁኔታ አልተፈጠረለትም እንጂ እኮ የማስተማር ዘዴ ኮርስ የሚሰጡት ሰዎችን ብታያቸው ቴያትር የሚሠሩ ነው የሚመስሉት፡፡ ትንሽ አስብ አርጎ ቀጠል

 

ለምሳሌ፡- በብርድ ወቅት ልታስተምር ስተገባ አንተ በቴሸርት /በስስ ሸሚሚ/ ከሆነኩ ተማሪዎችህ የምታስተምረውን የሚያዳምጡህ ይመስልሃል? በፍፁም ይሄ አስተማሪ አብድ ሳይን አይቀርም ብለው ነው የሚያስቡት፡፡ አሸእያስተማረክ ሳለ ፀጉርህን እየጠቀለልክ ከሆነስ? የተበደረውን ዕዳ እያሰላሰለ ነው አይሎም ብሎ ትገምታለህ? ብቻ ጥሩ አቀራረብ ያስፈልግሃል፡፡ እና ትምህርቱን የወደዱት ይመስለኛል፡፡ እሽ ሻዬ ስለቀዘቀዘ ብታስሞቅልን ይመችሃል? ብ ሳላስበው አስፈገገኝ፡፡

 

አብዱቄን ባስብኩት ቁጥር ይገርመኛል፡፡ ስለሰዎ የጠለያየ ባህርይና የሙያ ፍቅር ለማሰላሰልም እገፋፋለሁ፡፡ ስለሌጦ በማንኛውም አጋጣሚ አውርቶ አይጠግብም፡፡ ከመጽሐፍት ቅዱሳን ዋቢ ይጠቅሳል፡፡ ከታሪክና ባህልም ጋር ይተነትነዋል፡፡ በዘመኑ የሥልጣኔ ዕድገት የተደረሰበትን ደረጃ ይዘረዝረዋል፡፡ ስለሌጦ ከሱ ገለፃ ለ15 ደቂቃ ያህል ያዳመጣ የሳምንት ሴሜናር ከተካፈለ እኩል ዕውቀት ይገበያል ብል ማጋነን አይሆንም እስቲ አንድ ገጠመኝ ላስነብባችሁ፡፡

የፋሲካን በዓል አብድቄና ሌሎች መምህራን አንድ ቤት ምሳ ተጋብዘዋል፡፡ አብዱቄ የተጋበዘበት ቤት ሊገባ ሲል ቦሩ አካባቢ አንድ ነገር መሬት ላይ ዓይኑን ይስበዋል፡፡ አልገባም በማለት ወደ ኋላ ስመለስ የቤቱ ባለቤት ካጠፋሁ እክሳለሁ፡፡ ምንድን ነው ቅር ያለህ ወዳጄ? በማለት ጥያቄውን ያቀርብለታል፡፡ እኔ ክፍል ውስጥ ለሥልጣኞች ሊጦ መሬት ላይ እንዳይወጠር አያስተማርኩ እንተ ምን እያደረጋችሁ ነው? ኮስተር ብሎ አፈጠጠው አብዱቄ የቤቱን ባለቤት፡፡ እባክን ይቅርታ ባለማወቃችን ነው፡፡ በማለት ሌጦውን ወደ ጓሮ ዞር እንዲል ለቤቱልች ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ አብዱቄ ገብቶ መጋበዙን አድምጫለሁ፡፡

 

ከሁሉም ቦታ በቁም ነገር ከተነሳ ለሙያው ሽንጡንገትሮ ይሟገታል፡፡ ይን የሙያ ፍቅር እሱ መለከፍ ይለዋል፡፡ የሙያ ፍቅሩ ታዲያ በሠልጣኞችም እንዲሰርፅ የማይፈጥረው ዓይነት ዘዴ የለም፡፡

 

ቅዳሜ ቀን ከምሳ በኋላ ቡና አዘን እየጠጣን ሳለ አንዱን አንስተን ሳንጨርስ ሌላ እያልን ስለሌላ ዓም ሰዎች ተነሳና ሁሉም የመስለውን ሲናገር አብዱቄ የዓለማችን የጠፈር ተመራማሪዎ እኛ ገበሬ በከተማ እንደምንለው አነሱም ሌላ ፕላኔት ላይ ቢወጡ ልክ ከተማ እንደ ገባው ገበሬ ይደናገራችዋል፡፡ እነሱስ እሺ ከአፍሪካ ሻል ብለዋል፡፡ አላህ አፍርካን ሲሰራት ድርና መጓን አራርቆ ነው፡፡ ልክ እንዳረጀ ልብስ የምትበጣጠቅ ዓይነት አድርጎ፡፡ ይኽን እንዳለ አንድ ጓደኞን አፍሪካንስ እንደሱ ሰራት እኛንስ? ብሎ ብዙም ሣይቆይ አፍርካንስ እንደሱ ሰራት እኛንስ? ብሎ ብዙም ሣይቆይ አብዱቄ ከአፉ ተቀብሎ እኛን እንግዲህ ልብሱ ሲያልቅ ታውቅ የለ? ልክ እንደዛ በትናንሽ ጨርቆች የገጣጠመን ነው የሚመስለኝ፡፡ እያለ ብድግ በማለት በእጁ መሄዴ ነው ብሎ ዓይነት በስንብት መልክ አወናጭፎ መንገድ ሲጀምር ሁሉም ተነስቶ በየፊናው ነጎደ ወይ አብዱቄ ሰው እሱን ሲል ብቻ ይሀን የምሳ እረፍት ላይ ቡና ሊጠጣ የሚቀመጠው? አጃኢብ፡፡

 

 

ይቀጥላል

 

አብዱቄ ብዙ አጋጣሚ ላይ ሰው አልኮል ሲጠጣ እሱ ለስላሳ ይመርጣል አለያም አምቦ ውሃ ሲጫወት ግን በመጠጥ ሰውነቱን ካፍታታው ይልቅ እሱ ያምርበታል እንዲጠጣ የሚያግደረድር ከገጠመው የሚበቃውን ያህል ጠጥቶ እንዳቆመ ይነግረዋል፡፡ እኔ በምጠጣበትም ጊዜ ከጠርሙስ ወደ በርሜል የመጨመር ያህል ነበር፡፡ ይላል፡፡

 

አንድ ጊዜ ከሥር ባልደረቦቹ ጋር በዕረፍት ጊዜያቸው እንጀራውን በጂን እያጠቀሱ እንደበሉ አጫውቶኛል፡፡ ሲያስበው ሁሉ የሚገርም ገጠመኙ ደግሞ ሌላውን ሰው ምን ያህል ሊደንቀው እንደሚችል ይህን ወግ የሚነብ አንባቢ ስሜቱን ልብ ይበልልኝ፡፡

 

የጓደኛውን እናት አምቦ ኪዳነ ምህረት ለማድረስ ከጓደኛው ጋር በአዲሷሞዴል ዳትስን አምቦ ይዱና የጓደኛው እናት ቤክርስቲያን ሲሄዱ እነሱ ወደ መጠጣቸው ጎራ ይላሉሉ፡ የቅዳሴ ሰዓት እንዳለቀም የጓደኛውን እናት ይዘው ወደ አዲስ አበባ ይመለሱና እቤት ካስገቧቸው በኋላ ከቦታ ቦታ እየዞሩ መጠጣቱን ይቀጥላሉ ሞቅ እያላቸው ወጥቶ ቦተ ሲቀይሩ መኪናዋን መጠጥ ቤቱ አጥር ገቢ አቁመው ወደ ቡና ቤቱ ይገባሉ፡፡ እነሱ የሚጠጡት ቀርቦላቸው አስተናጋጇ ውጪ ለቆመችው አዲስ ዳትስን መኪና 4 ቢራ እንድትወስድ ይነግሯታል፡፡ የታዘዘችው ልጅት 4ቱን ቢራ ወደ መኪናዋ ወሰዳ መልሳ ይዛ ትመጣና መኪናዋ ውስ ማንም ሰው የለም እኮ ብላ ስትጠይቅ እነ አብዱቄ የምን ሰው ነው የምትፈልጊው ቢራውን ኣቱ ጎማ ላይአርከፍ ክፊበት የተጓዘቸው መንገድ ቀላል አይደለም ብለዋት ልጅቷም በተነገራት መሠረት 4ቱን ቢራ ለአራቱ ጎማ አጠጥታለች፡፡

