ህይወት ? ክፍል 1
… ማን ነበረ ይች ዓለም የተውኔት መድረክ ናት ህዝቦቿ ናቸው … ያለው? እኔ ሌላ መስፈሪያ ፍለጋ አይደለም ዓላማዬ በዚች የተውኔት መድረክ ተዋናዮቿን እላይ እታች፣ አንዴ ሐዘን ሌላ ጊዜ ደስታ፣ እንዲያፍሩ ደግሞ እንዲጠሎ፣ እንዲፈሩ እና እንዲደፈሩ፣ እንዲራቡ አለያም እንዲጠግቡ ወዘተ … የሚያደርጋቸው የተውኔቱ ድርሰት ልበለው? ህይወት ላይ ነው ትኩረቴ፡፡
አንድ የስራ ባልደራባዬን ነበር ህይወት ምንድን ናት ብዬ የቡና ዕረፍታችን ላይ የጠየቀቀኋት፡፡ … ሁሉም ነገር /ድርጊት/ ህይወት ነው በማለት ከጀመረችልኝ በኋላ ህይወት የተቃራኒ ገጠመኞችና ክስተቶች ጥርቅም ናት፡፡ … አለችኝ፡፡ እኔም ከሷ አባባል ተነስቼና ከፈላስፋው ጥያቄ ጋር በማቆራኝት የትኩረቴ መንደርደሪያ አደረግሁት፡፡
የህይወት የትናንሽ እስረኞች ጥርቅም ናት፡፡ /በግርድና ትርጉመ/ የሚል መንፈስ ያለው የእንግሊዝኛ ጥቅስ ከረዥም አመታት በፊት ማስታወሻ ደብተሬ ላይ ማስፈሬ ትዝ ይለኛል፡፡ ይህንን ጥቅስ ያፈለቀው ሰው በህይወት ትላልቅ ነገሮች የሜሌቸው ነገሮች ያልተጠመው በሌሎችም ህይወት እንዲሁ በሱ ግምት ትናንሽ ነገሮች ብቻ ሲከውኑ የመስከረ ይመስለኛል፡፡ /… ይመስለኛል የሚለው ቃል ሞኞች የፈጠሩት ቋንቋ ነው … ባትሉኝ፡፡/
ይህን አባባል በአንድ ወቅት የተገናሩት ሰው /አሁን ነፍሳቸወን ይማረውና/ ህይወታቸውን የኖሩት በሥራ ተጠምደውና መጻህፍትን ሲያነቡ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አንድ ጊዜ በክፍላቸው ያለ ሰራተኛ ለነገ ፈቃድ ይስጡኝ ወንድሜ ያገባል ስለዚህ ለሰርጉ አንዳንድ ሥራዎን ማገዝ አለብኝ ይላቸዋል፡፡
ሰውየውም ዕድሜ ርጋታን ባለበሰው ድምጻቸው … ነገ ሥራ አለ፡፡ ይልቅ ወንድምህን ሌላ ቀን እንዲያገባ ንገረው፡፡ … ብለውት በእጃቸው ወደያዙት ወረቀት አቀረቀሩ፡፡ … በማለት ያጫወተኝ ፈቃድ ጠያቂው ሠራተኛ ነበር፡፡ እኝህን ሰው አጋጣሚውን አገንቼ ህይወት ምንድን ናት? ብዬ ብጠይቃቸው ኖሮ … ህይወት ሥራ ናት … አይሉኝም ትላላችሁ?
አንድን ሰው በሃሳባቸው ባሉት መካከለኛ ቀመት፣ ነጻት አቆላላፍ የተዛነፈና ጽዳቱም ያልተጠበቀ፣ ድፍርስ አይኖችና የረሳውን ዕቃ የሚያሳለስል ዓይነት መፍዘዝ የሚታይበትን ሰው … ህይወት ምንድን ናት? … ብትሉትና ከመቅጽበት … ጠጅ … ባላችሁ ትገረሙ ይሆን? እኔ አይገርኝም ምክንያቱም ይህን የጠጅ ወዳጅ ጠጅ በማይጠጣበት ጊዜ ህይወት አስፈሪ አቦ ሃማ ዓለም ትሆንበትና ለሷ እሾና አስፈሪነት ለመሸሸግ የጠጅ ጋሻ አስፈላጊው ነውና፡፡ /እኔ ግን ጠጅ ሲሸተኝ አልወድም፡፡/
ቦሌ አካባቢ ያለውን የህይወት ተውኔት ተመልክታችሁ ወደ እኛ ሰፈር ደግሞ ብቅ ብሎ፡፡ ልዩነት የተ የለሌ ነው፡፡ መምባሳም ህይወት አለ ሞቃዲሾም እንዲሁ፡፡ ሄሮሺማና ናጋሳኪም ይኖራል፡፡ የህዋይ ደሴቶችና ቤቨርሌሄልስም እንዲሁ፡፡ ሁሉም ቦታ ህይወት አለ የሰማይ ምድርን ያህል ርቀት ያህል፡፡ /ግን የሰማይርቱ ከመሬት ምን ያህል ይሆናል?/ ተዉት ተዉት የመጀመሪያውን ጥያቄ መልሱ፡፡
አንድ የሳንንስ ፕሮፌሰር ጋዜጠኛው ለጠየቃቸው መልስ ሲሰጡት እንግዲ አስቸጋሪ ጥያቄ ስትጠይቃቸው ህይወት ምንድን ናት ብለው ብተጠይቁኝ ይሻል ነበር ብለው ይመልሳሉ፡፡ … በማለተት ስለጥያቄው አስቸጋሪነት በብልሃት እንደመለሱለት አንድ ከወደ አወሮፓ በኩል የዘለቀ የወጣቶች መጽሔት ላይ እንብቤያለሁ፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?
…../
ህይወት …? ክፍል
ማይከል ንክሰን የሚለወን መጠሪ ሰንሰማ በዓላማችን ከተወለዱ በጣም ጥቂት እድለኞች መካከል አንድ አንዱ አድርግን የምንገምት ብዙዎች ነን ብዬ አስባለው፡፡ በእርግጥም በሥራው ከፍተኛ ደረጃን ይዞ ቆይቷል፡፡ ገንዘብም ሞልቶ ተርፎታል፡፡ በሌላ ወገን ድግሞ … ትሪለር … የተባለውን የሚዚቃ አልበም ሲያወጣ ለዚህ ሥራው ስምት በአሜሪካን ፕሪዚንት ነው ቤተመንግስት ተጋግዞ እንደነበርም የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ው፡፡ ይህ ዘፈኑ ሙገሳን ብቻ አልነበረም ያጎናጸፈው፡፡ … በአብደት በተሞላ የሙዚቃ ስልትና በቀለሙ ዓለምን ሊለውጥ የተነሳ ጥቁር … ተብሎ እስከመተቸትም ደርሶበታል፡፡ ለአድናቂዎቹ መመለስ ደረጃ ቢበቃም በግላዊ ህይወት ልቦናው የፈቀደው መዝናኛ ቦታ ለመሄድ ግን ራሱን ለመለወጥ መነጽር፣ ባርኔጣ ሌላም መደረብ አለበት፡፡ ካልሆነ የሩብ ሰዓት ፊልም አንኳን ሳያይ መዘጋጀት ሊኖርበት ነው፡፡ በአንድ ወቅት ለህጻናት በጎ አድራጊነት ሰምገስ ቆይቶ አሁን ደግሞ አንድ ህጻን ልጅ በመድፈር የተከበር ስሙ እየጠፋ ነው፡፡ የህይወት አካሄድን አንድ በሉልኝ፡፡
ማዶና ስሟን ያልሰማና ፎቶራፏን በየመንገዱ ተለጥፎ ያላየ የሀገራችን ሙዚቃ አፍቃሪ ክፍል አለ ብዬ ለማሰብ እቸገራለሁ፡፡ ከሙዚቃ ስልቷና ውዝዋዜዋ ጋር ከአልባሳቷ ጋር የምታንጠለጥለውም መስቀል ምልክቷ ወደ ወሆኑ ተቃርቧል፡፡ በተለይም በታዳጊዎችና በወጣቱ ክፍል እንከን አይወጣላትም በመባል ጥብቅና የሚቆሙላት ብዙ ናቸው፡፡ በእድሜ ከወጣትነት ደረጃ ዘለል ያሉት ደግሞ ቀጥ አጣች፣ ለልጆቻችን መጥፎ አርአያ ሆነች እየተባለ ሂስ ይሰነዝርባታል፡፡
በአንድ ወቅት ኡ ለተባሉና በየጊዜው ለተነሱ የሆሊውድ ፊልም ቤት ተዋንያን ልባቸውን ወክክ የሚያደርግ የሱን ልብ ግን ለመንኛውም ያልሰጠ የተባለለት ኖረን ቤቴም በመጨረሻ የማየሰበር ልብ ገጠመው እየተባለ በማዶና ታምታባታል፡፡
ማዶና በየጊዜው በአለባበሶና በመድረክ እንቅስቃሴዋ በወላጆች ብትታማም ለአብዛኛው ሰው እግዚኦ የሚያሰኝ የራሷን ቅጥ ያጡ የፎቶግራፎች ሰብስባ እኔን ካልጨነቀኝ በሚል በመጽሐፍ አሳትማ ለሽያጭ ስታቀርበው መገናኛ ብዙሃን ሲያበጠለጥሏት በመጀመሪያው ቀን ሽያጭ ብቻ ለመግመት የሚያስቸገር ዶላር እንዳፈሰች አልሸሸግም፡፡ የማዶናን የህይወት አካሄድስ ሁለት አላላችሁም?
የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት ፈርድናንድ ማርቆ ሥልጣን ላይ እንዳሉ ተቀናቃኛቸውን አስገድሎ ተባለ ከጊዜ በኋላ ከስልጣን ተባረው ከባለቤታቸው ጋር ወደ አሜሪካ ሲኮበልሉ የሟች ባለቤት ከራዞን አኩዊኖ ሥልጣን ላይ ተቀናጠው ከብላዮቹ በስደት በተቀመጡት ሃገር በማጭበርበር ወንጀል የአሜሪካ መንግስት በፍርድ ሰምታችው ንግስቷ ባል 6.000 ጫማ ባለቤት ነበሩ አሁን አሜሪካ ከገቡ በኋላ የጫማ ነገር አያሳስባቸው የሬዲዮ ንግግር ከየቦታው ያሉት ሴቶች አሜሪካውያት በላኮላት ጫማዎች የሬዲዮ ፕሮግራሟን የምታሰራጭበት ቢሮዋ ተጣቦ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ያ ሁሉ አልፎ ንግስቲቷ ባለቤታቸው አዛው አሜሪካ ከሞቱ በኋላ ወደ ሃገራቸው እንደተመለሱና በተከሰሱበት ወንጀል ፍርድ ቤት እየተከራከሩ በጎን ወንዱ ልጃቸው ከሀገር ውጪ የተቀናቀኞችን የዘመድ ልጅ መሠርግ ሊያገባ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የሼክስፒር ገፀ ባህርያት የሮሚዎና የጁልየት ቤተሰቦች ባለንጣነትና የነሮሚዎ ፍቅር ጋር አልተመሳሰለባቸሁም? ነገር ግን ህይወት ምንድን ናት?
ህይወት?. . . . ክፍል 3
በፕላኔታችን ካሉት ታላላቅ የሃይማኖት ሰዋችና በጎ አድራጊዋች ማዘር ትሬዛ በከፍተኛ ደረጃ ስማችው ይወሳል፡፡ ህይወታቸውን ሙሉ ለበጎ አድራጎት ስራ ሰውተዋል ፡፡ የእርዳታ እጅ የሚያስፈልጋቸው ሰዋች ባሉበት ሁሉ ማዘር ቴሬዛ ደከመኝ ልረፍ ሳይሉ ይገኛሉ ፡፡ እያንዳንዷን ደቂቃ የተቸገረን ሲረዱ፡ የታረዘን ሲለብሲ ፡ የታመመን ሲያጽናኑ ሲጸልዩ ያሳልፋታል፡፡ ይህን ሁሉ በጎ ነገር ለአንድ ሰው አይበዛም ወይ ተብለው ሲጠየቁ ሁሉንም የሚያደርገው እግዚአብሔር ነው ለሱ ምን ይሳነዋል በማለት ይመልሳሉ፡፡ በሥራቸው ውጥን ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዋች ቢገጥማቸውም እግዚአብሔር በተአምሩ የታቀደውን እንደሚያሳካው ይናገራሉ ለእንደ ማዘር ቴሬዛ ዓይነት ቅዱሳን ህይወት ማለት እምነት ነው ብንል ያስሞደን ይሆን ?
በሃገራችንም በብጽዕነታቸው ብዙ የተባለላቸው አቡነ ተክለ ሃይማኖት በአንድ ወቅት የኢትዮጲያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ነበሩ ፡፡ አማማታቸውም ከእምነቴ ፍንክች እልልም ብለው በረሃብ እራሳቸውን አዳክመው ነው ይባላል፡፡ ለእምነት ኖረው ለእምነት መሞትን እዚህ ላይ ያስተውላል፡፡
በዚህ ረገድ ባለፈው ኣመት ማገባደጃ ላይ በአሜሪካን ሀገር መሲህ ነኘ ተብሎ ሰለተበነሳው ኮሬሽን የህይወቱ ፍጻሜ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ሰዋችን በማሳመን ችሎታውና በመጽሐፍ ቅስ እውቀቱ ብዙዋችን ያሳተው ኮሬሽ በምፅአት ቀን የማጎን ህይወቱ ያለፈው በመቶዎች የሚዎጠሩ የሰዎችንና ሕጻናትን ሕይወት ይዞ ነው፡፡ ይህንን ምን ይሉታል?
ካለፈው ዓመት ድርጊቶች ሳንመጣ አንድ የአየርላንድ ከፍተኛ የሃይማኖት ሰው ብፁዕ ነው ሲባል ቆይቶ ከብዙ ዓመታት በኋላ ከአንዲ ሴ የወለደው ልጅ መኖሩን ጋዜጦች ሲያትቁ የተወሰነ ግዜ ዜናውን ሲያስተባብል ቆይቶ አልሆነ
ሌላው ወደ ላቴን አሜሪካ መኮብለሉስ ምን ስያሜ ያስጠዋል? በሃይማኖ መርባ ብዙዎ በህይወታቸው የቆሸሹትን ለዚህ የሃይማኖት ሰው ተብዬ ሲናዘዙ ቆይተው፣ ንስሃ ገብተው ብዙዎች ባለፈ ባገደመ ቁጥር … የሰይጣን ድል መንሻና የክብር መውረሻ … መስቀል ተሳልመው የኋላ የኋላ እምነቱን የካደ ሰው መሆኑን ሲያውቁ ግራ ሳይጋቡ ይቀራሱ?