 

አልፎ አልፎ ይህን ጉዳይ ሳነሳበት ታዲያ ቢራ ለምን የጠሰራ መስሎሃል አቧራ መጥረጊያ ነው ካርቦራቶር ማጠቢ ካልሆነ ምን ሊፈይድ? በማለት መልሶልኛል፡፡ እሱ ያመሸ የነበረው ኮኛክና ጂን በመሻሸሎ የአልል መጠጦች ነበር፡፡ ትዳር ሊይዝ ሲል ግን አንድ ትልቅ ውሳኔ አሳለፈ መጠጥ ለማቆም፡፡

 

በአቋሙ ፀንቶ ከሠርጉ ቀን ጀምሮ መጠጥን እርም ብሎ ትቶታል፡፡ ማምሸቱን ገን ለ6 ወራት ያህል ከሠርጉ በኋላ ለስላሳ መጠጥ እየያዘ ቀጥሏል፡፡ ከዚያ ወዲህ ነው እንግዲ መጠጥ መጠጣትም ሆነ መጠጥ ቤት ማምሸት ያቆመው፡፡ መጠጥ አይገባም፡፡ በደንብ ሰክሮ ነው ቤቱ የሚመለሰው፡፡ ብዙ ጊዜ ወደ ቤት ሰክሮ ሲመለስ የሚሸጥው ውሻ አለ፡፡ አቤቱ እንደደራሱ ታዲያ የሰካራሙ እናት ውሻውን ይከፍሎታል ወሮታውን ምግብ በመስጠት፡፡ ከነዚህ ጊዜያቶች በአንደኛው ቀን ታዲ ሰካራሙ በታለመደው አካሄዱና የብቻጨዋታ መምጣቱን ሲያበሰር እናትየው ለሚከተለው ውሻ ምግብ ይዞው ወጥተው ያስቀምጣሉ፡፡ ወዲው ከየት መጣ ሳይባል አጥር ሽልኩ የገባ ውሻ ምግቡን ይዞ ይፈተለኳል፡፡ ይህንን ጉዳይ ሰካራሙ አይቶ ኖሮ እየተንተባተበ እማ … ዬ ለስ…ራ…ው ሳ…ይ…ሆ…ን ላ…ል…ሰራ…ው…ሻ…ሰ…ጠ…ሸ፡፡ …ማለት አሁንድረስ ያስገርመዋል፡፡

 

በሌላ አጋጣሚ ደግሞ ከየመን የመጣ ሰው አሱንና ጓደኛውን በመያዝ ኮከብ ሬስቶራንት ይሄዳሉ፡፡ ማን እንደሚጋብዝ ግን የታሰበበት ጉዳይ አልነበረም፡፡ ምግብ ከበሎ በኋላ የሚጠጡትን ጠጣጥተው የሄሳብ ደረሰኝ ጠረጴዛ ድረሽ ሽምጣላቸው ጓደኛው በጨረፍታ ሄሳቡን ሲመለከት ከ2000 ብር በላይ ከፍ ብሏል፡፡ ይሄን ጊዜ በመደንገጥ ለአብዱቄ ምን ተሸለን ሂሳቡን ብዙ ነው ሲለው አብዱቄ ከዚህ ፎቅ ላይ ዝለል፡፡ በማለት ግራ አጋብቶታል፡፡

 

የመጠጥ ገጠመኞች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም ነገር ግን መሠርጉ ውሳኔ ያቆመውን የሚወደውን መጠጥ ቤተሰብን በስርዓት በማስተዳደር ተክቶታል፡፡ ከሣምነተ ሁለት ቀን ጫት ይቅማል፡፡ ከቃመ በኋላ ግን የሚሰራውና የሚያባብሰው ነበር አያጣም፡፡ እንዳንዴም በሥራው ከመመሰጡ የጠነሳ ያለበትን አስከመርሳት ይደርሳል፡፡ ባለቤቱነገ ትስራዋለህ አሁን የመኝጣ ሰዓት ነው በማለት ስለምታስታውሰው ገን ዕረፍት ይወስዳል፡፡ ጫትና መጠጥን ሲያወዳድር ደግሞ እንዲህ ይላል፡፡ የሰከረ ሰው ትንሸዋን ጎጆዬን አቃጥላታለሁ፡፡ እያለ ሲፎክር በጣት የመረቀነው ደግሞ ይችን ትንሽ ጎጆ ፎቅ አረጋታለሁ፡፡ እያለ ነው እቅድ የሚወጣው፡፡

 

ከምሳ በኋላ አብዱቄ የጠጣው ቡና አላረካ ስላለው ሁለተኛ ቡና አዞ ሲጋራውን በላይ በላይ ይመግምገዋል፡፡ ዓይኑ አንድ ቦታ ተተክሎ በሃሳብ ጭልጥ ብሎ እንደ ሄደ ለተመለከተው በግለፅ ይታወቃል፡፡ የፈጣኑ ነገር ነው እያሳሰበው ያለው፡፡

 

ፈጣኑ የሚነግድበትን ብር 1,000 ያህን ከስሯል በተፈጥሮ ገራገርና የዋህ ብጤ በመሆኑ ዱቤ ሲጠየቅ ለመከልከል አያስችለውም ወዲያውኑ እጅ ይፍታል፡፡ ዱቤ ወሳጆች ግን ደሞዝ ላይ ብርቱ ጉዳይ ቢኖራቸው እንኳን ወደሱ ቤት ፊታቸውን አይመልሱም ይባላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የካርታ ቁማርም ስለማሞካክርና የንግድ ዕቅድም ስለሌለው በትንሽ ጊዜ ውስጥ መነገጃ ብሩ ወድሞበታል፡፡ በሩን በሽርክና እንዲነግድ ደሞዝትበት እንዳንድ ሰዎች ነግረውት ስለተጨነቀ ይህንኑ ለአብዱቄ ነግሮሎ፡፡ የዛቻው ወሬ የነፈሰው ከተቀናቃኝ ጫት ነጋዴዎች እሱ ከአካባቢው ዘወር እንዲልላቸው ባቀዱት ዓላማ መሆኑ ቢገመትም የህይወት ጉዳይ ነውና ፈጣኑን ረብሾታል፡፡ እንዲያውም ዛሬ 8፡00 ሰዓት ላይ ብ እንደሚል ሰው መላኩን ጨምሮ ለአብዱቄ አጫውቶታል፡፡

 

ሁለተኛውን ቡና እንዳጣጣመ ሲራውን ተርኩሳ ወደ ፈጣኑ ቤት አመራ፡፡ ል እንደደረሰ ፈጣኑና ጀማል ተኩራርፈው ተቀምጠዋል፡፡ ጀማል እስሚኛ ተናጋሪም ሰለ ነበር አብዱቄ እስላም አሊኩም አለና እጁንዘረጋ ሰውየው ንዴት ያጨለመው ፊቱ በራብሎ አሌኩም አሰላም በማለት የተዘረጋለትን እጅ ጨበጠው፡፡ በመቀጠልም አካም እያለ መልክት አደረገው? አብዱቄውን፡፡ አልሃም ዲሊላሂ ነበር የአብዱቄ መልስ፡፡ ቀደም ተብሎ የተዘጋጀውን ጣት ፈጣኑ ፎቶ መቃም እንደተጀመረ ወጋቸውም በአብዱቄ አነሳሽነት ቀጠለ በአስላሚ ቋንቋ እየተነጋገሩ ስለ ነበረም ፈጣኑ የፊታቸውንና የእጆቻቸውን መወኛጨፍ መመልከትና አልፎ አልፎ ገለታ ገቢ ኢንሽ አላህ የሚሉትን ቃላቶች በመጥለፍ በስተቀር ያዳመጠው አንዳችም ነገር የለም፡፡ ከፊታቸው ምንበብ እንደተቻለው ስምምነት ላይ የደረሱ ዓይነት መስሎ ተሰምቶታል፡፡

 

ልክ 9፡30 ላይ ነበር በረዥሙ ተንፍሰው ሲጋራ የተገባበዙት፡፡ ሲጋራቸውን እየሳቡ ከቆዬ በኋላ ማል አርብ ስምንት ሰዓት ላይ ጫት የ60 ብር ይዤልህ እመጣለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ግን እወቅበት ካሁን በፊት ላለው ይህ ትልቅ ሰው መሃላቸወን ገብቶ አስማምቶናል፡፡ አለው ፈጣኑን፡፡

 

ፈጣኑ ደስታ ፊቱ ላይ እየተነበበበት ምንም ችግር የለም ከእንግዲህ ሞኝነቴን ትቼ ነግዱ ላይ ነው የማተኩረው፡፡ ያለፈውንም ትንሽ ይቆይብህ እንጂ ከጊዜ ጋር አከፍልሀለሁ፡፡ ስላስቀየምኩህ ግን ይቅርታ አድርግልኝ፡፡ ሲል ተናገረ በዓይኑ እየተማፀነ፡፡

 

አላህ ይቅር ይበለህ እንጂ እኔስ ይቅር ብያሁ፡፡ አለ ጀማል፡፡

 

አብዱቄም ሲጋራውን እየሳበ ሁለቱንም እያፈራረቀ ሲመለከትና ሲያዳምጥ ከቆየ በኋላ ሰውነቱን ቀለል ሲለው ተሰማው፡፡ በሉ እንግዲህ ጀማልም እንደተባባልነው የ60 ብር ጫት አርብ ምሰዋ ላይ ላክ፡፡ ፈጣ እንኳን 60 ብር ምሳውንም ከጓደኞቼ ጋር ስለሆነ የሚባለው ብሩን እኔ እልክልሃለሁ፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ኃዘን ቤት ስምሄድ ይቅርታ አድርጎልኝ፡፡ በማለት ከተቀመጠበት ሲነሳ ጀማልም እኔም ሳይመሽብኝ ልሂድ ብሎ አብሮት ብድግ አለ፡፡ ፈጣኑ አበር ድረስ ሽኝቷቸው ሊመለስ ሲል አብዱቄም ዞር በማለት ጠቀሰው፡፡ ፈጣኑም እንደተደሰተ ለመግለፅ ሁለት እጆቹን ዘርግቶ ወደ ሰማይ ቀና አለ፡፡

 

አብዱቄም ከጀማ ጋር ትንሽ መንገድ ሄደው ከተሰነባበቱ በኋላ ሲለየው አልሃም ዲሊላሂ አለ በቀስታ ድምፅ፡፡ አሁን አንድ ሃሳብ ወደቀ፡፡ የሚቀጥለው ችግር ደግሞ በትላንትና ቀን አለቃው ዛቻ የስነዘረበት ጓደኛውን ትናንትና ከሰዓት በኋላ የተፈጠረ ምን አዲስ ነገር አለ ለማለት ወደ ኑርሐሰን ቤት አቀና፡፡

 

ቤቱን የእጣን ጭስ አፍኖታል፡፡ የተጉዛጉዘው አበባ ቅልቅል ሳር ለጀበናና ሲኒዎቹም ሆነ ለፍራሹ አነጣጠፍ ድምቀት አጎናጽፎታል፡፡ ኑር ሁሴን ከፊቱ ዘመን የማይሽራትን ብሪፍ ኪኪ አስቀምጦ በወረቀት ላይ ሃሳቡን ለማስፈር ይታትራል፡፡ እጁ ላይ የተለኩሰ ሲጋራ፣ በጉንጩም የጫት ተከዚና ይጠፋል ማለት ዘበት ከሆነ ዋይቷል፡፡ ጫትና የወረቀት ስራዎቹን ዓለም ዝባዝንኬ መወጪ ወይም መደበቂያ ያደረገቸው ይመስላል፡፡ ጫት ለተወሰነ ጊዜ ትቻሁ ሌሊትም የገዳም ስዕል ይመላስብሃል፡፡ በማለት ይመልሳል፡፡ እንዳንዴ ከወረቀት ሥራው ላይ ጓደኞቹ በጨዋታ ሲያናጥቡት እስክሪፕቶውን ቁጭ ያደርግና ለተወሰነጀ ሴኮንኮች በአይኑ ብቻ እያደመጫቸው አጠገቡ ያለ ሰው የማይደርስበት ቦታ በሃሳብ ተጉዞ ይመለሳል፡፡ አንድ ጊዜ ጨዋታ ጀመረ ማለት ደግሞ ማቆሚያ የለውም፡፡ በቀልድ ከጀመረ በቀልድ ይጨርሰዋል፡፡ በሥራም ከሆነ ከሥራ ውጪ ጨዋታ ለመቀየር ለደቂቃዎች ይቸግራል፡፡ ሰውን ቢወድም በትክክለኛው መንግድ የሚረዳት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ይህም ለሱ ችግር የሚፈጥረበት ጉዳይ አይደለም፡፡ ህይወት ትርጉም የሚኖረው መጀመሪያ ሥራውን ከተወጫ በኋላ ነወ፡፡ ሌላው ነገር ሁሉ ቤተሰብ፣ ፍቅር፣ ጓደኝነት ከሥራ ቀጥለው የሚመጡ ናቸው፡፡ ጫት ሲቅም አድሮ በሰዓቱ ሥራ ላይ ነው፡፡ መጠጥ ላይ አምሽቶም ይታያል፡፡ ያምርበታል፡፡ የቀመቱ አጭርነት በሩቁ የሚታይ ባያደርገውም እሱ ያለበት አካባቢ ጨዋታ ይኖራል፡፡ ስለቁመት አጥረት ሲነሳ አጭር የሆነ ነገር ሁሉ ቆንጆ ነው አጫጭሮች የሽቶ ብልቃጦ ናቸው ይላል፡፡ ረዣዥም ሰዎች ም እንደሚሉት ግን እስሁን የሰማሁት ባይኖረም እሱ በቁመቱ እንደሚደሰት ገምቻለሁ፡፡

 

የሴት ጓደኛው ሳሚራ ጀበናና ሰኒዋን ከፊቱ ድርድር አንዳንድ ጊጊ ትካድመዋለች፡፡ ሳቋ ከቁመቷ በላይ ይጉላል፡፡ ጓደኛዋን በደንብ ትንከባከበዋለች፣ ትቆጣጠረዋለች፡፡ ዛሬ ግን ከፊት ለፊቷ ያለውን ቁም ሳጥን እየተመለከተች በሃሳብ ርቃ ሄዳለች፡፡

 

በር ተንኳኳና አብዱቄና ሰላም ወደ ውስጥ ዘለቁ ተቀምጠው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ አብዱቄ ኑር ሐሰንን እሽ ምን አዲ ነገር አለ? አለቃህ ጠርቶህ አነጋገረህ? በማለት ጠየቀው፡፡ ኑር በምርቃና ደንዝዟል፡፡ ከፊ ለፊቱ በምትቀመጠው ዘመን የማይሽራት ብሪፍኬዝ አጠገብ የነበረ አንድ ወረቀት አንስቶ አቀበለው፡ አብዱቄ ማንበብ ሲጀምር ሰላም ሲጋራ አወጣና ለኩስ፡፡ ዛሬ ከወትሮው የተለየ ፈገግታ ይታይበታል ሰሞኑን ጤና የነሳው ውጥን አልባት ስለግኝ ውስጣዊ ደስታውን ከፊቱ ፈገግታ መገመት ይችሏል፡፡

 