እምነታቸውን ከደው በህይወታቸው የሸፈጡሰዎች ከራሳቸው ጋር እየተጣሉ ለመኖራቸው አሌያም አይባልም ቤተክርስቲያን የምታዘውና የአገልጋዮቹ ተግባር የማይገናኙበት ብዙ ጊዜ ተከስቷል፡፡ በአንድ ሃይማኖት ጥላ ስር ተሆኖ ግጭቱ ይፈፋማል፡፡ የእግዚአብሔር ቤትም ለተወሰኑ ከፍሎች ለማድረግ ሙከራዎችም ይታያሉ፡፡ በእግዚአብሔር ስም እንዲህ ዓይነት ነገር መፈፀሙ በጣም ያደናግራል፡፡ ለነገሩ እምነት ሲያስቀጣም ተሰተውታል ዋቢ መጥቀስ ቢያስፈልግ የፊሊፒንሱ ጳጳስ ማኒሊ ውስጥ በቀረበላቸው 666 የታርጋ ቁር ባላት የዲፕሎማቲክ መኪና በምንም ተአምር አልሳፈርባትም በማለታቸው በገንዘብ መቀጣታቸው እንደ ማስረጃ ሊቀርብ ይችላል? የሃይማኖት ሰው በህግ ሲዳኝ አስቲ አስቱት ግን ሕይወት ምንድን ናት?
ህይወት? ክፍል 4
በመዲናችን አውራ መንገዶች መተላለፊያ ላይ የትራፊክ ህግ እስኪፈቀድላቸው ቆሞ ከሚሎ እግረኞች ወይንም ባለመኪኖች … የዳቦ መግዣ ሣንቲም … እርጥባን የሚለምኑ አንድ ፍሬ ልጆች መታየት ከጀመሩ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው፡፡ ልብሳቸው እላያቸው ላይ ያለቀ፣ ሰውነታቸውን ውሃ ከነካው የሰነበተ፣ የቀኑ የፀሐይ ሐሩር፣ የማታው ብርድና የጠዋቁ ውርጭ ገላቸውን ያደነዘዘው እነኝህ አምቡ ልጆች ገና በዚህ ትንሽ ዕድሜ ለዚህ ሁሉ ፍዳ መዳረጋች ለምን እንደሆነ ለሚጠይቁበት ሩቅ አይሆንም፡፡ ከልመናቸው ባሻገር እርጣባን የሚወረውሩላቸወን ሰዎች፣ ፊት ነሰተው የሚያመናጭቋቸውን አለፍ ሲልም የሚሰድቧቸውን በልጅ ጭንቅላታቸው ቀርፀው የሚይዙት ምናልባትም ከሜችሉት በላይ ይሆናል፡፡
እዛው የመኪና መንገዶች ላይ ከመንገድ ወጣ ባለች አነስተኛ ቦታ ትናንሽ ጎሎች ሠርተው በጨርቅ ኳስ ቀልባቸውን አጥተው የሚጫወቱ ደግሞ እሱ ለዛውም በባዶ እግራቸው፡፡ ጎሎች አካባቢ የት/ቤት ደብተሮች አልፎ አልፎ አይጠራም፡፡ እነኝህ አንድም ከት/ቤት ቀርተው አለበለዚያም የት/ቤት የወር ክፍያ በወቅቁ መክፈል ሳይችሉ የተባረሩ ናቸው፡፡ ወላጆቸው የወር ክፍያውን ከእጅ ወደ አፍ ከሆነች ኑሯቸው ቀናንሰው እስኪከፍሉ ድረስ በመንገድ ዳር ኳስ ጨዋታ ነፍሳቸውን ያስደሰታሉ፡፡ የወር ክፍያ ሳያቋርጡ እየከፈሱና ደህና እየለበሱ በሜማሩት ጓከኞቻቸው በትንሿ ልባቸው እየቀኑ፡፡
ከእነሱ በዕድሜ ብዙም ያልራቁ በቤተሰብ ተጽዕኖ ከትምህርት ሠዓት ውጪ ሊስትሮ፣ ጋዜጦች፣ ሎተሪ እና ሌላም ሸቀጦች ይዞው በአንድ በኩል ቤተሰብ እየደገሙም የሚኖሩ ልጆች ብዙ ናቸው እነዚህ ልጆች ከእንዳንዶች በቀር ት/ቤት የተሰጣቸውን የቤት ሥራዎች በአግባቡ እየሰሩና እያጠኑ ከክፍል ወደ ክፍል የሚሸጋገሩት በጣም ጥቂት ቢሆኑ ነው፡፡
ከዚህ ዕድሜያቸው ትምህርትም ሥራም አቅማቸው የሚፈቅደው አይደለም፡፡ ከትምህርት ሠዓት ውጪ ካልሰሩ ደረቅ ዳቦ እንኳን ሲያረባቸው ነው፡፡ የቤተሰባቸው የኑሮ አቅም ደግሞ አያወላዳም፡፡ ያላቸው ምርጫ እንደምንም ተሯሩጠው መኖር ነው፡፡ የልጅነት ጨዋታ በልጅነት ዕድሜ አያምራቸውም ገና በልጅነታቸው ችግር ብዙ አስተምሯቸዋል፡፡
በታዳጊ ዕድሜ ያለ ሌሎች ደግሞ አሉ ከቤት ወደ ት/ቤት ከት/ቤት ወደ ቤት ቤት እንደደረሱ እረፈት አድርገው፣ የቤት ልብሰ ይቀይራሉ፡፡ መክሰስ አማርጠው ይቀርብላቸውና ከግቢ ሳይወጡ ይጫወታሉ ከጨዋታ በኋላ ወደ ጥናት፡፡ በማግስቱ ቆንጆ የት/ቤት ልብስ ከዘመኑ የልጆ ፋሽን ልብሶቻቸው ለዚያ ቀን ደስ ያላቸውን ለብሰው በሜወዱት የምሳ ዕቃ ምሳቸውን ይዘው ወደ ት/ቤት፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ያለይዋቸው የቪዲዮ ካሴቶች ይመጡላቸዋል፡፡ ከት/ቤት ጓደኞቻቸው ጋር ስልክ ይደዋወላሉ፡፡ የሚሂድባት የቤትሰብ መኪና የትራፊክ መብራት ሲያስቆማት አኒያ የመንገድ ላይ እርጥባን ፈላጊ አንድ ፍሬ ልጆች ወደ መኪና መስተዋት ጣጋ ብለው እጃቸውን ይዘረጋሉ፡፡ መኪና ውስጥ ያሉት የቤት ልጆች አይስክሬም እየላሱ ሲሳሳቁ ለእርጥባን የቆሙት አንድ ፍሬ ልጆች ያዩዋቸዋል፡፡ … አቤት ባርኔጣ እቤት ቀሚስ ደግሞ የሚባሉት ነገር ሲያስጎመጅ … ምራቃቸውን ሲወጡ አባትና እናት የመኪና መስተዋቶችን ግጥም አርገው ዘግተው በዚህ … ደባሪ … የትራፊክ ቀይ መብራት ላይ ኮተር ብለው ያፈጣሉ፡፡ ለእርጣባን የተዘረጉት እጆች መኪናውን መዳበስ ሲጅምሩ ቀዩ መብራት ጠፈፍቶ ቢጫና አረንጓዴ ሲበራ በደመ ነፍስ ወደ መንገድ ዳር ወጣ ይላሉ፡፡ መኪናዋም እኒን ቆንጆ የለበሱ ህጻናትን ይዛ ትፈተለካለች፡፡ እርጣባን ፈላጊዎቹም ዓይናቸው እንደተንከራተተ፣ ዕንባ እንዳቀረረ ሌሎች ተረኛ መኪኖ ይጠብቃሉ፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?
ህይወት ? ክፍል 5
በዓለም ላይ ስንኖር በፈለግነውና ባሰብነው መንገድ ሳይን እያንዳንዷ ቀን ባልተገመተው ሁኔታ ነው እየከነፈች ያለችው፡፡ ምክንያቱ ግን ለብዙዎቻችን ግልፅ አይደለም፡፡ በርግጥ በግላችን ኑሮም ሙሉ በሙሉ ወሰኝ አኛው ባለመሆናቸን ለነገሩ አስተዋጾኦ ይኖረዋል፡፡
ከእኛነታችን ስንነሳ በጤንነትና በማህበረሰቡም ተቀባይነት ኖሮን ለመቆየት የተወሰኑ ያልተጻፋ ህጎችን መጠበቅ ይኖብናል፡፡ ለምሳሌም ብንወስድ የግል ጽዳታችንን የቀን ተቀን ክትትል አድርገን መጠበቅ የሃይዲን ሳይንስ ህጉን በተለይዩ ሁኔታዎ አቀበሉናል፡፡ ይህን ህግ ካልጠበቅን ጥገኛ ነፍሳት ሰውን መቅረብ እስኪያሳፍሩን ድረስ ሊጎዳኙን ነው፡፡ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብም ካልተመገብን የውስጥ ተሃዋስያን ሆዳችን ውስጥ እየጯጯሁ ጤናችንን ሲያናጉትና ከማህበራዊ ህይወት ሊያርቁን ይዘጋጃሉ፡፡
በቤተሰብ የኑሮ ተቋም በእኛነታችን ለቤተሰቡ ፍቀር ስንል የምንከፍላቸው ግዴታዎች ወይም ያልተጻፉ ህጎች ያስጠነቅቁናል፡፡ ከነኝህ ግዴታዎች አንዱ ካልተሟላ ያለን መዋደድና መተሳሰብ አደጋ ላይ መሆኑንም ለማወቅ … ኮሌጅ መበሠስ የሚያሰፈልገው … ጉዳይ አይንም፡፡ እያንዳንዱ አባል የቤተሰብ ፍቅር ፀንቶ መኖር ከፈለገ ከሱ የሚጠበቀውን ግዴታ መወጣት አለበት፡፡
ቤተሰብ ያለ ጎረቤትም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ይፍጥራል፡፡ መኖሪያችን በአጥር ስለተከለለም አትድረሱብኝ የማለት ደረጃ ከባህልና ኤኮኖሚ አቋም እንኳን ስንገመገም አልደረሰንም፡፡ ስለዚህም ቤትና ጎረቤት ዘንከን ሳይግጥማቸው ኑሮን ለመግፋት አሁንም በውስጥ የሚታወቁ ድንጋጌዎ ይኖራሉ፡፡ ጎረቤት ልብስ አያጠቡና አያሰው ከሆነ ቤቶቻችን ጣላቢ ቆሻሻ ለማቃጠል መነሳት የለባቸውም አለያ በዘልማድ የታወቁት ድንጋጌዎች ጥሰው ከጎቤት ይቀያየማሉ፡፡ ከቤት ግብዣ ኖሮ ተጋዛዥ በሙዚቃ መደሰት ካለበት የጎረቤትን የእረፍት ቀን ወይንም የእንቅልፍ ሠዓት ማደፍረስ አይገባም፡፡ ድንጋጌዎች ከተበላሹ ገን የከፋ ቀን ደራሽ የጎረቤት ወዳጆችንን ልቤ እንዲርቀን ምክንያት ሆነዋል፡፡
እንግዲህ ጎረቤት ካስቀየምን ስማችንም ማህበረሰቡ ውስጥ ሲነሳ ነው፡፡ ማህበረሰብ የሰፋ ደረጃ ቢኖረውም በዕቁቡ፣ በዕድሩና ሌላም የመረዳጃ ማህበራት ውስጥ ለመቀጠል ያልተጻፉትንም ሆነ የተፃፍጽን ህግጋት ማክበር ቀዳሚ ግዴታችን ነው፡፡ ከማህበረሰብ መውጣት ማለት ከባህር ውስጥ የወጣን አሣ መሆን ነውና፡፡
ከዚህ ላይ ያልተፃፉት ህጎች ሙሉ በሙሉና ከተጻፍትም በከፊል ሰው በማህበረሰቡ አዛውንቶች ይመከራል፣ ይወቀሳል፣ ይቀጣል፡፡
አንድ ሰው በሌብነት ወንጀል ቤከሰስ ህግ ተላልፏልና በፖሊስ ታድኖ ፍርድ ፊት ይቀርባል፡፡ እዚህ ላይ እንግዲህ እንደ ህግ አስከባሪ ሆኖ ፖሊስ ተጨምሯል፡፡ ሥራውም አጥፊዎን እያደነ ለጥፋታቸው ፍርድ እንዲቀበሉ ማድረግ ስለሆነ ተገቢ ቦታ አለው፡፡ የፖሊስ የስራ ተግባሩ ለማህበረሰቡ በጣም የተቀደሰው ሲሆን በዚህ ሙያ የሚሰማራው ሰው ራሱ ህግ ተላላፊ ወንጀላኛ ለሆነስ? የህግ የበላይነት አበቃ ያስኛል፡፡
ስላልተጻፈም ሆነ ስለተጻፈ ኅግ ከሁሉም በፊት የህሊና ፍርድ ወይም የህሊና ሚዛን ወሳኝነቱን ለሰዎች ልጆች ባይደበቅም የህሊና ሚዛኑ በብዙዎች ዘንድ ከተረሳ መቆየቱ እህህ …… ያስብላል፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?
ህይወት? ክፍል 6
በሃገራችን የእግር ኳስ ስፖርት ሲነሳ አብረው የሚነሱ ስፖርተኛ ከጅምሩ አሁን እስካለበት ድረስ ያደረሱ፣ ከሃገርም አልፈው በአህጉና በዓለም በከፍተኛ ደረጃ የታወቁና ከብር የተለረሳቸው ድንቅ ክቡር አቶ ይድቃቸው ተሰማ ይጠቀሳሉሉ፡ የአንጋፋው የስፖርት ሰው በአካል ባናገኛቸውም የህይወት እያሉ የፈጸሟቸውና እየጉላ ነው፡፡ …ስፖርትና ጎጂ ባህሎች ሌጣመሩ አይገባም ስለዚህም በስተዲየሞች ያሉ የጎጂ ሱስ ማስታወቂያዎች መነሳት አለባቸው፡፡ … አፍሪካን በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ዋንጫ የሚወከሉ ቡድኖች ቁጥራቸው ከፍ ማለት አለበት… የሚሉት ነጥቦችን ማቅረብ ለቅሱስ ዓላማቸው ቁርጠኛነታቸውን ሲያሳዩ የሚችሉ ምሳሌዎች ናቸው፡፡
እንዲያውም ቅዱስ መጽሐፍ ላይ … ነብይ በእግሩ አይከበርም… እንዲሉ ካልነ በቀር ለክቡር አቶ ይድነቃቸው መታሰቢያ እስካሁን እንድም አለ መደረጉ ወይም ሲመከር አለመስቱ ወይ ጊዜ፣ ወይ ጊዜ እያሰኝ የስፖርት ቤተሰቦችን ማንገብገቡ በብዙ ቦታ ይደመጣል፡፡ በዓለም ደረጃ ብዙ የተነገረላቸው እኚህ … የጀብራልተሩ አለት… ሞሮኮ ውስጥ አንዱ ስቴዲየም በስማቸው መሰየሙ ለኛ ፌዴሬሽን ጆሮ አልደረሰ ይሆን?