ኑርሐሰን ግን ከምርቃናው ጋር የአለቃው የወቀሳ ደብዳቤ ተዳምሮ ያለወትሮው ዝምታውን መርጧል፡፡ ሰላም ከሳሚራ ጋር የቆት የባጡን ሲቀባጥር አብዱቄ ግራ እየገባው ከአንድ ሁለቴ ቀና በማለት እያመነታ ማንበቡን ቀጥሏል፡፡ ደብዳቤውን እንብቮ ሲርስ ሰላም ከእጅ ላይ ተቀበለው፡፡ ማንበብ እንደጀመረ አነአብዱቄ ጨዋታ ሲጀምሩ ይቅርታ በመጠየቅ ሀሳቡን አሳባስቦ ለማንበብ ወደ ሳሎን ሄደ ደብዳቤውን አንብቦ ሲመለስ አብዱቄ አንተ ገና ለጎዳዬ አዲስ ነህና፡፡ ከኔ ደግሞ በዚህ በኩል የሥራ እግዳ ዜና እያለ እናንተ የሆነ ያልሆነውን ስትቀባጥሩ ምን መሆንህ ነው ልልህ ከአንድም ሁለቴ አስቤ ነበር፡፡ ለነገሩ ምን ዓይነት ደብዳቤ ነው? ጥያቄውን በጥያቄ እየመለሰ ሁሉንም ቃኝት አደርጋቸው፡፡ ዝምታ በመኘታ ክፍሏ ሰፈነ፡፡

 

ሰሚራ ቡናውን ቀድታ በማቅረቢያ አከፋፈለች፡፡ አንቅልፍ ስሚከለክለኝ አልጠጣም የሚለው ሰላም እንኳን ቡናውን ተቀብሎ ፉት በማለት አጠገቡ አስቀመጠው አብዱቄም ሲጋራውን ከቡናውና ከሃሳቡ ጋር እየተሟገት ይሰበዋል፡፡ ኑር ሁሴን ቡና በጣም ስሚወድ ፉት እያለ ወዲያው በመጨረስ ሲኒውን አስቀመጠ ሰሚራም አጠገቧ ያለውን ስቶሽ /ምድጃ/ ሙቀቱን ለመቀነስ ከሶኬቱ ነቅላው ቡናውን ቀስ እያለች ትጠጣለች፡፡

 

አብዴቄ ከሃሳብ እንደነቃ ምንም አይደለም፡፡ የደብዳቤው ይዘት እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት አፃፃፍ አልገመትኩም፡፡ በይዘት የተገለፁት ሁኔታዎች ለእግዳ የሚያበቃ አይደሉም፡፡ ስለዚህ አንተ ሪፖርት የምታደርግበት ቦ በነገው ቀን ሄደሄ አነጋገር፡፡ አገዳውን ግን እንደእረፍት ቆጥረህ እንዳንድ የምትሰራቸውን ስራዎች ስራበት፡፡ እንኳን ጊዜ አግኝተህ ከሥራ በኋላም እቤትህ ውስጥ የምትሰራቸውን ስራዎች አሁን ጊዜ ስላገኝህ በእርጋታ አከናውን፡፡ ይህ ሊረብሽህ የሚገባ ጉዳይ ስላልነ ራስህን ብዙ አታሰጨንቅበት፡፡ አለፍ ኑርን ተመለከተው፡፡ ኑር በእሽታ መልክ ራሱን አነቃነቀ፡፡ ሳሚራም ድጋፏን በፈገግታ ገለፀቸው፡፡ ሰላምም ሊናገር ያሰበውን አብዱቄ ስለተናገረው ይኽው ነው፡፡ በማለት አጀበው፡፡

 

ለትንሽ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ከቆዬና ከተጨዋወቁ በኋላ አብዱቄ ሐዘን ቤ እንደሚያመሽ ተናግሮና ተሰናብቶ ተለያችው፡፡ ሐዘን ቤት አድሮ ሌሊት ላይ እዛው ኃዘን ቤተ አብሯቸው ያደረ ሰው የእናቱ ዜና እረፍት ቀደም ተብሎ ስለተሰማና ሌሊት 11 ሰዓት ላይ አውቶበስ ታዞ የሚሄዱ ሰዎች ሲመዘገቡና ሲሸኙ ከመ/ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር አብዱቄም አብሮ ስለነበረ በማግስቱ ምሳ ላይ አብዱቄ በትላንትናው ቀን የስምሪት ኃላፊ ሆኖ ነበር ያመሸው፡፡ የሚል የተሰነዘረ አብዱቄ ምሳውን እየበላ ይህንን አነጋገር ሲያደምጥ ፈገግ ብሎ ራሱን በመነቅነቅ ተአበኛ ግቢ እያለ በግርምት ስሜቱን ገልጾታል ለተቸገረው የቅርብ ረዳት፣ ላዘነው፣ አጽናኝ፣ ለቁም ነገር ፈላጊው ቁምነገረኛ፣ ቀው ነዋሪ ሳይቀረ በስሙ ብቻ የእርዳይታ ሰው ጥሩ መንፈስ አሳድሮበታል፡፡ እኔማ ሳስበው ይኽንን ስ እባህህ ፓርለማ ተመራጭ ሆነህ ተወዳደርልን ሳይባል የሚቀር አይመስለኝም፡፡ አወይ የሰው ዓይነተ፡፡

 

እርዳይታ በፀሐያማ ወቅት ለመጣበት የመጀመሪያ እይታው ጀምበር ወደ አድማሱ ስትጠልቅ ስሚያጣጥማትና መ/ቤቱ ከከተማ ርቆ በከተማ መሰል ህንፃዎች ስለጌጦ ድንቅ ደሴት ወይንም በዘመናዊ ገዳም ስሌት ነው፡፡

 

ከእ.አ. 305 ሊ.ሜ አኪባቢ ርቀት ላይ ስትገኝ የባህር ወለል ከፍታዋ ከ2400 እስከ 2600 ሜትር ይደርሳል፡፡ የወይን ደጋና የደጋ የአየር ጠባይ አላት፡፡ በውስጧ ያለው የካምፕ ህይወት ነዋሪውን የተለያየ ጊዜ ማሳለፊ እንዴያመቻች ሁኔታው ቢገፋፈውም አብዛኛው በካርታ ጨዋታ እየተዝናና ራሱንም እያሰጨነቀ የሚገኝባት ደሴት ሆናለች፡፡ የሰራተኞች መዝናኛ የካራምቡላ ጨዋታ ቢኖርም ሠራተኛው የቤት ቢዲ ብሎ በሰየመው የካርታ ጨዋታ ሌሊቱን ያነጋል፡፡

 

አብዱቄንም ይህ ጉዳይ ነበር አጃኢብ ያሰኝው ባል ሚቱን ጥሎ ሌሊት ሙሉ ካርታ አቀፎ የሚቀመጥበት ምስጢር አያስገረመው፡፡

 

ስለካርታ ሲነሳ ሁሌም ትዝ የሚለኝ አንድ ቀልድ አለ፡፡ ሰውየው ካርታ እየተጫወተ ስለሚነጋበት ጠዋት ቢሮ የሚገባው ስለ ካርታ እያሰላሰለ ነው፡፡ ታዲያ በአንዱ ቀን ጠዋት ወደ አለቃው ሄዶ አንድ ወረቀት ይሰጠዋል፡፡ አቶ አለቃእ ወረቀቱ የያዘው ጉዳይ እሱን የሚመለከተው ስላልነበረ ምን ላርገው? ሲል ጠየቀው፡፡ ሰውየው የመለሰለት መልስ ፐውዘው የሚል ነው፡፡ ባያስቅም ፈገግ ያሰኛል ብዬ ነው፡፡

 

የእርዳይታ የካርታ ደንበኞች ታዲያ ከሥራ መልስ አንድ ቤት ሰብሰብ ይላሉ፡፡ እንቀልድ ይጀምራሉ የምግብ ሰዓት ይረሳል፣ ማህበራዊ ጉዳይ ይዘነጋል፣ ሌላም ሌላም፡፡ የቤተሰብ ህይወት ግን በዚህ መልክ ምን ይዞ ይኖዋል? የልጆችስ አባታቸውን መናፈቅ የስነ ልቡና ችግር አያስከትል ይሆን? አብዱቄንም ያሳሰበው እንዲህ እንዲህ ያለው ጉዳይ ነው፡፡

 

የካርታ ተጫዋቶች ባበለቤቶች ባሉቻቸው ካርታ ላይ ካላደሩ አይመቻቸውም ወይንም ተሰላቻችተው ለመለያየት ጊዜ ነው የሚብቁት? በካርታ ላይ የሚፋው ጊዜ፣ ገንዘብና ማሰቢ ጭንቅላትስ ስለቤተሰብ የኑሮ ችግር ላይ፣ የወደፊት ህይወትና የመሳሳለውን በወያዩበት አይሻልም? ከዚህ ካምፕ ህይወት ተወጥቶ ከተማ ሲኖር የሚኝመውን ችግፈር ካሁኑ ለመቅረፍ ዘዴዎ ከየቤተሰቦቻቸው ጋር ቢቀይሱ ከአሁን የበለጠ አመቺ ጊዜአይነረም፡፡ ግን እኛ ምን አገባን?

 

ግን፣ ግን የካርታ ጨዋታ ከቤሰብ አልፎ ማህበራዊ ግንኙነትንም የሚያሻክርበት አጋጣሚ ይበዛል፡፡ እናም ሁላችንም ችል ማለት ያለብን ጉዳይ ስላልሆነ በየጊዜው መነጋገሩ የጨዋታው ሱሰኞችን ትኩረት እንዲሰጡበት መገፋፋትም ነውና የመነጋገሩም ባህል መለመድ አለበት፡፡

 

ለካርታ ጨዋታ አመቺ ጊዜ ተብሎ የሚወሰደው አንድ ሰው ዛን ላይ ተቀምጦ ለማስተዛዝን በሚል ሽፋን ነው፡፡ ኀዘንተኞች ሴቶ እንዳነድ ቀልዶች ሲለዋወጡ ወንዲች ግን በካርታ ይመሰጣ፡፡ በዚህ ሰሞን ነው አንዲት ሰራተኛ ኀዘን ላይ ተቀምጣለች ከተረዳች 2ኛ ቀኗ ነው፡፡ አለፍ እያ ካርታ ተጫዋቶች በቡድን ተቀምጠው ካርታው ይጨወታሉ መሸት እንዳለ አንድ ለማስተዛዘን ሰምታ የመጣች ሴት እዬዬዋን ስታስነካው ኀዘን ላይ የተቀመጠቸው ልጅም በደከመ ድምጽ አጀበቻት፡፡ ጓደኞቿም እንዲህ፡፡ አንድ አንድ ተጫዋቶች በለቅሶው ሳቢ ካርታቸውን ደገሞ ጨዋታቸው ላይ ተቀምጠው ለኔ ጂ ጦር ነው የሚስፈልገኝ እባክህ ካልሆነ ጆከር መሳብ አለብኝ፡፡ ይባባላሉ፡፡ በአንድ በኩል ኃዛን በሌላ በኩል የካርታ ጨዋታ፡፡

 

ይህ ለሚመለከተው ሰው እውን ለማስተዛዘን ይመስላል? ኀዘንተኛዋስ ምንድን ነው የሚሰማት? መሸካከር ማለትስ ከዚህ ወዲያ ምን ይኖራል? ጨዋታው ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን አዲስ ኀዘንተኛ ሲመጣ ለጊዜው ቆም ቢደረግ ምን የሚያመጣው ችግር አለ?

 

አሁን የተለመደው ገና የኀዘን ወሬ እንደተሰማገና ኀዘን ያለበት ሰው ሲመጣ ቤቱን አዘጋጅተው ጠብቀውት እንደገባ ገፍትረው ነው የሚስቀምጡት ይባላል፡፡ ከዚ በኋላ ታዲያ በቡድን የሚመጡት ሁሉ የየራሳቸውን ካርታ ይዘው ነው የሚመጡት፡፡ ለነገሩ ኀዘን ቤት ይቀጥል እንጂ ጨዋታውን ከሥራ ውጪ የሚጀምሩት በአንዳቸው ቤት ነው፡፡

 

እርዳይታ ውስ ለት/ቤት ያልደረሱ ህጻናት ሁሉ ቁጥር ማወቅ የሚጀምሩት በካርታ ነው የሚል ቀልድ መሰል አውነት አለ፡፡ ከቤተሰብ ጭቅጭቅ ምክንያቱ ካፈርታ መሆኑን እስኪረዱ ድረስ እንደ አባቶቸው በካርታ ለመጎበዝ ሳይመኙ ይቀራሉ? የቤሰብ መናጋቱ በካርታ አዳር መንስኤነት መሆነኑን ግን ካርታ ሲያዩ ሁሉ ከንዲሚዘግንናቸው ከወዲሁ መገመት ይቻላል፡፡

 

የካርታ ጨዋታ ከሚያመጣቸው ችግር ውጪ አዝናኝ ጎን እንዳለውም የሚካድ አይደለም ሱስ ደረጃ እስልደረሰ ድረስ፡፡ በሥራ የደከመን አእምሮ ከጓደኛ ጋር ለገማሽ ሰዓት በካርታ ማሳለፍ የሚጎዳ አይሆንም፡፡ በተለይ ደግሞ እንዳነድ ጊዜ የካርታ ጨዋታ ላየ የሚታዩና የሚወሱ ቀልዶች ትዝ ባሉ ቁጥር የሚያስፈግጉ ናቸው፡፡

 

ጨዋታው ህገ ወጥ እንደመሆኑ /የቁማሩ ማለቴ ነው/ በስርቆትም የተሞላ ማታለል ነገር ይባዛበታል፡፡ አንድ ተጨዋች ለሁለት ትሪስ የምትሆነው 9 ቁጥር ጦር ብቻ ኖራለች፡፡ እሱ ግን ያገኝው ሁለት 9 ቁር ጦር ሳይሆን እንድ ብቻ ናት ካሸነፈ ቆይቷል አሁን ደግሞ ሌላው ካርታ ተሰተካክሎ 9 ቁጥር ጦር ብቻ አልመጣችም፡፡ በአሸናፊነት ለመጨረስየመረጠው ዘዴ ግን ጆከርን ወይም ሌላዋን 9 ቁጥር ጦር መጠበቅ ሳይሆን በእጁ ላይ ያለችውን 9 ቁጥር ጦር ለሁለት በመቅደድ ሁለቱን ታሪስ ሰርቶባት መጠቀም ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ካሸነፋ በኋላ 9 ቁጥር ጦር መቀደዷ የታወቀው ካርታው መፐወዝ ሲጀምር ነው፡፡ የስርቆቱ ነገር መቼም ጉድ ነው፡፡ በዚህም የሚረኩት ሥነ ልቡናቸው ቢፍ ለማህበራዊ ሳይንስ አንድ ጠቃሚ ጉዳይ ሳይገኝ አይቀረም ብዬ እገምታለሁ፡፡

 