ከእግር ኳስ ስፖርት ሳንወጣ የጊዮርጊን ሺ መለያ ቁጥር 8/ን/ ለብሶ የጎል አካባቢውን ሜዳ /ቃላቶቻችን እንደሚያስታውሱት/ በቁጥጥሩ ሥር የሚያደርገው የጎል ካፒታኑ መንግስት ወርቁ ጨዋታም ካቋረጠ በኋላ በአሰልጣኝነት ገፍቶበት ከአፍሪቃ አሠልጣኞች ቀዳሚነቱን ደረጃ የያዘ በሙያው አንቱ የተባለ ሆኖ በተወለደበት ሀገር ላይ ግን ለ ጡረታ መሰናበት አያደር መገረሙ አይቀርም፡፡
ያደላቸው ቸሎታ ያለውን ከሌላ ሀገርም ቢሆን ለምነው፣ ተደራድረውና ተንከባክበው ያስሩታል፡፡ ከእኛው ሀገር ግን የሀገሪቱን ብርቅ ልጆች የሚያቆሉ ሁኔታዎ ገጥመውናል፡፡ አረ ወገን ዜው ካለፈ በዋዛ የሚተኩ ሰዎች አይደሉምና ተገቢውን ትኩረት እንንፈጋችው፡፡
ስለክቡር አቶ ይድነቃቸው የአለም ጋዜጠኞች የመሰከሩላቸው ራሱ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው፡፡ …ከመቀረት መዘግየት… ይሻላልና እንተባበር፡፡
ከሀገር ወጣ ብለን ደግሞ እሰኪ ወደ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ አሬና ላይ ባለፉት ቅርብ ዓመታት ሲወደስና አብረውት ከሚጫወቁት ግዝፎ የወጣውን ማራዶናን ለአፍታ እናስበው፡፡
ይህ የአረጀንቴናው ተወላጅ ዲዮጎ ማራዶና በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ የሀገሩ ስም ሁለት ጊዜ ያስጠራ የሀገሪቱ ብርቅ ልጅ ነው፡፡ በጨዋታው ድንበር ተሸግሮና ውቅያኖስን አቋርቶ ጣልያን ክለቦች ረዘም ላለ ጊዜ ሲጫወት በዓለም ላይ ስ ከዳር እስከዳር ናኝቷል፡፡ ሀብፈትም ጉርፎለታል፡፡ በስፖርት ዕቃዎችና የተለያዩ ነገሮች ላይ ስሙን ማስተዋወቁም አድርጎ ተዝቆ የማያልቅ አግኝቶበታል፡፡ ለማራዶና ኑሮ ግን ብዙም አልተመቸውም፡፡ በፍቅሩ ወይንም በግንዘቡ የተጠመዱ ሴቶች አላስወጣ አላስገባ እያሉትና ሁለቱ ያህልም ይወስዳል በሚል ክስ ፍዳ መክራውን አይቷል፡፡ የማፊያ ቡድንም ዋ አያለው ቆይቷል፡፡ በእግር ኳስ ከፍተኛ ዝነኛ ሀብት ያገኛው ማራዶና ስሙ በቤትና በሃሺሽ ተበጠልጥሏ፡፡ ኑሮ የሚባለው አባዜ ትንሹንም ትልቁንም በትለያዩ ሁኔታዎች አያሠጋው ነው፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?
ህይወት? ክፍል 7
… አይ ጊዜ አይ ጊዜ… ብዮ ብጀምር ግዜን መወንጀል እንዳይመስልብኝ ፈራሁ በእርግ የልማት ክንውኖችም ሆኖ የጥፋት ድርጊቶች በጊዜ ውስጥ ያልፈው፡፡ ለልማቱ አስየው ሲባልለት ለጥፋት እርግማን አይቀርለትም፡፡
በዘመናችን ብዙ ጥሩ ነገሮች እንደታዩና እንደተከወኑ ሁለ መአቶችም ተከስተዋል፡፡ ለምሳሌም ያህል የአካባቢው አይር መሳሳትና መቀደድ በውጤቶም ኋይለኛውን የፀሐይ ጨረር ንዳድ በምድር እንዳንድ ቦታዎች ላይ የአየር መዛባትን እስከትሏል፡፡ የእርሻ መሬቶች ደርቀዋል፡፡ ብዙዎችም በእርዳታ እየተደገሙ ከረሃብ ድነዋል፡፡ ለድርቅ መስፋት የአዞን መቀድድ ድርሻ ያኑረው እንጂ ከቦታ ምክንያቶ ይለያያሉ፡፡ የተባይ፣ የአረም በሽታዎችም ከመከላከል አቅም በላይ በሆኑበት ቦታ ትንሽ የማይባል ጉዳት አድርሰዋል፡፡
በመሬት መንቀጥቀጥ፣ ጎርፍ ለመጥለቅለቅ፣ እሳት ቃጠሎ በመሳሰሉት ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮ ህይታቸው ያለፈው፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው፣ የእድሜያቸውን ያካበቱት ንብረታቸው የወደመባቸው፣ ቤተሰባቸው ተበትኖቻቸው የተሳቀቁ እጅት ብዙ ናቸው፡፡
አሳሳቢውና የሰው ልጆች አፈጣኝ መፍትሄ ሊያደርጉለት የሚባው ደግሞ ሰው ሰራሽ የአካባቢ ግጭቶችን በውይይት እንዲፈቀ ማድረግ ነው፡፡ በምስራቅ አፍር ጎረቤታችን በሆነቸው ሶማሊያ በመካሄድ ላይ ያለው የፖለቲካ ብጥብ ሀገሪቱን በሰው ህይውትና በኢኮኖሚ እያዳሸቃት ነው፡፡ ህዝቦቿም ወደ ጎረቤት ሀገሮች ስደት ተዳርገዋል በአንጉላ፣በደቡብ አፍረካና በዩዝላቪያ የተፋፋመ የእርስ በርስ እልቂ ችል ተብሎ ሊታይ አይገባውም፡፡ በእርግጥ አሁን በደቡብ አፍሪካ የሚካሄደው የፖለቲካ ፓርቲዎች ለነፃ ምርጫ ፉክክር ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም፡፡ ነገር ገን ከረጅም ዓመታት በፊት የተጫረውን እሳፈት ማጥፋት አለበት፡፡
የሰው ልጅ የኑሮ አቋም በበሽታውም ወገን በጣም አስከፊ ዕጣ ድርሶታል፡፡ ኤድስ፡፡ በሽታ ከተፈጥሮ ጋር የተቆራኝ መሆኑ ቢታወቅም የመስፋፋቱ ጉዳይ ግን ሰው ሰራሽ ነው ማለት የሚቻልበት ደረጃ ተደርሷል፡፡ ምክንያቱም የበሽታ መዛመቻ መንገዶችን በጸመለከጸ መግናኝ ብዙኃን ከመቼው ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ተምህርታዌ መግለጫዎን፣ ማስታወቂያዎችን አሰራጭተዋል፡፡ በተለያዩ የበጎ አላማ ማህበራት በራሪ ወረቀቶችን … የህይወት ጃኬቶችን … እከፋፈለዋል፡፡ ነገር ገን አልፎ የሚነገረው የበሽተኞች ቁጥር መጠን ከፍ ለማት ግን የሰው ልጆች ለሚሰጡት ትምህርቶቸ ልቦናቸውን እንዳልሰጡ ያመለክታል፡፡
በአንድ ወቅት ከወደ ሩቅ ምስራቅ የተደመጠው ዜናም የሚዘገንን ነው፡፡ በህንድና በታይላንድ የኅህጻናት ሽያጭ፡፡ በለጋ ዕድሜያቸው ወደ ሽርሙጥና ዓለም የሚደረጉት ህጻናት ዓይናችውን ከፍቅረተንዋይ ያሳወራቸው አረመኔዎ ነው፡፡ ይህ በዚህ እንዳይቀጥልም መላው የሰው ልጅ በአጭሩ ለመቅጨት መፍትሔውን መሻት ያስፍልገዋል፡፡
ከኢጣሊያ ያለው የማፊያ ድርጅትም ለህግ ወጥ ድርጅቱ መበልጸግና የማሕበረሰቡን ሰላም ሰቆቃ እንዲመላበት ድርጅቱን አጥብቀው የሚቃወሙትን የፐሊስ ኃይሎች፣ የፍርድ ቤት ዳኞንና የመንግስትን ባለሥልናት በየቦው ከነቤትሰቦቻቸው እየፈጁና የህዝቡንም ሰላማዊ ኑሮ አያደፈረሱ ይገኛ፡፡ የኩልምቢያ የአደንዛዥ ዕፅ ተደጃሮች ከኢጣሊው ማፊያ ከሚያደርሰው በደል አይደለም እየፈፀሙ ያሉት፡፡
ባሁን ጊዜ ስላሎች ችግሮች ሙሉ በሙሉ መጥቀስ አባይን በጥፋት ይሆናል፡፡ ለነገሩ ግን ህይወት ምንድን ናት?
ህይወት? ክፍል 8
ዘመን ዘመንን እየተካ ሲሄድ ትውልዱም እንዲሁ ተክቶ ማለፍ አይቀሬ ነው ከዘመን ጋር አብረው የሚስወጡተፈጥሮዊም ሆኑ ማህበራዊ ክስተቶች በየትውልዱ ላይ ከሚያትሙት አሻራ ለቀጣዩ ትውልዱ ስብዕና ወሳኝነት አላቸው፡፡
ከአያቶችን ዘመን ስንነሳ ሰዎች በየተሰማሩበት መስክ ለፍተው ደክበመው የተገኝውን እነሱም በዛ ከቤተሰብ ተከፍለው፣ ከሥራ ውጪም ከዕድአኩዮቻቸው ጋር ፀጋቸውን አውግተው /ለልማት ሥልም ሆነ ለሽምግናል/ አደባባይ ውለው አመሻሽተው ይገባሉሉ፡
የነሱ ልጆ /የኛ ወላጆች ማለት ነው፡፡/ ከብት አያገዱ ወይንም ሌላ ስራ እየሰሩ የልጅነት ጨዋታችውን ከጓደኖቻቸው ጋር ተዋዘተው አሳልፈውታል፡፡ ከፍ እያሉም ሲሄድ የቤተ ህክነት የትመህርተን ቀስመው አሌም የቤተሰቢቻቸው ዱካ ተከትለው ከጠነከሩ በኋለ በየስራ መስኩ ተስርተዋል፡፡ ገበሬውም ወደ እርሻው፣ ነጋዴውም ወደ ንግዱ፣ ወደ ወትድርና ወደ እጅጥበብና ሌላም ሌላም ሙያዎች ላይ በመሰማራት ቤተሰብ መስርተው እናነ ተክተዋል፡፡
የድሮ ሰው ኩራቱ ተተኪ ልጅ ማፍራተቱ ነው ይባላል፡፡ … ተተኪልጅ… ታዲያ በዘመኑ የነበሩ የራሱ መስፈሪያ ነበረው፡፡ እግዚአብሔርን ፈሪ፣ ሰውን አክባሪ፣ ወላጆቱን ጧሪ የሚሉት ሐረጎች ከነበሩት መመሪያዎች ይደመራሉሉ፡
እናም እንግዲ ት/ቤት ገብተን፣ከዚህም ሥራ ላይ በመሰማራት እየተፈጨረጨርን ሲሆን ዘመናችን ግግ በብዛው መልኩ በቴክኖሎጂ እየታገዘ ወላጆቻችን ከኖሩበት ይልቅ ኑሮን የተቃለለ አድርጎልናል፡፡ ይህ ፈጣን የቴክኖሎጂ ዘመን ግን የነጠቀንም ሀብቶች ትንሽ አይደለም፡፡ ባህላችንን፣ እና የመኖር ዋስትናችን ለዋቢነት በቂ ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡
ወላጆቻችን ሃይኖታችውን ይዘው ርጋታ በሞላበት ኑሮ ዘመኑ በፈቃደው ሁኔታ መና ብሎው ኖረዋል፡፡ እኛ ደግሞ ከቴክኖሎጂ ወጣቶች ሁካታ ጋር ርካታም ሳናጋኝ እንደተነጫነጭን እንዳለን አለን፡፡ ጊዜው ከመጠቀም አኳያ ወላጆቻችንም እኛም ዛሬን እንደሰት በሚለው ዘይቤያቸን ጊዜውን ቁም ነገር ሳንሰራበት አያሳርፍ ነው፡፡
ምናልባት እኛ ከተዘናጋንበት ለመንቃት አሁንም ጊዜ አለን፡፡ ነገር ግን የተበታተነውን ትኩረታችንን አሰባስበን በመወያየት አንድ ነገር መጀመር አለብን፡፡ ወቅቱ እያለፈብን ከሄደ ለልጆቻችን የምናወርሰው ጉዳት ልጆቻችንን ወደፊት የሚያሳርፍ እንዳይን ጥረቱ ከዛሬው ይጠበቅብናል፡፡
ልጆቻችን የሚኖሩበትን አካባቢ አለፍ ብለውም ሀገራቸውንላቅ ሲልም ዓለማችንን በጊዜው እንዲውቁና ለማህበራዊ ኑሮ ጥሩ እውቀት እንዲኖራቸው በቤትም ሆነ በት/ቤትም የቀን ተቀን ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡
ከሀገራችን ጥያቃዊነት አኳያ ዘሬ ያለንበት ሁኔታ በተለያየ መድረከ ሲገመገም ብዙም ፈቅ አለማለቱ ለምንድን ነው? የሚለው ጥያቄ ከህሊና ወጥቶ በአደባባይ የታረክ ሊቃውንት፣ የስነ-ልቡና ጠበብቶች፣ ሌሎችም የማህበራዊ ሳይንስ ጠበብቶች ሊነጋገሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጭንቅላት እየተገገዋለለም ዐማታት መቁረ አሁንም የቀጣይን ትውልድ ዓይን ሽፍኖ ራስንችለህ ሄድ ከማለት አይለይም፡፡
አያቶቻችነ ኖረው አልፈዋል፡፡ ወላጆቻችንም ሲሰሩ የሚችሉበትን ጊዜ ጨርሰውታል፡፡ ነገር ግን ለልቻቸው የሚነገሩትና ለለንበት ደረጃ ምክንያት የሚሆን አያሌ አውነታዎችን ለመሰክሩልን ይችላሉና የቀራቸውን ጌዜ ከመጠቀም ባንቀጥብ ብልህነት ይመስለኛል፡፡ እኛም የተወሰነ መሰሪያ ጊዜ አለን፡፡ /የት ለመድረሰ ካልተባልኩ፡፡/ ለልጆቻችን ዋና ቀናውን ካሁን ማውረስ መቻል ተገቢነው ባይነኝ ገን ህይወት ምንድን ናት?