ሌላው አስቄኝ ነገር ደግሞ ከሚወቱት ሰዎች እንደኛው ሁለት ቁርን አጥበቆ ይጠላታል ወይ ተደምራ አትሞላና የልመብ አታደርስ ወይ በትሪስ መልክ ተሰርታ አትመጣ፡፡ ብቻ ይናደድባታል፡፡ በጨዋታ ላይ ሁለት ቁር ብቻ እየተደበለች 6 ካርታ ይመጣለታል፡፡ 6 ካርታዎ የሚጠላት ሁለት ቁጥር ሰብስብ አንጀቱ እርር ብሎ የወሰደው እርምጃ ሌሎች ተጫዋቶች ሳያዩት ሁለት ቁጥሮችን ሰብስቦ ቀዶ በመጣል ጨዋታውን መቀጠል ነበር፡፡ ለኛ ለአድማጮቹ አስቂኝ ቢሆንም እሱ አፎያለበት ገጠመኝ ነው፡፡ ይሄው ተጫዋች ደግሞ እንድ ቀን እየተጫወተ ሲደክበው ይንጠራራና ካርታ መታደል ይጀምረል፡፡ ቤቱ የጓደኛው ቤት እንደመሆኑ መጣሁ ብ ወደ መኝታ ክፍል ይገባል፡፡ በጀርባው ጋለል እንዳለ ሁለት ነገሮች ዓነት ይሰቡታል፡፡ ሙዝና ሸንኮራ፡፡ ከተንጋለለበት በመነሳት መጀመሪያ ሙዙን ከዚያም ሽንኩራውን በልቶ አፉን እየጠራረገ ሲወጣ ተጫዋቶች ሽንት ቤት የሄደ መስሏቸው እየጠበቁት ነበር፡፡ አይ የእርዳይታ ካርታ ጨዋታ አፍቃሪዎች የጀንበር መጥለቅንም ሆነ የጀንበር ንጋት ውበትን ሳያጣጥሙ እንዳሉ አለ፡፡ አብዱቄ እውነቱን ነው ‹ይሄ ተአብኛ› አገር በማለት ግርምቱን የገለፀው፡፡

 

የሕይወት ፍሰት /አካሄድ/ እንደ የሀገሩ ባህል፣ እንደሰው የኢኮኖሚ አቋምና አመለካከት ሀራምባና ቆቦን ያህል የተራራቀ ነው፡፡ በደህና የሀብት ደረጃ እየኖሩ ህይወትን እያማረሩ የሚኖሩ እንዳሉ ያጡ የነጡ ሆነው ራሳቸውን ላማሻሻል ደፋ ቀና የሚሉት አልታጡ፡፡ ከነዚህ ውጪ ደግሞ ባላቸው አነስተና ስራ ሆነ ሽቀላ አምላካቸውን እያመሰግኑ ..ይህንኑ ባርክልኝ ፡፡..እያሉ ተደስተው ጊዜያቸውን የሚገፉ አሉ፡፡

 

አብዱቄ የፈጣኑ ነገር እንዳሳሰበው እንደገረመው አለ፡፡ በትላንተናው ቀን ማለትም ሰኔ 22 ፈጣኑን ካገኘሁት ቆየሁ እስቲ እንዴት እነደሆነ ልጎበኘው በመለት የጠዋት ማስተማደር ስራውን ጨርሶ ወደ ፈጣኑ ቤት ጎራ ያለው ፡፡ የፈጣኑ ቤት ዕቃች ተመሰቃቅለዋል ሳሎኑ ቀለም እየተቀባ ነው፡፡ ሰራተኞቼን.. እንደምንዋላችሁ ..በማለት መንገዱ ላይ የተረጋጡትን ዕቃዋች ሰራተኞች ..ወዴት ነው .. በማለት ጥያቄያቸውን እቀረቡለት ..ፈጣኑ የለም እንዴት ..ጥያቄያቸውን በጥያቄ ሲመልስ በአገጫቸወ በማመልከት .. እዚህ ነው የተኛው ፡፡ .. ብለው ይነግሩታል ፡፡ ወደጠቆሙት አቅጣጫ ሲመለከት አልጋው ሳሎን ውስጥ በሰያፍ ተቀምጣል ፡፡ እንዴት ብርድልብስ ጣል አድርጎ የተኛም ሰው አለበት፡፡

 

..እሱ ተኝቶ ነው እንዴ እናንተ ቀለም ቤቱን የምትቀቡት ደግሞስ እንዴት ይመቻችሃል.. ሲል ጠየቃቸው አብዴቄ ቀለም የሚቀቡትን ሰራተኞች ፡፡

 

..ሌላ ጊዜ መጥተን እንቀባ ስንለው ግድ የለም እኔን አትረብሹኝም ሰላለን ነው አሱ ባለበት አካባቢ ስንቀባ ቀስብለን ከነአልጋው ፎቀቅ እናደርጋዋለን ስንጨርስ ደግሞ እንመልሰዋለን ስንጨርስ ደግሞ እንመልሰዋለን ፡፡.. አሉት ፡፡

 

አብዱቄ የመርገም ፈገግታ ተላብሶ ራሱን እየነቀነቀ ወጣ፡፡ ..ምን አይነት ህይወት  ..የሚለው ጥያቄ እየተመላለሰበት ነበር ያገኘኝና ይህንኑ ያጫወተኝ፡፡ በሃሳቤ የመጣው በጥንት ዘመን የኖረውና ያለፈው ግሪካዊ ፈላስፋ ዲዮናግን ነበር ፡፡ዲዮጋን ከውሃ መጣጫው ቅል በስተቀር የኔ የሚለው ሃብት ንብረት ያልፈለገና ምስኪን /ለዘመናችን / ሆኖ የኖረ ሲሆን አንድ ቀን ባህር ዳር ተቀምጦ እያለ በባህሩ በኩል የሚያልፍ መንገደኛ በእጅ የባህሩን ውሃ ጨለፍ አርጎ ሲመጣ በመመልከት ያችን ብቸኛ ንብረቱን ..ለካስ በህይወት ጎዳና ይቼም ቅል ትርፍ ፎራለችና በማለት ሰብሯት መገላገሉን የአቶ ስብሃት የጋዜጣ ጹሁፍ ላይ ቆየት ባለ ጊዜ ማንበቤን አስታወስኩ፡፡

 

ከሃሳቤ ያነቃኝ ..ሃይበጣ ..የሚል ንግግር ከአብዱቄ ሲሰነዘር ነው፡፡ .. አየህ ከነሻሸጎበና ሌሎች ሰዋች ጋር ተሰብስበን እያለን ያ አልይ የሚባው ልጅ በአጠገባችን ሲያልፍ ..አንካን ደስ ያለህ .. እያሉ ሲጨብጡት ምን አግኝቶ ነው  አልካቸው ፡፡ በመ/ቤት ለእግረኛነት ተወዳድሮ ስላሸነፈነው ብለው ሲመለሱልኝ ሃየበጫ፡፡ ትዝ አለኝ ሃይበጫ ምን መሰለህ ሲዳሞ ውስጥ እንዲት ኑሮዋ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ጉሊት ውስጥ ቅመም ጥመም እየቸረቸረች የምትኖር ሴት እመሻሽ ላይ ጓዟን ሰራተኛ ቀጥፈራ አሸክማ ወደ ቤቷ ስታመራ ያያት ሰው የተናገረው ቃል ሃበጫ በማለት ሲሆን፡፡ ይቺም ኑሮ ተብላ ሰራተኛ መቅጠር አስፋለጓት ዓይነት ትርጉም ያለው ምፀታዊ አባባል ነው፡፡ የአነጋገር ፈሊጡ ዕየገረመኝ በአንድ ወቅት ስለ ደራሲና ጋዜጠኛዋ መንግስቱ ገዳሙ የሰማሁት ወግ ከዚህ ላይ ላነሳው ወደዱኩ፡፡ 

 

ደራሲ መንግስቱ ገዳሙ ያሁኑ ፒያሳ አራዳ እየተባለ በሚራበት ጊዜበተለያዩ ነገር የታጨቀውን ቦርሳውን ለአንድ ፈረንጅ በወር ከሚያገኝው የራሱ ደሞዝ በላይ እየከፈለ ያዞረው ነበር አለ፡፡ ለዚህም ምክንያት ሲሰጥ ጥቁር ህዝብም ነጩን በአሸክርነት እንደሚሰራው የሀገሬው ህዝብ ይመልከትና ይወቅ ብሎ ሲሆን ምን ያህ እውነት ነት እንዳለው ግን በበኩሌ ለማረጋገጥ አጋጣሚያች አልፈቀዱልኝም ጨዋታውም ጨዋታ ያነሳዋል እንዲሉ ጠቃቅስጄት እብጂ፡፡