ህይወት? ክፍል 9
ብዙነሽ ወደ ቢሮ ስተወጣ ግቢዋን የሚጠበቅላት ላስቻለው የተባለውን ከትንሽነቱ ያሳደገችውን ውሻ ዘወትር እንደምታደርገው ደባብሰው እንገቱ ላይ ካለው ቀርቶ ጋር የታሰረበትን ሰንሰለት አላቀቀችለት፡፡ ላስቻለው እየፈነደቀ ግቢን አንዴ ከዞረ በኋላ ተመልሶ መጥቶ እግሯን ስር ተጋደመ፡፡ ዓይኗ እንባ አቅርሮ … መተኪያ… ብላ በቀስታ ተናግራ የግቡዋን በር ዘግታ ውጣች፡፡
ቢሮ አስከትደርስ የምታስላስለው የጓደኛዋ አስቴር ስለተላከላት የልደት ቀን ጥሪ ወረቀት ነበር፡፡ አስቴር ጋር ተኳርፈው ከተላያዩ ሦስት አመታቸውን ይዘዋል፡፡ አብሮ አደግ ጓደኛዋ ጋር የተከራረፈበት ጉዳይ ቀላል ቢሆንም ጥፋቱ የሷ ስላልሆነ በጣም አምርራ ተለይታታለች እየዋለ ሲያድር አስቴር ጥፋቷ ስለገባት በሰበቡም ይቅርታን ለማግኝት ሁለት ጊዜ በየዓመት የልደት በአሏ ላይ እንድተገኝላት ብትጠራትም ብዙነሽ … ካሁን ወዲህ ሰው ለምኔ… በማለት አልተበገረችላትም፡፡
…ላስቻለው… በሚል ስያሜ የምጠራውን ውሻም በህጻንነቱ ማሳደግ የጀመረችው ከምትወዳት ጎከኛዋ ጋር ተኮራርፋ ስተለያይ ሲሆን ለውሻው በግል …መተኪያ… ትለዋለች፡፡ የአብሮ አደግና የሚወዱት ጎደኛን ማስረሻ ለማሰለት፡፡
አብሮ አደግ ጓደኛዋ አስቴር አሁንም ሳትሰለች ለሦስተኛ ጊዜ በላከችላት የጥሪ ወረቀት በአጥሩ የእግዚአብሔር ይቅር ባይነት በማንሳት ይህንን ሶስት ዓመት ልቧ እያለቀሰ እንደተሰቃየችና ለመጨረሻ ጊዜ ጥሪውን እንደላከችላት የሚገልፅ የማስጠንቀቂያ ጽሁፍ ከግርጌው ሰፍሯል፡፡
በቢሮው የክፍል ኃለፊነቷ ብዙነሽ በቀልጣፋነቷ የተመሰገነች ቢሆንም በዛሬው ቀን በምትሰራው ሁሉ ነገር ላይ ፊቷ የኃዘን ደባብ እየተበበበትና እንዳንድ ጊዜም ትናንሽ ነገር ሁሉ እየረሳች ፀሐፊዋ ለአንድ ጉዳይ ሁለት ጊዜ መሳሳቷን ነግራታለች ከዚህ በኋላ ነበር ፀሐፊዋም ብዙነሽ ሰዎች አንዳይረብሿት ባለጉዳዮችን ለሌላ ጊዜ እየቀጠረች ያሰናበተቻቸው፡፡
ምሳ መድረሻ አካባቢ ስልክ ተደወለላት ከሃሳብ ማጥ ውስጥ አስበርግጎ ስወጣት ስልኩን ገላምጣው በንዴት ብድግ አደረገችው፡፡ ታዲዋስ ነው ከውሻዋ ቀጥሎ የምትወደው የወንድ ጎደኛዋ፡፡
ለምሳ ወጥቶ እንዲስዳት ከነገረቸው ሀኋላ ስልኩን በመዝጋት የሚደላው ወንበር ላይ ተደግፋ በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ የቢሮ ጠረጴዛዋ ላይ በስጦታ ወረቀት ተጠቅልሎ ገብ ያለውን ናሽናል ፓናሶኒክ የሙዚቃ ማጫወቻ ቀኝ ላይ ዓይኗ ሲያርፍ ከሶስት ዓመት በፊት ስለተከሰተው ሁኔታ በትዝታ አስታውሰ ቁጭት ያበስላስላት ገባ፡፡
ያልተነጠፈው አልጋ ላይ ጋደም ብላ አስቴር ያዋስቻት ትንሽ ቴፕ የሚያንቆረቁረውን …አይ አዎ በሶሌንግ… የሚለወን የሮድ ስቴዋርት ዘፈን እያዳመጠች፡፡ ያልተነጠፈው አልጋ ስላልተመቻት ብድግ በማለት የአልጋ ልብስ፣ ብርድ ልብስ አንሶላ አነሳስታ ማንጠፍ ጀምራ ሳትጨርስ ከአልጋው አጠገብ በተቀመጠው ኮሜዲኖ ላይ ያለችው ትንሽ ቴፕ በብርድ ልብሱ አማካኝነት የሲሚንቶው ወለል ላይ ውብላ ወድቃ ብትንቅኗ ወጣ፡፡ ብዙነሽም ደነገጠች እየቆየችም ስትሄድ ደግሞ አይኗ ቲማቲም እስኪመስል አነባች፡፡ አስቴር ከወንድ ጎደኛዋ በስታ ያገኝቻትና የምትወዳት ቴፕ ነበረች፡፡ ብዙነሽ ለቅሶዋን ሳትጨርስ ለጎደኛዋ የቴፑን መርዶ በስልክ ስታደዳት አስቴር …በፍቅር ህይወቴ መጣሽብኝ ካሁን አንተዋወቅም አትድረሽብኝ… ነበር ያለቻት፡፡ ብዙነሽ ስልጁን ቀስ ብላ ዘግታ ስታስበው መናደዱን ተያያዘቸው፡፡
የቢሮው በር ተንኳክቶ ፀሐፊዋ የምሳ ሠዓት መድረሱን ስታበስራት ነበር ከትዝታዋ የተመለሰችው ብዙነሽ ለፀሐፊዋ መልሰካም የእረፈት ቀን ተመኝታላት በአንድ እጇን የስጦታውን ፓኬት በሌላው ቦርሳዋን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጋ ስትወጣ ፀሐፊዋ ፓኬቱን ልትረዳት እንደምትችል ብታስታውሳትም ግድ የልመ… የሚል ሰጥታች በችኮላ ተንደረዳረች፡፡ የመ/ቤቷን የውጪ በር እንደወጣች ታዲዎስን አመኪናው ውስጥ እንደተቀመጠ አየችው መኪናው ጋር ደርሳ በሩን ከፍታ እንደገባች በልቧ የመነኩሰች ልዕልቴ ሰላምታዬ ይድረስሽ… በማለት ሳም አደረጋትና ጭኗ ላይ ያለውን የስጦታ ዕቃ ተመልከቶ መኪናውን አንቀሳቀሰው፡፡
ሆቴል ግብተው መሳ ቀርቦላቸው ሁሉ ዝምታ ሰፍኗል በመሃላቸው፡፡ ከምሳ በኋለ ቡና እየጠጡ ሳለ … በመጨረሻ ልታረቃት ወሰንኩ… አለችው ብዙነሽ የቡናውን ስኒ ማስቀመጫው ላይ እንዳለ አያሸከረከረች፡፡
ታዲዎ ብዙ ጊዜ ስለአብሮ አደግ ጎደኛዋ አጫውታዋለች፡፡ ስለ አስቴር አውርታ አትጠግብም፡፡ ነገር ገን ሁሉት ዓመት ሜሎ ልደታ ላይ እንድትገኝ ስትጠራት ወሳኔዋ ቁጥር ነበር፡፡ በአስቴር የልደት ቀን ግን ብዙነሽ ስታለቅስ ነው ያሳለፈችው፡፡ የዘንድሮውን ግን ልትሄድ ወሰናለች፡፡ የስጦታ ዕቃዎ አዘጋጅታላታለች፡፡
…ግሩም ነው… …በዛሬ ታላቃ ቀን ገን እኔም ብገኝ ምንኛ ደስ ባለኝ እነዚያ ጅቦች አስችኳይ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡… አለና ሲና ደድ እንደያደርገው እጅን አወናጨፈ ‹ጅቾች› የሚላቸው አለቆቹን ነው፡፡
…በታክሲ ልሄድነው እንዴ ታዲያ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ነውኮ ጥሪው?... አፈጠጠችበት
የገንዘብ ቦርሳውን አወጥቶሄሳቡን ጠረጴዛው ላይ ካኖረ በኋላ ከመቀመጫው እየተነሳ …አንቺ መ/ቤት ታደርሺኝና መኪናዋን ይዘሽ ትሄዳለሽ፡፡ አላት ትከሻዋ ላይ እጁን ጣል አድርጎጎ፡
…ዛሬ እንኳን መሪ ባልይዝ ይሻል ነበር፡፡ ቸግር ከሆነ ግን ምን ይደረግ፡፡… በማለት የመኪናወውን ቁልፍ ተቀበላ በሹፊሩ መግቢ በኩል ገብታ ለሱም በሩን ከፍተችለት፡፡
መ/ቤቱ አድርሳው ቶሎ ከጨረሰ ከቤቷ እንዲጠብቃት ከነገረችው በኋላ …መተኪያ… ለምትለው ውሻዋ የአሁድ ቀለቡን ከተኮናተረችለት ቦታ በመያዝ ውሻዋን ለማየትና ከዚያም ልብስ ለመቀየር ወደ ቤቷ ከነፈች፡፡
ቤቷ በር ላይ ደርሳ መኪናዋን እንደቆመች የተሰበሰቡት ሰዎ ሲጠቃቀሱባት አስተውላ ነበር እንዳለ ገባት፡፡ ሁለት ፖሊሶች ወደ እሷ ተጠግታው ሰላምታ ሰጥተዋት ለምርመራ እንደሚልጓት ነገረው ፖሊስ ጣቢ ወሰዷት፡፡ ለጥያቄ ስምንት ሰዓት የሄደች …ስልክ እንኳን ልደውል፡፡… እባካችሁ አድራሻዬን እንኳ ለዘመድ ንገሩል …እያለች ብትወተወትም ለጥያቄዋ መልስ ያገኝቸውና በዋሰ የተፈታቸው ከጠዋቱ በሦስት ነው፡፡ የታሰረችበት ምክንያት ያትም ውሻዋ …መተኪያ… ኳስ ሊያወጣ በአጥር ዘሎ ግቢዋ የገባውን የጎረቤት ጎረምሳ ስለነከሰ ነበር፡፡ቀን የጠፋን በሬና የሚሰርቅ ሌባን ያገናኛል፡፡.. እንዲሉ፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?
ህይወት ክፍል 11
የሰው ልጅ በኖረባቸው ብዙ ሺኅ ዓመታት በተፈጥሮ ያደረገው ዝግመታዊ ለውጥና ከተፈጥሮ ጋር ባደረገው ፍጥጫ የደረሰባቸው የቴክኖሎጂ ውጪቶች የሚያስደንቁን ቢንም እንዳንድ ጊዜ ገን ግራ እያጋቡን ይጋኛሉ፡፡
ከቻርሊስ ዳር ዊን ቴዎሪ ተነስተን የሰውን ልጅ በራሱ ላይ በተፈጥሮ ክስተቶች በመታገዝ ያደረገውን ዝግመት ለውጥ ሰናይ በማህበረሰብ በመሰባሰበብ ያሳለፈውን ህይወትና የማህበረሰቡን የዕድገት ደረጃ እንደናጢን መገደዳችን አሌ አይባልም፡፡
በኢትዮጵያችን እንኳ ባሪያ መሸጥ መለወጥ እንዲቆም በአዋጅ ደረጃ /በተገበር ላይ ከአዋጁ በኋላም ቆቶ ተሰተዋሏልና፡፡/ በአፄ ሚኒሊክ ጊዜ ነው የተደረገገው፡፡ /ይህ የባሪያ ፍንግሌ ግን በዘመናዊ መልክ ቀጥሎ የመኖር እስትንፋሱ በተወሰነ ደረጃ ቀይሮ ባሪያ የነበረው ሠራተኛ ተሰጥቶ ይገኛል፡፡/ እዚህ ላይ አማረኛ ቋንቋ ስሚችግረኝ ለቃላት አጠቃቀሜ እንባቢን ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡/
በቴክኖሎጂና ብሔራዊ ሀብት መጠን በልፀገዋል በሚባሉት ሀገሮች ሁሉ የባሪያ ፍንግሌ /ያላችሁትን በሉኝ እንጂ/ እንደቀጠለ ነው ያለው፡፡ እዚህ ላይ ምሳሌ ብጠቅስ ሃሳቤን ግልፅ ያደርገዋልና እንካችሁ፡፡
ለሞኑን የዓለም ዋንጫ እተካሄደ ነው፡፡ እኔ እንኳን ጥሩ የእግር ኳስ ጥበብ ለማየት ብቻ ሰምቼ እያለሁ እንጂ በቀን በቀን የአንቀጽ ልፍ ሰዓቱን እንዲሻብብቅ አልፈልግም፡፡ ወደ ቁም ነገሩ ልግባና የአንዱ ክለብ የእግር ኳስ ጨዋታ ሙያጠኛ /ፐሮፌሽናል የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃለ ከተካልኝ/ በኮንስትራት ለተወሰነ ዓመት ከተሸጠበት ክለብ ወደ ሌላ ክለብ ተመልሶ ሲሸጥ ይሰተዋላል፡፡ ተጫዋቹም ይ ብዙ አያሳስባውም፡፡ ገንዘብ እስከተከፈለው ድረስ የሚሸጠው ክለብ አተረፈበት አላተረፈበትም፣ ለብዕናው ወደ ሸቀጥነት /ዘመና ባሪያነት/ መለወጡ ደንታዎ አይሰጠው፡፡ እንግዲህ ይህ ሁኔታ ህይወትን በማቆየት ውሳኜ ደረጃ ይለያይ እንጂ ከጥንቁ የባሪያ ፍንገላ በምን ይለይ? ያ የተሸጠ ተጨዋች ደገሞ ጨዋታው ከተቀነሰ ምንም ያህል ለክለቡ ውለታ የዋለ ቢሆን እንደ አሮጌ ቆርቆሮ መጣሉ አይቀሬ ነው፡፡ እርገትጥ በቁሳዊ ጥሪት መያዙና የባንክ ደብተሩ ላይ ቁጥሮች መነበባቸው ከሥጋዊ ምቾት ትንሽ ይጠቀመው ይሆናል፡፡ ነገር ገን ለሞራል ጎዳቱና ለህሊናዊ ጥያቄ ምን መልስ ይገኝለታል?
ሃሳቤን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ አንድ ሌላ ምሳሌ ልጨምር፡፡ አኔሁ በለፀጉ የሚባሉ አገሮች ብዙ የተማረ ኃይል እንዳላቸው ይነገራል፡፡ የተማረውን ኃይል እንዴት አፈሩት ብንል ገን የሚኖረን መልስ በየሀገሩ ጥሩ ጭንቅላት ያለውን ምሁርን በተለያየ ዘዴ በማስኮብለል እያስቀሩት መሆኑን ደግሞ የተደበቀ ሁኔታ አለመሆኑን እንረዳለን፡፡
አነኝህ ምሁራን የሚኩበልሉበት ምክንያት ቢለያይም ከሀገር ወጪሄደው ቢሮሩ ገን በቁጭት እየተብሰለሰሉ አወዳደቃቸው እንደማያምር ይደመጣል፡፡ የቤተሰብ ናፍቆት፣ የሀገር ውበትና አየር፣ የደርጉበት ሰፈርና ጎደኖች፣ የተማሩበት ት/ቤና የልጅነት ፍቅረ በሃሳባቸው እየተመላለሰ ጤና እንደሚነሳቸው ከኖረበት ክ/ሀገር ወደ ሌላ በሥራም ሆነ በዕረፍት ለሄደ ሰው የሚረስ ነገር ስሆነ አዚህ ላይ ብዙ ማለት የሚስፈልግ አይመስለኝምም፡ አስገዳጅ ሁኔታዎችም እንደሚኖሩ አልዘነጋውም፡፡ ነገር ገን ለሰው ልጅ መብት ተከራካሪዎች ነን እያ በየመገናኘው ብዙሃን ባሸበረቁ ቃላቶች ዲማጉጋቸውን የሚለፍፉ ሀገሮች ከአንድ ወቅተ ጀምረው በሚያወግዙበት አፈቸው በየጊዜው በሚፈጠሩት ገደብ የለሽ ምንክያቶቻቸው በማደግ ላይ ያሉ አገሮን ምርት ዜጎች እየሸበቡ በዘማነው ባርነት ማድከማቸውና መጠፈራቸው የጥንተ ባርነት መልኩን ለውጦ እስከ ዘመናችን ድረሰ አልዘለቀም ለማለት የምንደፍር ሰንቶቻችን ነን? በአሜሪካ የጠፈር ምርምር ማዕከል ሆነ የመክላከያ ኃይል ተቋም በእውቀታቸው ተከብረው የሚሰሩ ምሁራን በራሳቸው ፍላጎት መልቀቅ ቢፈልጉ የመኖራቸው ዋስትና አደጋ ላይ መውደቁን ማሰብ ራሰ ጥንት በባርነት ከማቀቁ ሰዎች ልዩነቱ ምን ያህል የሰፋ ነው?
ከላይ ለመጠቃቀስ የሞከርኩት የሰው ልጅ ተፈጥሮን ለመለወጥ ባደረገው ትግል ብዙ ቢሳካለትም በራሱ የአስተሳሰብ አድማስ ነው ያደርገው ለውጥ ግን ሰው ሆኖ ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙም ፈቅ አላለም ለማለት ነው፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?
አስፈሪው ሌሊት
ሌሊቱ ረጭ ብሏል ምንም ኮሽጻ አይሰማም፡፡ እጄን ለማንቀሳቀሰ አንኳን አልደፍርም፡፡ ፀጥታውን ላለማደፍረሰ ፈርቼ፡፡ ከእንቅልፌ ምን እንደ ቀሰቀሰኝ አላውቅም ብቻ ነቅቻለሁ፡፡ በጀርባዬ እንደተጋለልኩ ጨለማውን ልክ እንደ ቆንጆ ገን አስፈሪ ሙዚቃ ማዳመጥ ጀመርኩ፡፡
ለትንሽ ጊዜ በኋላ በሩ ኳ ኳ ያለ መሰለኝ፡፡ አቤት ውስጥ ሌላ ሰው ቢኖር እንኳን እሱ ይሆናል የሚል መረጋገያ ይኖረኝ ነበር፡፡ ነገር ገን ብቻዬን ነኝ፡፡ ደንገጥ በማለት ተንፍሼን ወጥ አርጌ ያዝኩ፡፡ ቆየት ብሎ ደግሞ መስኮቱ ኳ ኳ ይላል፡፡ ሌባ በሩ በቀላሉ ስለማይከፈት መስኮቱን እየሞከረ ሳይሆን አልቀረም፡፡ እንዱያውም የኔ መስኮት ገፋጋፋ ሲደረግ ቶሎ የከፈታል፡፡ ይሄንን የሚያውቅ ውስጥ አዋቂ ሌባ ነው፡፡ በሩን የሚንኳኳውም እንደተኛሁ ለማረጋገጥ ይሆናል፡፡ ስለዚህ መበጨረሳን ልይ በማለት ካለሁበት አልተነቃነቅሁም፡፡ በተኛሁበት ሁኜም እስቲ አሁን ወንደላጤ ቤት ምን ይገኛል ብሎ ነው ያውም እኔ ቤት ያለችኝ ብርቄ ሬዲዮ ነች፡፡ በተረፈ የአዘቦ ቀን ልብስ ነው፡፡ ውስጥ አዋቂ ቢሆን ለአንድ ሬዲዮ ብሎ ሌሊት ቤት ሰብሮ አይገባምም፡ ከሩቅ አካባቢ የመጣ ይናልል፡ አያልኩ ሳስብ አንድ የሰማሁ ቀልድ ትዝ አለኝ፡፡
በከተማው አደጋኛ ዘራፊ ሰው አያገደለ የሚዘርፍ መጥቷል ተብሎ ተወርቷል፡፡ አንድ ባለሱቅ ነጋዴ ሱቁን ዘጋግቶ ሲያሸልብ የሱቁ መስኮት በመንኳኳት ይባንናል፡፡ ማን ነህ ብሎ ሲጠይቅ እኔ እከሌ ዘራፊው ነኝ ክፈት የሚል መልስ ያገኛልል፡ ይሄኔ ባለሱቁ የለሁም ሰብረህ ግባ! ብሎ መለሰለት አሉ፡፡
የኔ ነገር ቤቴን ሰርስሮ የሚገባ ሌላ ቤቴ ደጃፍ ላይ ሲንደፋደፍ የሰማሁን ቀልድ አስታውሳለሁ፡፡ የራሱ ሁኔታ ቢገርመኝም የመስቴ መንኳኳት ወድ አሁኑ መለሰኝ፡፡ እንዴ አረ ብዙ ናቸው መሰለኝ፡፡ ሹክሹክታ ነገር ይሰማኛል፡፡ ሸፍቶችስ ቢሆኑ መሳሪነገር ሳይዙ መቼም አይመጡ፡፡ ገን እኔ ቤት ምን ሲያደርጉ ይመጣሉ? እኔ ለራሴ አንድ ተራ ሠራተኛ ከሃብት ሃብት የለኝ፡፡ /ከንብረት ንብረት/ ከሥልጣን፡፡ አበው አይመጣምን ትተሸ ይመጣል አስሰቢ ይላሉ፡፡ ሲተርቱ ለማንኛውም ያቺን እንደ ዱላም እንደ ጩቤም የምታገለግለዋን የት አርጌያት ይሆን? አዎ የራስጌዬ ኮሞዲና ውስጥ፡፡
ቀስ ብዬ ከአልጋዬ ወርጄ ያችን ዱላ በመያዝ በባዶ እግሮቼ ጣቶች እየረገጥኩ ድምፅ ሰላሰማ የመኝታ ቤቴን በር ከፍቼ ሳሎን ገባሁ፡፡ እስካሁን ከመስኮቱ ጋር እየታገሉ ነው፡፡ ግድግዳ ሥር ጆሮዬን አስጠግቼ ሳዳምጥ ምንም ሹክሹክታ የለም፡፡ እንግዲህ ሌሎች ሄደዋል ማለት ነው ለብቻው ደሞ ከመስኮቱ ጋር የሚታገለው ደህና መሳሪ ስለያዘ በራሱ ተማምኖ ይሆናል፡፡ እሱም አንድ፣ እኔም አንድ፡፡ መትረየስ እንኳን ቢይዝ አይዝም እንጂ እኔ ቆንጆ ጬቤ አለኝ፡፡ አንገቱን ላይ እሸቀሸቅለታለሁሁ፡ እሱ መስኮቱን ከፍቶ ከገባ በኃለ መብራት አብርቶ መኝታ ከፍል ሰው ካ ድምፅ በማያሰማ ሹጉጥ ገድሎ ንብረት ዘርፈ ለመሄድ ነው የሚያስበው፡፡ ያውም እንቅል ጭልጭ እድርጎ የወሰደው ሰው ስለዚህ ይዘናጋል፡፡ እኔ ደግሞ ከቆንጆ እንቅልፍ ላይ የቀሰቀሰኝ ዘራፊ ሌባን መጨረሻውን በዓይኔ በመመስከር ለቅርስነት በተገባቸው ጩቤ ለኔ ባለድልነት መድቦታል፡፡ አድሉ ሳያደርግ አልቀረም፡፡ የሰማዩን ንጉስ ለተጠቂ አይደል የሚያዳላው፡፡
የመስኮቱ መንኳኳት እየበረታ መጣ፡፡ የቆምኩበት እግሬም ወለሉ ላይ የተነጠፈው ቅዝቃዜ እየተሰማኝ በሃሳቤ መቁነጥነጥ እበዛሁ፡፡ ፍርሃቴ እየጨመረ ሄደ፡፡ እስከዛሬ ድረስ ሰው ገድዬ አላውቅም፡፡ የገደል ሰው በህግ ፊት ይቆማል፡፡ ለኔስ ገድያ ስቅላት ይፈረድብ ይሆን? ሌባ ስለገደልኩ አያደርጉትም፡፡ ባይሆን ይሸልሙኛል፡፡ ከምድራችን ላይ አንድ የሰላም ህይወት ቀበኛ አጠፋሁ ማለት አይደል እንዴ? ግን ሌባው ጁዶ ቢችልስ? ይሄ መቼም ትልቅ አደጋ ነው፡፡ የጩቤውን ነገር ትቼ ብጮህ ይሻላል፡፡ የሰው ያለህ አረ ኡ በል ይሻላል፡፡ አይ ከዚህ ሌባ፣ ሌባ፣ ሌባ ያዙ ኡ … ማለት ይቀላል፡፡ ለምን ጎረቤቴን ጩቤዴን በጋሮ በኩል ተጠርቼ አልቀሰቅሰውም? ለዚህ ሁሉ አያፈጫሁ መብራቱን አብርቴ ጫማ ካደረኩ በኋላ ንፋስ እንደሚልግ ሰው በሩን ከፍቼ ወደ ወጪአልወጣም? ሌባውም ጋና መብራት ሲበራ ተነቃበኝ ብሎ እግሬ አውጬኝ ማለቱ አይቀርም፡፡ ከበፊቶቹ ዘዴዎች ሁሉ ይሄኛው ይመረጣል፡፡ ሎሎች ዘዴዎች በጎረቤቶቼ ያሳጡል፡፡ በሃሳቤ ካወጣሁ ካወረድኩ በኋላ በፍርሃት ለሣሎኑንም መብራት በግ አድርጌ ፍርሃቴን ለመሸፈን አያፋጨሁ በሩን ከፈት ሳደርግ ድምፅ በሌላው መሣሪያ የተወረወረ ነገር ለግንባሬ ታልሞ ዥው ብሎ ሲምዘገዘግ በድንጋጤ ጎንበስ ስል ከግድግዳው ጋር ተጋጭቶ መሬት ወደቀ፡፡ ድንጋጤው በረድ ሲል የተወረወረብኝን ነገር መልክት ሳደርገው አብድ የወረወረው ድንጋይ የሚያክል ጥቁር ጢንዚዛ ነበር፡፡
በእውነት
የ14ኛውን የዓለም ዋንጫ ብራዚልና ስዊድን ሲጫወቱ ለማየት አስቤያለሁ፡፡ የእግር ኳስ ስሜቴ ብዙም አይገፍኝ፡፡ እንዲያው በኳስ አርዕስት ጓደኞቼ ሲያወሩ የበይ ተመልካች ዓይነት እንዳልሆን ብዬ ነው፡፡ ሰዓቴን መልከት ሳረግ አንድ ሰዓት ከሩብ ትላላች፡፡ የእሁድ ማታ አንድ ሰዓት ከሩብ በአሰላ ከተማ፡፡ ለምን ሲኒማ አልገባም በማለት ቲኬት ቆርጬ ዘው አልኩ፡፡
ፊልሙ የቻይና ካራቴ ኩምክና ስነ ነበር እልፎ አልፎ ፈገግ እያደረገኝ ምስራቅ ትዝ እለችኝ፡፡ ዛሬ ማታ 12 ሰዓት አካበባቢ አግኝቻት ሰላም ተባብለን ዛሬን እንኳን እንድትቆይ ሰጋባባት ነገ ሥራ መግባት አለብኝ ብላ ድርቅ አለች፡፡ ሥር ከገባች ያገኝኋት ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ነበረ የምስራች አልኳት ምስር ብላ በማለት እንደገና ተሳሳምን፡፡ ሠራተኛም ስለሆንሽ የምስራቹን እናክብራው ብዬ ሃሳብ ባቀርብም የማይሆን ሆነ፡፡
ምስራቅ የቀይ ዳማ የምትባል፣ ቀመቷ ዘለግና ፈርጠም ያለ፣ ፈገግ ስትል በውሃ የበለዙ ጥርሶቿ ገሃድ፣ ቢወጡም ውበቷን የማያጠፋበት ጎበል ነች፡፡ ከተዋወቅን አንድ ዓመት ቢያልፈንም ያለንበት የመኖሪያ ርቀት እንደልባችን ተገናኝተን እንድንጫወት አላስቻለንም፡፡ በተገናኝንባቸው ሰዓታት ግን የልብ ለልብ የተግባባን ሆነናል፡፡ ወሬ አጥተን ሳንደባበር 4 ሰዓት 5 ሰዓት ተጫውተናል፡፡ ያለችበት ከተማ ስሄድም ሆቴል አሲዛኝ ስንጫወት አምሽተን ወደ ቤት ሸኝጫት ከመመለስ በቀር በፍቅር ጉዳይ ገና ነን፡፡ ቢሆንም መንፈሱ እንዳለ ሁለታችንም እናውቀዋለን፡፡ እንዲያው በደፈናው በጣም ጥሩ ጓደኛሞች ለመባል ችለናል፡፡
ዛሬ ታዲያ በአጋጣሚ ነበር እሷማ ጓደኛዋ ዘመዶች ጋር ከጓደኛዋ ጋር መጥታ፣ እኔም የሦስት ቀን ፈቃዴን ጫረሼ ወደ ምሠራበት ቦታ ለመሄድ መንገድ ሳድር የተገናኝ ነው፡፡ ዛሬን እደሪ እቤት ደውለሽ ብላትም የስራውን ሁኔታ ጠቅላ አልበነር ያለቸውና ወደና ሁን ጎደኛህን ሰላም በልልኝ ብላ የተሰናበተቸኝ፡፡
ፊልሙ ሲያበቃ ነው እኔም ከሃሳቤ የባነንኩት፡፡ ሆዴንም ስለሞረሞረኝ የምግብ ፍላጎትም ባይኖረኝ ቀማምሼ ቴሌቪዥን ለመከታተል ጎራ አልኩ፡፡ ባጋጣሚ የቴሌቪዥን የሰሞኑ ተመልካቸው ብዙ ስለ ነበር ክፍሏ ደግሞ ጠባብ ስለ ነበረች እንግዳ መቀበያው በር አካባቢ ወንበሮች ተደርድረዋል፡፡ ቴሌቪዥኑ ከቡና ቤቱ በር ላይ ደረጃው ሥር ከፍ ያለ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጧል፡፡ እንዳንድ ተመልካቶች ድምጽቸውን ዝጥ አርገው ይንሾካሾካሉ፡፡ የበረንዳው እንጨት አጠገብ አንድ ባዶአግዳሚ ስለ ነበር ሄጄ በመቀመጥ የእግር ኳስ ጨዋታውን መጠበበቅ ጀመርኩ፡፡ የሰሞኑን ጨዋታዎች በተመለከተ እንዳንድ ዜናዎች ይቀርቡ ነበር፡፡ የስፖርት ዜናው አልቆ በጣም የተጠበቀው የብረዚልና የስዊድን ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ዩናይትድ ስቴቴስ በቼከዝላቪኪያ 5 ለ 1፣ ሶብየጥ ህብረት በሩማኒያ 2 ለ0፣ መሸነፈቸው እዛ የተቀመጠውን ተመልካች ያነጋግረው ጀመር፡፡
ልክ 4፡00 ሠዓት ላይ ነበር/በኔ ሰዓት/ ዳኞች ወደ ሜዳው የገቡት፣ ተመልካቹንም ረጭ በላ ፀጥታ፣ ከቴሌቪዥኑም ኋላ ካለው ቡና ቤት እንዲት ገብል በመቅደም ጓደኛዋም ከኋላዋ በመከተል ወደ መኝታ ክፍሎች ሲያመሩ በዓይኔ በብረቱ የተመለከተኩት፡፡ ልጅቷ ምስራቅ ያልኳችሁ ለነገ ሥራ መድረስ ስለምፈልግ አላድርም ያለችኝ ናት፡፡ በዛው ደቂቃ ብዙ ነገሮች ተመላለሱብኝ፡፡ ካልም ዳውን የሚል የዶ/ር ፓልን መፍሐፍ ያነበብኩት በቅርብ ስለ ነበር ቁጣን ማስወገድ አይቻልም ማቀዝዝ እንጂ በሚለው ርዕስ ስር ንዴቱን ስላመጣው ነገር ረጋ ብሎ ማሰብ ይረዳል የሚለውን ሃሳብ አስታውሼ ውስጤ ግን እየጨሰና እየተኮማተረ አንድ ሌላ ብኩን ቤት አልኩ በሆዴ፡፡ ለነገሩ ግን ሸወደችኝ፡፡ በእውነት ሸወደችኝ፡፡
ተመልካቶች ኡስስ …!