 

በየአካባቢው ኩሩ ህዝቦች እንደሚኖሩ ቢታወቅም እንዳንድ ጊዜ ከማህበረሰቡ በየአጋጣሚው ጉልተው የሚጡ መታየታቸውን ሁሉም ያሰደንቀናል፡፡ ከዚህ ጋር የሚያያዝ አንድ ሌላ ገጠመኝ አለው አብዱቄ፡፡ በመስክ ሥራ ክባልደራቦቹ ጋር ወደ ከምባታና ሃዲያ መስመር መኪና ይዘው ይወጣሉ፡፡ የምሳ ሰዓት ደርሶ ምሳ ከተባለ በኋላ ጉዞ ሊጀምሩ ሲሉ አንድ በዕድሜ የገፋ ሴት ጫት ይዘው ወደ መኪናው ይጠጋሉሉ፡ አብዱቄ ስንት ነው? ይጠይቃል አሮጊቷም መሸጫ ዋጋ እንዲነገሩት፡፡ 75 ሣንቲም እየተከራከሩ ዋጋወን 5 ሳንቲም ደረጃ አደረሰው፡፡ ከ5ቷም ሣንቲም ጊዜ አሻራውን በጣለበት ዓይናቸው መልከት አርገውት ከኔ ከባሰብህ ወሰደው በማለት እጁ ላይ ጣሉለት፡፡ አብዱቄም ወይ ሕይወት እያለ ከኪሎ 1ብር አወጥቶ እጃቸውን ላይ አስቀምጦ ጉዟቸውን ቀጠሉሉ፡ እኝህ አሮጊት ገን ያን ቀን ሞተው ይደሩ ይም አበደው  ይደሩ አብዱቄ እንዳላወቀ ይናገራል፡፡ ወይ ኑሮ! የአቶ ክፍሌ አቦቸር ተኖረና … ለኒኝ መስል ገጠመኞ ይሆን ስንኙ የጠቋጠረው?

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የማዶና ደሴት ብቸኛ ነዋሪዎች

ሃሪ አርኖልድ እንደዘገባው

በደቡባዊው ፓስፊክ ንጋት ፈንናቋል፡፡ በትንሿ ደሴት ውስጥ ቆዳው በፀሐይዋ የጠየመው ሰው ከእንቅልፍ እንደነቃ የአሳ ማጥጃውን መረብ ወደ ሐይቅ ወረወረው፡፡

 

በደቂቃዎች ውስጥ የመረቡ እንቅስቃሴ አሳ መጣመዱን ስላበሰረው ለባለቤቱ ቁርስ በማለት ተጣራን ባለቱን በዚን ሰዓት ከእንቅልፏ ተነስታ ሶስቱን ልጆቿን እያለባበሰች ነበር፡፡ የጥሮፒኳም፣ ፀሐይ በበሩ በኩል አለሁ እያለች በልቹ ገላ ላይ ታብረቀርቃለች፡፡

 

ከደቡባውው ቄልስ፣ ስዋንሲያ ለመጡት የሚሊናም ቤተሰቦች በትፍስህተ ገንተ ውስጥ ዛሬም ሌላ ቀን ናት፡፡ የ31 ዓመት ዕድሜ ያለው ቶኒ ዊሊያምስና ባለቤቱ ካቲ እንዲሁም 3 ልጆቻቸውን በኒውዘላድ አየር መንግድ ከ10,000 ማኮልስ በላይ ተጉዞዋል ጭር ባለ ደሴት ላይ መኖር የሚለውን የልጅነት ጊዜ ህልሙን ዕውን ለማድረግ፡፡

 

‹ገነት አይደለም እንዴ?› ከህብረተሰብ መግለል ለማለት ይህ ከሆነ ምንም ጊዜ ቢሆን በመርከብ ላይ አደጋ ደርሶብኝ እንዲህ ዓይነት ቦታ ብወድቅ ደሰታዬ ወሰን ያለውም ይላል ቶኒ፡፡ ማዶና በኩክ ደሴቶች ላይ በተንጠላለው ሰማያዊ ሐይቅ ትንሽ ቦታ ናት 150 ማዶልስ ያህል ወደ ደቡባዊው ምዕራብ ራሮቶንጋ ትጠጋለች፡፡

 

ከዚህ ቦታ ነበር ከፎቶ ግራፍ አንሺዬ ሃሪ ፔጅ ጋር እኒህን ቤተሰቦች የተቀላቀልኳቸው፡፡

 

‹ወደ ገነት ደሴታችን እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡› አለ ቶኒ በፈገግታ ክሬግ የ11 ዓመት ማቲው የ7 ዓመት እና የ4 ዓመተቷ ስታሲ የጠባሉ ልጂቹ ዙሪያችንን ከበቡን

 

ከጭውውታችን እንደተረዳሁት ከአራት ዓመት በፊት ቶኒና ባለቤቱ ብቻቸውን በሌላ ደቡባዊ ፓስፊክ ደሴት ለ6 ወራት መቆየታቸውን ነው በዚያን ጊዜ ከተፈጥሮ ጋር ላደረጉት ፍጥሚ ብዙም ዝግጅት አልነበራቸው፡፡

 

ወደ ሐይቅ ዳርቻው በምናዘግምበት ወቅት ማላበቴሰቡ በፀሐይም ንዳድ ቆዳቸው እንደተለበለበ ተመለክተኩ የቶኒቆዳ ግን የበለጠ ጠቁሯል፡፡ ቆዳው ከትከሻው አካባቢም እየተሰነጣጠቀ ነበር፡፡

 

ማንኛችንም  ብንሆን ደህን ያህል የፀሐይ ንዳድ አለ ብለን አላሰብንም ፀሐይም ግለቷን የምትጨምርበት ወቅት በመሆኑም በጊዜ ምርጫዬ ተሳለቿለሁ ለፀሐይ ቃጠሎ የቆዳ ቅባት ብናመጣም ያን ያህል ፀሐይዋን ሊቋቋመው አልቻለም ለፀሐይ ቃጠሎ የሚሆን መድሃት መያዝ እንዳለብን ደግሞ ፍፁም ዘንግተናወል ከሁላችንም የከፋው ቃጠሎ በኔ ቆዳ ላይ የሚታየው ምግብ የማምጣት ኃላፊነቱ በኔው ተከሻ ስለወደቀ ነው አለ ቶኒ፡፡

 

ካቲ ምግብ ለማብሰል ያያዘቸው እሳት ላይ ቆሞ እግሩ የተጎዳበት ማቲው እግሩን ያክማልበ የምግብ ማብሰያቸውም በጣም ጥቂት ነው፡፡ ከልበስ ሌላ ካቲ ሁለት ማብሰያ ድስት፣ የዓሣ ማጥመጃ መሳሪያ፣ ባትሪ፣ ቢላ፣ ትንኝ መከላከያ፣ ሶስት ፍጣዎች፣ ትንሽ የህክምና ዕቃዎችና ለችግር ጊዜ የሚረዱ የደረቁ ምግቦች ይላለች፡፡

 

እና ክብሪቶች እኔም ሆንኩ ቶኒ እንጨትን ከእንጨት ጋር በማፋተግ እሳት ለማደንደድ የምነደርገው ሙከራ አይሳካልንም ወደ ፀጉር ሰሪ ቤ መሄድ አያስፈልገኝም፡፡ ሽቶም ከጥያቄ የሚገባ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የወባ ትንኞችን ይስባል፡፡ የፊ ሜክ አፕም እዚህ ቦታ ትርፍ ነው፡፡ ፀሐይዋም ራሷ በጥሩ ሁኔታ ፊትን ታጠይማለች በማለት ካቲ ነገረችን፡፡

 

ነገር ገን ካቲ ሙዚቃን ናፍቃለች፡፡ የካሴት ማጫወቻ አልያዘችም፡፡ የያዙት የቴክኖሎጂ ውጤት ቢኖር በዚህ የፓስፊክ ደሴት የሚያሳልፉን ጀብድ የሚቀርፁበት መሳሪ ብቻ ነው፡፡