ነገር በምሳሌ ያስተማሩን አበው ምስጋና ይድረሳቸውና ዝምታ ወርቅ ነው ይሉ ነበር፡፡ በምክንያት አውሮፓውያንም መቼ ዝም ማለት እንዳለበት የሚያውቅ ሰው ጅል አይደለም የሚል አባባል አላቸው፡፡ የአበውን ብሂል ሲያጠነክሩት፡፡ ለነገሩ አልኩ እንጂ ሃሳብን መግለጽ ከተፈለገ ዝምታም የሚገባው ካገኝ ይናገር የለ፡፡ ለዚህም ነበር ግርማ በጋሻው በቅጽ 2 ቁ 2 1980 መድረካችን እትም …ዝም ቃል… በሚል ርዕስ ሥር
‹… ያሸኝን ብላችሁ ያሰበኩትን ሁሉ፣
የዝምታው ዘዬ ባይሰማም ቃሉ፡፡
የሰሙ ሰምተዋል አውግተዋል ከኔ፣
በከንፈር እድምታ በሙት ምላሽ ቅኔ፡፡
ዝም ብዬ ዝም ብል ዝም ብሏል አትበሉ
የዝምታው ዘዬ ሲጠፈቸው ውሎ፡፡ …›
በማለት ያስፈሩት፡፡ ሺ ጉዜ ቢነግረውም የማይገባው እንዳለ ሁሉ ለማወቅ ለፈጠነ ግን ዝምታም ብዙ ይናገራል፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋል ሆኖ ነው እንጂ የጽሑፍ መነሻ በየአጋጣሚ የምሰማው ያለቦታቸው የሚነገሩ ንግግሮች ናቸው፡፡
እዚህም እዚያም የቼዝ ውድድር ይደረጋል፡፡ በየሁለት ተፎካካሪዎች መሐል፡፡ ተመልካቶችም ከሰው ይመለከታሉ፡፡ ተወዳዳሪዎቹ ክንዳቸውን ጠረጴዛ ላይ ስደግፈው ግንባራቸውን እያሹ ያስባሉ፡፡ አልፎ አልፎ ሌባ ጣታቸውን ከንፈራቸው ላይ ጣል በማድረግ በየት ልሄድ በሚል ዓይነት ቅኝት የቼዝ /ሠንጠረዡን/ ይቃኛሉ፡፡ አስበውና ተጨንቀው ይሄዳሉ፡፡ በዚህን ጊዜ እንዳንዱ ተመልካች መቅበጥበጥ ይጀምራል፡፡ ጨዋታው ቀጥሎ ቅብጥብጡ ተመልካች ያስበውን ዓይነት መንገድ ተጫዋቹ ሲሄድ አዎን አየህ ገና ከቅደም የነበረው ዕድል ይሄው ነው፡፡ በሚቀጥለው አፈካሄድም ቼክ ኤንድ ቼዝ /ንጉሱና ንግስቲቷን በቁጥጥር ሥር/ ትለዋለህ፡፡ ወይም አየህ በዚህ አካሄድህ ንግስቲቷን ብታጣ መሸሸጊያ ገዳሙን አታጣውም ይለዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ተጫዋቹ ይሄኛውን አላየሁትም ነበር፡፡ ሲለው ሁለተኛው ተጫዋች ምን እንደ ሚሰማው መገመት አያስቸግርም፡፡ የቼክ ጨዋታ ግን እንኳን ከተመልካች ከባለጋራም ተጫዋች ንግግር የሚጠበቅበት አልነበረም፡፡ ስለዚህ ተመልካቶች እባካችሁ ፀጥታ!
በሰው የተመላቸውም አረንጓዴዋ የካራምቡላ ስታዲየም ውስጥም የሚኖረው ጫጫታ እንኳን ተጫዋቹን ጊዜ ለማሳለፍ የመጣውንም የካራምቡላ አፍቃሪ ውጣና ብረር የሚያሰኝ ነው፡፡ የሚወቱት ማሰብ እስኪሳናቸው ድረስ በዚህ በኩል ብትሄድ ባሊናን /በካራምቡላው ጨዋታ ተፈላጊዋን ኳስ/ ታገኛታለህ፣ እኔ ብሆን አተራምሰው ነበር፣ በሜዛ ስፖንዳ /በግማሽ የመጫወቸው ወለል/ ቅረባት፣ ደርሶ መልስ ሂድ የማይሰጥ ምክር የለም ክፋቱ የሁሉም በአንድ ጊዜ ስሚወጣ ጫጫታው አያድርስ ነው ተጫዋቹ ኳሶቹ ባያንሱት እዛ ቆሞ እንዲህ አርግ፣ እንደዚያ አርግ በሚሉት አስተኳሾች /መካሪዎች/ እሱ ምንም ማሰብ እንደማይችል በነሱ ጭንቅላት የመመራ ሮቦት ማድረጋቸው ሲያቃጥለው ኳሱን እነሱ ከመከሩት አቅጣጫ በተቃራኒው ወርውሮ እምቢ ማለቱን በዝምታው ዘየው ይገለጻል፡፡ ዳሩ ማን የሚገባው ተገኝቶ ጭራሽ እንዲህ ብታደርገው ኖሮ ብው ኳስ ይዘው ወርውረው ሊያሳዩ የሚቃጡም አይጠፉም፡፡ /በሰው ሰዓት!/ የከተማው አካባቢ የካራምቡላ ጨዋታ በእረጋታና በፀጥታ የሚከናወን ሲሆን አልፎ አልፎ በጓደኛማች መካከል መረን ያልለቀቀ የቀልጆች ምልልስ ይሰማሉ፡፡ ምነዋ ታዲያ የኛ ካራምቡላ አፍቃሪዎች እንደማይሆን ሆኑ?
ፊልም እየታየ ነው፡፡ ብዙ ሰው ተቀምጦ ይከታተላል፡፡ ትንሽ ፈገግ የሚያደር፣ ወይ የሚያስቅ ነው ከተሰማ አምስት ደቂቃ ሙሉ ሆዱን ይዞ በሚያስገመግም ድምጽ ይሰቃል እንዳንዱ፡፡ ይሄኔ ተመልካች አጨብቦለት ከዛ ፊልሙም ብቀጥል ጥሩ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ፊልሙን ታሪ በእርካታ መከታተል እንዲቻል፡፡ ሌላው ደግሞ አለ፡፡ ፊልም ይእ የታየ ከጓደኛው ጋር የቤቱን ወግ የሚርቅ ነገር ግን ገንዘብና ጊዜውን ክፍሎ የመጣው ፊልም ለመመልከት ነው ሁኔታው መልኩን ቀይሮ አስር ደቂቃ ፊልሙን መከታተል ሳይችል ቀርቶ እንደገናም በአካባቢው የተቀመጡትንም ሰዎች ፀጥታ ነስቷቸው ይቆያል፡፡ ፊልም ለመመልከት የመጣ ሰው በፀጥታ ተከታትሎ እንዲሄድ ፊልም ቦታ የማውራት ልምድ ያላቸው ሰዎች ለፊልም ሠዓት እንኳን ቢታቀቡ የሞራል ግዴታቸውን እንደልምድ ያላቸው ሰዎች ለፊልም በሰዓት እንኳን ቢታቀቡ የሞል ግዴታቸውን እንደተወጡ ይቆራልና በየአጋጣሚው እባካቸሁ ሊባሊ ይገባል፡፡
ምሳ ከተባለ በኋላ ሻይ ቡና ሲባል የ6፡30 ዜና ይደመጣል፡፡ ከጉናችሁ ወንበር ሰላጣ የጠቀመጠ ወይ ግሩም ብሎ እዛው እብራችሁ የሰማችሁን ዜና ይደግምላችሁል፡፡ እሱ ያንሱ ዜና ሲደግምላችሁ ሌላ ዜና አልፋችኋል፡፡ ለነገሩ ዜና መደጋገሙ ስለማይቀር በማታው እዳምጠዋለሁ ብለው ይጽናናሉ ቢሆንም ግን ከጎናችሁ የተቀመጠውን ‹የማነው ችኮ› ማለታችሁ አይቀርም፡፡ በልባችሁ፡፡
እስካሁን ማለት የፈለኩት ሳይገባችሁ የቀረ አይስለኝም፡፡ ያላገባችሁ ካላችሁ ግን ዝም ብያለሁና በዝምታዬ ልተረዱኝ ሞክሩሩ፡
ያልተወራረደ ፍቅር
የመጋቢት ወር አየር በአካባቢ ለጤና ተስማሚ ቢሆንም ሄኖክ እንደ ደበተው ነው፡፡ ከወሩ ጋር የመጡትን የተለያዩ ወፎች ባገኝው አጋጣሚ ያስተውላል፡፡ ቢሮው ገብቶ ሊያነብ ይልና ሃሳቡ ይበተንበታል፡፡ ጓደኞቹ አጠገብ እያለ ባያውቀው ጭልጥ ይላል፡፡ ሲያወሩትም ያወራል፡፡ ግን አይጥመውም፡፡ ምግብም ቢበላ አቀርቅሮ ማሰብ ሆኗል ሥራው፡፡ ማሰብ ብቻ ሌላው ሁሉ ነገር ለሱ ደንታ የሚሰጠው አልሆን ብሏል፡፡ ለሴት ልጅ አዲስ አይደለም፡፡ በትምህርት ቤት ብዙ ኮረዶች ቢጠጉ የወሬ አርእስታቸውም ስለማይጥመው፣ ደደቦች ናቸው ስለሚልና ስለሚንቃቸው ብዙም አያናሰግራቸውም፡፡ ለዚህ ነበር ኮረኮች ‹አውሬው› ብለው ቅፅል ስም ያወጡለት፡፡ ያሁኑ ግን ሁለመናውን መስጧዋለች፡፡
ፀሐይዋ ወደ ምዕራብ አድማስ እየተጠጋች ነው፡፡ ሙቀቷን ለዘብ አድጋው ብርሃኗን ግን ደመቅ አርጋ ለቃዋለች፡፡ የዛፎች ቅጠሎች ሊከልሏ ቢልጉም ባገኝችው ቀዳዳ አለሁ ከማለት ወደኋላ አላለችም፡፡ ሄኖክም ለአካባቢው አዲስ ስለነበረ ከጓደኞቹ ጋር ተፈጥሮንእያደነቀ ያዘግማሉ፡፡ የደኑ ጥቅማጥቅ ማለትና ፀጥታማ መሆን የአውሬ መኖሪያነቱን ያበስራል፡፡ ከወደታች በኩል ጫጫታ ሰምታው ወደዛውአመሩ፡፡ አንድ በድልድይ ሥር በሚልፍ ጅረት ሥር ልጆች ይንቦጫረቃሉ፡፡ ከተራራ ላይ መጥቶ ድልድይ ጋር ሲደርስ ጥልቀት ያለው ኩሬ ስላላ እዛ ከገባ በኋላ እንደገና ድልድዩን አልፎ ይፈሳል፡፡ እንዳንድ ልጆች ድልድዩ ላይ በመቆም ወደ ኩሬው ይዘላሉሉ፡ ትንሽ ከተንቧቹ በኋላ ተመልሰው በመውጣት እንደገና ለመውርወር ይዘጋጃሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ነበር ሄኖክን የመሰጠው ነገር ያገኝው፡፡ ልጆቼ የሚዋቹበት ኩሬ ውስጥ በሁለት የተጠላለፈ ዛፎች መሃል በተኩላዋች እንደ ተከበበች የበግ ግልገል ዓይን ወዲያ ወዲያ እየተንከራተቱ ወገቧ ድረስ ውሃ ውስጥ የጠለቀችና እጇን በማጣመር ጡቶቿን ከልላ የቆመች ጉብል ትታያለች፡፡
ውሃው ውስጥ የሚንቧቹት በሙሉ በግምት በ14ና 15 ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወንዶች ሲሆኑ ሴት እሷ ብቻ ነበረች፡፡ አሁን ድግሞ ቱሪስት የመሰሉ ጸጉረልውጥ ወንዶች ልክ እንደ ዱር አውሬ ሲመለከቷት ግራ ተጋብታለች፡፡ አጠገቧ የሚዋኙት ልጆች ውሃ ሲረጫት ለመተላከል እጇን ከጣመረችበት ስታነሳ አትንኩኝ የሚሉት ጡቶቿ ተጋለጡ፡፡ ይሄን ጊዜ ነበር ሄኖክ በኪስ ካሜራውና በልቡ ሰርቆ የቀረፃት፡፡ በፎቶ አነሳስ ችሎታዬ አልተማመንም በሚል ዘይቤውም ሁለት ጊዜ ነው ያነሳት፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር እሷም ጤና የነሳቸው፡፡
ሄኖክ ልጅቷን ካየ በኋላ የራሱ ሁኔታ ስላስደነገጠው ቶሎ ቶሎመራመድ ወዳቆመው መኪናቸው ተንደረደረና መኪናው ውስጥ ገብቶ እንደተቀመጠ የልጅቷ ስዕል በኩሬው ውስጥ እንዳለችና በዛፎቹ መካከል በአእምሮው ይመላለስበት ጀመር፡፡
ሜላት ጠዋት ተነስታ ቁርሷን በልታ ከጨረሰች በኋለ ለአያቷ የድጋፍ ሰልፍ ስላለ ለምሳም እንደማትመለስ ተናግራ ነበር ከአብሮ አደግ ጓደኛዋ ገነት ጋር ተያይዛ የወጣችሁ፡፡ የድጋፍ ሰለፍ እንዳብዎ ምሳ እነገነት ቤት በልተው ለሁለኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና 3 ወር በሙሉ ሲያጠኑ ስለከረሙና የኩሬ ዋናና የተፈጥሮ ንጽህ አየር ስለናፈቃቸው ወደዚህ ኩሬ መጡ፡፡ እንደመጡም ዋና ሲጀምሩ የሰፈሮቻቸው ልጆች እንደፍዎቻኋለን እያሉ ሲያስፈራሯቸው ነገት ጎመን በጤና በማለት ወጥታ ዛፍ ላይ ተቀምጣ ታያለች፡፡ እስቲ አንድ ሰው ይንከኝ በማለት ሜላት ስተዋኝ ብዙ ሰዎች መጡ የሚል ንግግር ስትሰማ ድንብርብሯ ወጥቶ ዋናውን አቁማ አጇን አጣምራ አይኖን እያቁለጨለጨች ፈዛ ቀረች፡፡
ሜላት ከቁመቷ ዘለግ ያለች ተፈጥሮ ባደለቻት ፀጋ ብቻ የምትሮር፣ በአያት አድጋ ሥርዓት የያዘች የ18 ዓመት ጉበል ናት፡፡ በሰውነቷ ቅርፅ ብዙ ወንዶች ቢቀርቧትም እየቀለደች ታልፋቸዋለች፡፡ ጥሩ አቀራረብ ያለው ከሆነም ልክ እንዳመጣጡ ትመልሰዋለች፡፡ እስካሁን ግን ለማንም ያልሰጠች ጉብል ነች፡፡
… ሜላት ፎቶ ግራፍ ሲያነሳሽ ነው፡፡ … አላት ሃምዛ የጎረቤት ልጅ ነው፡፡
ቀና አለች ሃምዛ ወደ ጠቆማት አቅጣጫ፡፡ ሄኖክ ካነሳት በኋላ ጓደኛዋ ብራቮ ሲለው ለጓከኛው ፈገግታ ሲያሳየው የመለከተችው፡፡ ልቧ ስንጥቅ አለ፡፡ ፎቶ የማያቃት ሰው በዛ ሁኔታ ስላነሳት ሳይሆን በሄኖክ ሁኔታ ምክንያት ግን አልገባትም፡፡ በደንብ እየቸው፡፡ ድልድዬን ተሸግሮ ደረቱ ዳር ካለ ድንጋይ ላይ ልብ የሚያጥብ ልጅ ሲያነሳ ተመለከተች፡፡ ልቧ ከቦታው ተነቃነቀ፡፡ …ወየው ዛሬ… አለች፡፡ ሁኔታዎች ሲገርሟት በምትጠቀምበት አማርኛ፡፡ ከኩሬው ውስጥ ቶሎ ብላ ወጥታ ገላዋን አደራርቃ ልብሷን ለባበሰች፡፡ ከነሄኖክ ጋር የነበሩ ወጣቶች ያሳስቋት ጀመር፡፡ ከነሱ ጋር እወራች ብትስቅም ዓይኗ ሄኖክን እየተመለከተ ነበር፡፡
መኪናው አካባቢ ሲደርሱ ለመታሰቢያ በአንድ ላይ ፎቶ ተነስተው ለመሄድ አውቶብሱ ውስጥ መግባት ጀመሩ፡፡ ሄኖክም ለፎቶ ወርዶ ስለ ነበር ከሚሽ ጋር ዓይን ለዓይን ተጋጨ፡፡ ብርክ ያዘው፡፡ መኪናው ውስጥ ከገባ ከት/ቤት ጀምሮ የሚያወቃቸውን ሴቶች አንድ በአንድ ማስታወስ ጀመረ፡፡ ድንጋይ ነህ፡፡ ያሉትም ነበሩ፡፡‹በሽተኛ ነው› ያሉም አልታጡም፡፡ ይሁን ስሜቱን ሲያስብ የተፈጥሮ ምስጢር በማለት ፈገግ አለ፡፡
ትከሻውን ነካ በማድረግ ሄኖክ አለች፡፡ የኩሬዋ ጉበል አውቶብሱ ውስጥ ሆና ብላ ነው ከሱ ኋላ የተቀመጠችው፡፡ እንኳን ለራሱ የፈለገችውን ለጓደኛዋ ያሰበችው ካለ እንኳን በምንም በምንም ብላ ታቀርበዋለች፡፡ ዛሬም ራሴ ለራሴ ካልሆንኩ ብላ ከዚህ ከሄኖክ ጋር እልህ ይዟታል፡፡
ሄኖክም ዞር በማለት ለጥሪዋ መልስ ሰጠ፡፡ ዓይን ዓይኑን እየተመለከተች ያነሳህኝን ፎቶግራፍ ትልክልኛለህ? በማለት ሳቅ እያለች ጠየቀችው፡፡ በሚገባ እንጂ ሄኖክ ነበር የዓይኗን የስበት ኋይል በቋቋም ተስኖት እንደበፊቱ ተቀምጦ ውጪ ውጪውን ማለት ጀመረ
ጥጋበኛ አለች የኩሬዋ ጉብል በሆዷ እልህህን አስጨርስሃለሁ፡፡ በማለት አድራሻዬን ልስጥህ? አለችው፡፡ አልተዋወቅንም መሰለኝ ሄኖክእባላለሁ፡፡ አላት እንደማትለዋው ልቡ ስላወቀ፡፡ ሜላት አለችው የዓይኗን ሽፈል ገርበብ አርጋ፡፡ በደንብ ማውራት ከጀመሩ በኋላ ከሲዳሞ ከመጣን አስር ዓመት አለፈን ህሄናውን ግን ልክ እንደ ተወለድኩበት አካባቢ ነው፡፡ ለወባ ኪኒን ምናምን የምባል ነገር እንኳን አላውቅም… ብካ ዓይን ዓይኑን ታየው ጀመር፡፡ የሷ ዓይን እንደ አዳኝ የሱ ደግሞ እንደታዳኝ መባረር ይዘዋል፡፡
አውሬው የሚል ቅፅል ስም እንዳልወጣለት በሶስትና በአራት ሄዋኖች ተከቦ ምንም የማይመስለው ሄኖክ ዛሬ የዚችን ጉበል ገላዋን ለመዳሰስ ባለው ፍላጎት ሊፈነዳ ደርሷል፡፡ ይህ እንዳይታወቅበት ነበር ዓይኗን ሲሸሽ መግቢያ ያጣው፡፡
…አራት እዚህ አካባቢ ተበልቶ አንድ ሰዓት ላይ እንቅስቃሴ ይጀምራል ተብሎ ሰው ከመኪናው መወረድ ሲጀምር ሄኖክ ያረፈበትን ሆቴል የክፍሎች ቁጥር ነግሯት ወደ ጓደኞቹ ፈጠን ፈጠን እያለ ሄደ፡፡
ምቱ ደመቀ ያለ ነው፡፡ በማዩም ጥረት ያለ፡፡ ለሰስ ያለ ንፋስ ለሜላትና ለገነት የተስማማችውን ያህል ቀስ እያሉ ወደ ቤት ያዘግማሉ፡፡ ከዋክብት ለሰማዩ ግርማ ሞገስን አጎናፅፈውታል፡፡
…አይ ገኒ ምናለበት ላሁን ብቻ ያንን ሄኖክ ብትሆኚልኝ፡፡… ሜላት ነበረች፡፡
…እሱም ይሄን ጊዜ አንቺን ይሆናል የሚስበው፡፡… …እባክሽ አትዋልጇ ገኒ እኔ እኮ ካየሁት ጀምሮ ብክንክን ብያለሁ፡፡
…ልጁም ብክንክን የሚደርግ ነው፡፡ ቢሆንም ገን ቀድመሽ እንዲህ አትሁኚ፡፡…
…ሄኖክ ጥጋበኛ ነገር ይመስለኛል፡፡ እኔም ፍዳውን ላስቆጥረው እችል ነበር ብቻ ጊዜ የለም፡፡ የሚሄዱ ከነገ ወዲያ ነው፡፡…
…ዝምተኛነቱ ደስ ይላል፡፡ በተቀረው ግን ዓይኑ እላይሽ ላይ አይደል እንዴ ሲንከራተት የነበረው፡፡…
…ታዲያ እንዴት ላርግ ትያለሽ አሁን፡፡ የሆቴሉን ስምና ያረፈበትን ከፍል ቁጥር ነግሮኛል፡፡…
የአንቺ እኮ እታረጊውም አይባል ዛሬውኑ ክፍሉ ድረስ ልትሄጂ እኔ አልገባበትም፡፡…
…ጭንቅ ብሎናል ያለውን ይበል እንጂ እሄዳለሁሁ፡ ይልቅ አሁን እቤት ገብተን ለእማማዬ አንቺ ጋር ለፈተና ዝግጅት እንደምናደርግ ነግረናት ከሃምዛ ጋር ሆቴሉ ድረስ ሸኙኝ፡፡
ገነት ጓደኛዋ እንደተያዘች ገመተች ያ ቀልድኛነቷ ያ ፍቅር ማለት ደስታ ነው የምትለው አሁንፍቅር የነፍስ ስቃይ ሆኖባት በመጀመሪያ እይታ መጠመዷ አስፈራት፡፡ ወደ ሰማይ ቀና ስትል ከዋክብት አዚያም ተፈነጣጥቀው ሰማዩን እድምቀው ታዬዋት …የፍቅረኞች ምሽት… አለች በልቧ…
ከሻወሩ በሚወርደው ውሃ ሥር ሁለት ሦስት ጊዜ ቢለቃለቅም ሄኖክ በዕውነቱ ላይ የሚወርደውን ቀዝቃዛ ውሃ አልጠገበውም፡፡ ዝም ብሎ ቆሞ ጀርባውን እንደጠበል ውሃ ያስመታዋል፡፡ የክፍሉ በር ሲመታ ነው፡፡ ከሻወር የወጣውና ፎጣ ያሸረጠው ከዚያም በር ለመክፈት የተጣደፈው፡፡
በሩን ሲከፈት ሜላት በፈገግተ ሄኖክ ይኖራል? አለችው፡፡ አዎን ይግቡና ይጠብቁት ሻወር እየወሰ ነው ግን ማን ለበለው? አለና ጠየቃት በሷው የአነጋገር ዘይቤ ወደ ውስጥ ከዘለቀች በኋላ ፍቅር የራባት አጋዘን በለው ብላ ፀጉሯን መፈታታት ስትጀምር እሱ የክፍሉን በር ቆልፎ ወደ ሻወር ጥልቅ አለ፡፡ በሃሳቡ እንዴት አድርጌ ልሳማት እያለ ሲያስብ በሩ ተከፈቶ ሜላት ገባች፡፡
እንደምን ነሽ? መልዕክቱ ደርሶኛል፡፡ ሰውነቴን እስካደራርቅ ብዬ ነው እኮ የቆሁት አላት ሄኖክ እየቀለደና ከእግር እስከ ራሷ እየተመለከታት፡፡ የዘመኑ የፋብሪካ ውጤት የልብስም ዘር ሆነ የቅባት ዓይነት ሊመለከት አልቻለም ልብሷን አወላልቃ ነበር ዘው ያለቸው፡፡ ፀጉሯን ሲመለከት ተንጨፍሯል፡፡ እውነትም የደጋ አጋዘን ትመስላለች አለ በሃሳቡ፡፡ የውበቷን ነገር ግን ማጣጣም ጀምረ፡፡ ንፁህ ሰውነት የተስተካከለ ቅርፅ ኮራ ያለ ዳሌ፣ ሙትት ያለ እንጀት፣ የረዘመ ሸንጥ … እቤት ሰውነቷ የሚለው ዘፈን ትውስ አለው፡፡
እንደምን ነህ እኔ ደግሞ ብቻህን መሆን የለብህም እኔ እያለሁ ያውም የጠፈጥሮን ውሃ በረከት ለመቀደስ በማለት ነው የመጣሁት እኔም አብሬህ ልቁም ውሃው ሥር? አለችው ዓይነት ዓይኑን እያየች ፈገግ ብላ ድረብ ጥርሷን ይፋ በማድረግ፡፡ የሄኖክም ልብ ፍስስ አለ፡፡ ጥሎበት ድርብ ጥርስ ይወዳል፡፡ ያቺ ቆንፈጆ የሰፈራቸው ልጅ እንኮይም ድርብ ጥርስ ነው የነበራት፡፡ እነ ሄኖክ ልጆች ሆነው ብይ ሲጫወቱ እሷን በመኪና የተለያዩ ሰዎች ሲያደርሷት በነሄኒክ አጠገብ ሲታልፍ ታዲያስ ልጆ በማለት ሄኖክም በኋላ ትጫወታለህ አሁን ና ብላ ይዛው ትሄድ ነው ወደ ቤቷ፡፡ ከዛማ ችኩላት ትበጠዋለች፡፡ እሱን እየበላ ትወደኛለህ?ትለዋለች ራሱን በመነቅነቅ ይመለስላታል፡፡ አይ እንደሱ አይደለም ትልና እላይ ላይ እንዲተኛ አረጋው አቀፍ አድረጋ ከንፈሩን ጭምጭም ታረጋው ነበር፡፡ ቤት ለቀው ላላ ሩቅ ሰፈር ባይገቡ በፊት ፡፡ እሷም ታዲ ገና ከሩቁ ፈገግ ስትል ያ ድርብ ጥርሷ ቢታይ እቤት ሄኖክ ሲወዳት፡፡