 

ቶኒም ቆንጨራ መሰል ነገር አለው፡፡ የሚጠጣ ነገር ፈልጌ ቆንጨራውን ከቶኒ ተቀብዬ አንድ የኮኮናት ጫፍ ለመቁረጥ ብሞክር አልተሳካልኝም ብዙ ስለ ስራ ሳይደለዱም አይቀርም፡፡

 

ካቲ በሐይቁ ጨዋማ ውሃ ልብስ የምታጥብበት አነስተኛ መጠን ያለው ሳሙና አላት፡፡ ምንም ምቾት የላችም የጠርሙስ ወይም የቆርቆሮ መጠጥ ያለም፡፡ አልጋ ወይም ትራስ አይታደም ትንሽ መጻሕፍት በቀር የጠፈጥሮ ብርሃን ብቻ ነው ሃብታችው፡፡  

 

የመጸዳጃ ቤት ችግርን ለማቃለል ቶኒ ጥሩ የሆነ አካፋ ለማምጣት አስቦ በስህተት ሳይዘው መጥቷል፡፡ ባገኝው እንጨት ለመቆፈር ተገጿል፡፡

 

የውሃ ችግረም ሌላውየተወሳሰቦ ጉዳይ ነው፡፡ በደሴቱ ላይ ንፁህ ውሃ አይገኝም ስለዚህ ከኮኮናት ውስጥበሚገኝው ውሃ ተስፋቸውን ሙሉ በሙሉ ጥለዋል፡፡

 

ብዙዎቹ አውሮፓውያን የኮኮናት ወተት ሁልጊዜም ጣፋጭ እንደሆነ አድርገው ነው የሚያስቡ፡፡ ነገር ገን ፍሬው ገና ሳይበስል ውስጡ ያለው ፈሳሽ ልክ እንደ ንፁህ ውሃ ነው፡፡ የውሃ ጥማታቸውን በዚህ ያቃልሉታል፡፡

 

ክሬደግ ለኮኮናት ሰብሳቢነት ራሱን ሾሟል፡፡ ማቲውም የቆሰለውእግሩ ሲድነለት ልክ እንደ ወንድሙ ሊሆን ተስፋ አድርጓል፡፡ ማንኛቸውም ይህንን ከባድና አስዳች ያልሆነ ህይወት አላማረሩትም፡፡

 

እየተጫወተን ሳለ ቶኒ ወደ ባለቤቱ መልክት አድርጎ ቁርሳችንን አሳውን በጥሬ ብንባለው ይሻላል? በማለት ጠየቃት፡፡

 

የኮኮናት ወተት ስለለ በሱ እቀቅለዋለሁ፡፡ ልጆቹንም ማንጎዎ እንዲያመጡ አልካቻዎለው፡፡ ስተልመለሰችለተ ቶኒም ወደ እኛ ዞር ብ አያችሁ በኮኮናት እና ዓሳ ብቻ መኖር ይቻላል፡፡ አለና ሳቀ

 

ደሴቱ ውስጥ ማንጎ እና በካፒቴን ኩክ ያወድድ የነበረው የዱባ ፍሬ በብዛት ይገኛል ካፒቴን ኩክ በጊዜው ይህንን ፍሬ ወደ ጀማቲካ እየወሰደ ለገናገዴዎች ይሰጠው ነበርነጋዴዎቹም ለባሮቻቸው እንደምግብነት ተጠቅመውበታል፡፡ ካቲ ከዚህ ፍሬ እየቆራረጠች ዳቦ ለመስራት አሳ የሚያጠምዱ ቶኒና እሷ በቡን ሲሆን ሁላችንንም የሚመግብ በቂ እሷ ለማጥመድ በባህሩ ውስጥ መረባችውን ሲጥሉ በፈጋግታ አስተዋልኳቸው፡፡

 

ቶኒ እንደሚነገረው እንዲሁ ሲታይ ያን ያህልም ባይሆን በዓም ላይ ካሉት ነገሮች ሁሉ አስደናቂው ትዕይንት ነው ማለት ይቻላል፡፡ ቤት የሚፈራው ከአንዱ ዛፍ ሊላኛው ላይ የኮኮናት ቅጠሎ በማጠላለፍ ሲሆን ሌሊት ሌሊት በሰማይ ተንጣለው ይኖራሉ ከምትሏቸው በላይ ብዛት ያላቸው ኮኮናት ማት ትችላላችሁ፡፡

 

ቶኒ ወደ ሃይቁ ዳር ተንሳፈው ከመጡ የእንጨት ቁርጥረጮችና የኮኮናት ቅጠል በመታገዝ ጎጆ ቀልሷል በጠረጴዛም ከወደደቁ እንጨቶ ሰርቷል፡፡

 

የቤተሰቡ ምግብ ማብሰልና የቤት ስራ ካን በፊት የምታውቀው ነገር ቢኖር ረሰታዋለች፡፡ በየቀኑ የምትሰራው ዓሣ ስሚሆን ስለሜኑ አትጨነቅም ሁልጊዜ ዓሣ የሚሰለች ቢሆንም በጥቂት መጠን ካመጣችው የጣሳ ልጋ ማጠፋጫ ዓይነት ትጠቅምበታለች፡፡ መርከባችው ተሰብሮ ከአደጋ እንደ ተረፈ ዓይነት ሰዎች አኗኗር ለማየት ስለሆነ ዓላማቸው ተሳክቶላቸዋል ያሰኛል፡፡

 

ወንደኪቹ ልጆች ደሴቱ ላይ ሰዘዋወሩ ሁለት ሴት ዶሮዎችና እንድ አውራ ዶሮ አግኝተው ዕንቁላል መጣያ ቦቸውን ለማወቅ አስሰው ለመድረስ አልተቻለቸውም ይህን ቦታ እስካላገኙ ድረስ ደግሞ ኦመሌት የመብት ሃሳባቸው ህልም እንደሆነ ሊቀር ነው፡፡

 

የተለያየ አልሚ ምግብ ማግኝት ቢችግርም ሃይጂን ግን ከችግር ዝርዝር ውስጥ አይገባም፡፡ በቀን ለብዙ ጊዜ ሐይቁ ውስ እየተነኮሩ ይወጣሉ፡፡

 

የቶኒን ፊት የፀሐይ ግረት እጅግ አጠይሞል፡፡ የፀጉሩም መንጨብረር ላየው ሰው ሮቢንሰን ክሩሶንን ያስታውስበታል፡፡ ‹ለሳምንታት ያህል መስታወት አላየሁም፡፡ ለነገሩ ምን እመስላሁ?› አለና ጠየቀኝ፡፡

 

‹ሽፍታ!› ብዬ መለስኩለት፡፡ ቤተሰፈቡ ሁሉ በሳቅ ተንከተከተ

 

የምታቀጥው ፀሐይ ውደ ምዕራቡ አድማስ እየተጠጋች ነው፡፡ እኒህ ዘመዶቼ ከመኝታ በፈት አራታቸውን ተቋድሰዋል፡፡ ስታሲ ወደ እናቷ ሽጉ ስትል ወንዶ ልጆ በሰማይ ላይ ያሉትን ኮኮቦች ለማየጥ ከአባታቸው ጋር ተቀመጡ፡፡ ‹እጅግ በጣም ወደነዋል፡፡ ምናልባትም እስከመጨረሻው ማለት እንችል ይሆናል፡፡› አለ ቶኒ

 

‹የእጅ ሥራ ጉዳይ ብዙም ስለማልችል ሮቢንሰን ክሩሶ እንደሰራው ዓይነት ጀልባ አንኳን እንዴት እንደሚሰራ አላውቅም እናም አልስቅም ብለህ ቃል ግባልኝ እንጂ ዋናም አልቻልም፡፡› ብሎኝ የበለጠ አስገርሞል፡፡