ነይ እሺ አላት እጅን በመዘረጋት ሜላትን እጁንይዛ ተጠጋቸው ተጠጋት፣ ቀርበቸው ቀረባት፡፡ የሷ እጅ ደረቱን ትከሻውን፣ የሱም ሽንጥና ዳሌ ዋን ይደባበሱ ገቡቡ፡ የሻወሩ ውሃ እሳያቸው ላይ እየተንቧቸ ትንፋቸውን አልፎ አልፎ ከመቆራረጡ በቀር እምብዛም አልረበሻቸውም፡፡ ዓይናችውአልፎ አልፎ ይገናኝና የተላለፉል፡፡ የሄኖክ እጆች ከጆች ከሸንጧ ወደ ጡቶቿ ቢሸጋገሩ ሜላትትንፋሿን በኃይል ወደ ውስጥ ስባ ቀስ እያለች ተነፈሰች፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በዚህ ሁኔታ ከሳለፋ በኋለ እንደገና ተቀራርቡ አፏን ከፋት ከርጋ በዓይኗ ጠዋበችው፡፡ ሳቅ ብሎ ሳም አራጋት፡፡ እጆቿ በአንገቱ እጆቹ በሸንጧ ዙሪያ ተጠላለፈ፡፡ ሜላት አንድ ጊዜ የታቸኘውን ላ ጊዜ በአንግቱ እጆቹ በሸንጧ ዙሪያ ተጠላለፈ፡፡ ሜላት አንድ ጊዜ የታቸኛውን ላ ጊዜ የላይኛውን ከንፈሩን ትመጠምጠው ገባች፡፡ ሄኖክም ደሙ እየሞዋ ሄደ የመጨረሻው ግለት ላይ ሲደርስ የሻወሩን ቧንቧ ዘግቶ ቀስ ብሎ ከንፋሩን በማላቀቅ እንዲተኙ ከነገሩት በኋላ ሁለት ፎጣ እንጥፋውየመኝታ መብራት እጥፋተው በባኞ ቤቱ የመብራት ሙጋጋን አልጋው ላይ እሱ እሷን እሷ እሱን ይፈልጉ ጀመር፡፡ ከአንድ ሁለት ሶስቴም ወገቡን ሱጥጥ አያረገች በደከመ ደምፅ ሄኖክ፣ ሂኖክ ስትለው አድምጧል፡፡ እርካታውን እሷ ጋር ለመደበል የፍር ከበሮውን በጥሩ ዜማ የደለቀው ግን እሷ ለአራተኛ ጊዜ ወገቡን ስትጨምቀው ነበር፡፡
ሄኖክ እንቅልፉን ይለጥጣል፡፡ ሜላትን ልጅን ያንተርሳት እንጂ የሱ ሰይቋረጥ የሚተነፍሰውን ትንፋሽና ያልቡን ምት በእጇ እየዳበሰች ዓይን ዓይኑን ታየዋለች፡፡ ያለወትሮዋ እንቅልፏን ትታ የምታየው እሱን ነው፡፡ በሃሳቧ ግን ሌላ ቦታ ሄዳለች፡፡ ወደ መጀመሪያው ቀን፡፡ ያለፈው ሁለት ዓመት ት/ቤት መዘጊያው ላይ ነው፡፡ ከጓከኞቿ ጋር ተያይዘው ጫሞ ኃይቅ ላይ የጀልባ ሽርሽር ያደርጋሉ፡፡ አብዛኞች ሞቅ ብሏቸው ስለ ነበር የሚደርጉት ነገር ሜላትን የኮረኮሯትን ያህል ያስቃታል፡፡ ከሽርሽር መልስ አንድ ጓደኛዋ ቤት የቢራና የዳንስ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ ምሳ ላይ የበላቸው ምግብ ስላልተስማማት እንዲበትንላት በጓደኛዋ ምክር ጂን ይዛለች፡፡ አንድ ጠይም ረዝም ያለ መጥቶ ለዳንስ የስነሳታል፡፡ ከመቀመጣዋ ብድግ ስትል ገድገድ ትላለች፡፡ ይደግፍና ወደ ዳንስ ያሰነሳታል፡፡ ከመቀመጫዋ ብድግ ስትል ገድገድ ትላላች፡፡ ይደግፍና ወደ ዳንስ ወለሉ ሄደው መደነስ ይጀምራል፡፡ ሙዚቃው የዳና ሳመር ዘ ውማን ኢን ሚ የሚለው ለስላሳ ሙዚቃ ነበር፡፡ ዓይኗን ጨፍና ሙሉ ሃይሏን የልጁ ትከሻ ላይ አሰደግፈ ትጫወታለች፡፡ ቀስ በቀስ ሰውነቷን እየወረራት ደስ ደስ እያላት ሲሄድ ተሰማት፡፡ ሙዚቃው ሲያልቅ ሰውነቷን የወረራት እንዳች ረሃብ አልለቀቃትም፡፡ ለዳንስ የተየቃት ልጅ ልጇን ይዞት ወጣ፡፡ ፀጥ ያለ ክፍል ይዞት ገብቶ አልጋ ላይ ካስቀመጣት በኋላ ስሟን ጠየቃት፡፡ ነገረችው፡፡ ስሙን ነገራት አልሰማቸውም፡፡ ቀስ ብሎ ይሰማት ጀመር፡፡ ያ ደስ የሚል ስሜት በሰውነቷ ታሰራጨ እጁ ወደ ሱሪዋ ቁልፎ አመራ ለትከለክለው ሞከረች አሺ አላላትም ተወቻ ልብሷን ማወላለቅ ሲጀምር እሷም ረዳቸው፡፡ ፍቅር መሥራት ሲጀመር ብዙም አልተደሰተች፡፡ በኋላ ላይ ሰውነቷ በቆርቆር አንተቧጠጠ ያህል ተስማት፡፡ ጮክት ከዛ የሆነውን አታውቀውም፡፡ ለያዩ ወንዶች ተዋውቃለች፡፡ ማንኛውም ቢሆን ደስታ አልሰጧትም፡፡ አብራቸው የምትወጣውም ስለወደንዶች ማወቅ ስለምትፈልግ ብቻ ነበር፡፡
<!--[if !supportLists]--> <!--[endif]-->ተንጠራራ ሄኖክ ዓይኑን ገለጥ አድርጎ ሲመለከት ሜላት ከንፈሩን ሣም አደረገቸው፡፡
<!--[if !supportLists]--> <!--[endif]-->አቶ እንደልቡ የሠወ ሰው አምጥተህ አንተ እንቅልፍህን ትለጥጣለህ፡፡ አለች በመቀለድ፡፡
<!--[if !supportLists]--> <!--[endif]-->አስካሁን አልተኛሽም ማለት ነው? እኔንስ መቼ ነው እንቅልፍ የወሰደኝ? ሰባብረሽኛል አልታወቀሽም እንጂ፡፡
<!--[if !supportLists]--> <!--[endif]-->በል እስቲ ተጫወት፡፡ ተክዝ ብላ ዓይን ዓይኑን በማለት፡፡
<!--[if !supportLists]--> <!--[endif]-->ምን ሆነሽብኝ የኔ አጋዘን? ጎንጯን ጎንተል በማድረግ እሱም ትክዝ እንደማለት ብሎ፡፡
<!--[if !supportLists]--> <!--[endif]-->እንደእሱ እትየኝ ዓይንህ የሆነ ሰው ያስታወሰኛል፡፡
<!--[if !supportLists]--> <!--[endif]-->ማንን?
<!--[if !supportLists]--> <!--[endif]-->በቃመ ሄድሽ ነው?
<!--[if !supportLists]--> <!--[endif]-->አዎን ሳልወድ መሄዴ ነው፡፡ በማለት አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላ
ሣም አረጋቸው፡፡ ደሞ የረሳሁት ነገር አድራሻዬን ባልሰጥህ ልሄድ ነበር፡፡ ልነግርህ የምፈልገው ነገር የትላንትናውን ቀን መቼም አረሣውም ለማንኛውም ፃፍልኝ፡፡ እኔም እጽፋለሁ፡፡ ብላ ጉንጩን ንክስ አርጋው ነበር ደህና ሁን ያለችው፡፡
ሄኖክ ወራቱ ያመጣቸውን ወፎች እያስተዋለ በሃሳብ ጥልጥ ብሎ ከሄደበት ሲመለስ ንፋሱ መጀመሩን አይቶ ጃኬቱን በመቆለፍ ወደ ካፌ ሲያመራ የሜላት ሰውነት ለቅፅበት ውል አለው፡፡ ሰውነት መሞቀወ ሲጀመር ሳቅ በማለት ያልተወራረደ ፍቀር አለ በሃሳቡቡ፡
በሶጋራ ዙሪያ
…ሲጋራ በአንደኛው ጫፍ እሳት በሌላኛው ደግሞ የዋህ አፍ የሚገናኙበት የሲሊንደር ቅርፅ ያለው ነባሪ ነው፡፡… ይላሉ ባሙኤል ጆንሰን ሲጋራ ምንድነው ለሚለው ጥያቄ ሲመለሱ፡፡
በሃገራችንም ውስጥ ሲጋራ በሌላ መልኩ ትንባሆ መጨስ ወይም መሰንፈጥ /አፍንጫ ማሸተት መቼ እንደተጀመረ በእርግጥ አይታወቅም፡፡ ይሁን እንጂ ወደ አገራችን የገባው የእሰልምና ሐይኖት ተከታይ በሆኑ ሰዎች መሀኑ የተረጋገጠ ነው፡፡ መስፈፋት የጀመረው በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ገደማ እንደ ነበር በህዳር 8/77 እትሙ አዲስ ዘመን አስፍሮታል፡፡
በአካባቢያችን ያሉ አጫሾች የሚያጨሱት ሲጋራ ይዘት ምን እንደሆነ አውቀው ከሆነ ድምፅ በሌላው መሣሪያ ራሳቸውን መግደል ለምን እንዳስፈጋቸው የኅብረተሰብ ጥናተ ምሁራን የምርምር ትኩረታቸውን እንዳይነፍጉ ያደርጋል፡፡
በአንዱ ሲጋራ ውስጥ የተወሰነ መጠን ኒኮቲን፣ ታር እና ካርቦን ሞኖክሳይድ የሚባሉ መርዛማ ጋዞች አሉሉ፡ እነዚህ መርዛማ ጋዞች የሳንባን የአየር ከረጢቶች ኪጊዜ ወደ ጊዜ አያደፈኑት ሳንባ የመተንፈሻ ኃይሉን እንዲያጣ ከዛም እልፎ ለካንሰር እንዲጋለጥ ያመቻቹታል፡፡ ጉዳቱ ይሄም ብቻ ሳይሆን የምላስና የጉሮሮ ካንሰርም እንደሚያመጣ የህክምና ጠበብቶች ሙያቸው ለዘለዓለም ይዘከርና በጥሩ ሁኔታ ዘግበውታል፡፡
ይህም ሆኖ በእንግሊዝ አገር አንድ አስገራሚ ሁኔታ ተከስቷል፡፡ በሲጋራ የሚርካት መብት ነጻነት ድርጅት መቋቋም ነው፡፡ በእንግሊዝኛው ምኅፃረ ቃ
በተለያዩ የዓላማቸን ክፍሎች ግን የሰውን ልጅ ከነዚህ መርዛማ ጋዞች ጥገኝነት ለማውጣት እርምጃዎች እየተወሰዱ ናቸው፡፡ በቴያትር ቤቶችና ሲኒማ ቤቶቸች እንዲሁም እንዳንድ የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎ ሲጋራ እንዳይጨስ ተደንግገዋል፡፡
በአሜሪካ ሲጋራ መጨስ ለማቆም ከፈለጉ የሚመዘገቡበት ድርጅት አለ፡፡ ድርጅቱ የሚሰጥዎትን መመሪያ በተግባር ከተረገሙ ከሲጋራ ሱስ ተላቀቁ ማለት ይቻላል፡፡ እንዲት 25 ዓመት አጫሽ ያቆመች ሴት እንዴት እንደተሳካለት ስትገልፅ …የመጀመሪያው ሳምንት ላይ ድርጅቱ የሰጠኝን መመሪያ ተከትዬ ተግባራዊ ሳደርግ ከህጻንነቴ ጅምራ ያሳደገችኝና በዓለም ላይ ያለቸኝ አክስቴ ስትሞትብ ካዛን ኩት ኀዘን የበለጠ ነበር የተሰማኝ፡፡ እየቆየሁ ግን ለመድከት ብላ ነበር፡፡ ልብ አድርጉ ይህቺ ሴት በቀን ሶስት ፓኬት የምታጨስ በቀላሉ ሲጋራ ከእጇ የማይጠፋ ነበረች ማለቱ ይቀላል፡፡ ከዓመታት በፊት ይሄንኑ ጉዳይ ለአንድ ጓደኛዬ ነገሪው እሷ 25 ዓመት ካጨሰች እኔ ገና 7 አመቴ ነው እንደ እሷ ለመኖን 18 ዓመት ይቀረኛል በማለት መቀለዱን አስታወሳለሁ፡፡
አንድ ሌላ አጫሻ ደግሞ …ሲጋራ እንዳቆምኩ ስፖርት ጠዋትና ማታ ጀመርኩ፡፡ አጫሾች የደረሱበት ባልደርስ ቀላል ምግቦችን በመመዝብ ከቤቴና ከቢሮዬ ሲጋራን ሲያስታውሱ የሚችሉመተርከሻዎችና መለከሻዎች የመሳሰሉትን በማጽዳት ደህና ሆኜ ሳለ አንድ ቀን ጠዋት ከባለቤቴ ጋር በነገር ስላልተጣጣምን ሲጋራን ክብሪት ገዝቼ ቢሮ ከገባሁ በኃላ ለማጨስ ስዘጋጅ ጠረጴዛዬ ላይ የሆነ ጽሑፍ ዓይኔን ሳበው፡፡ ጽሑፍ ከጽዳት ሠራተኛዬ ለኤ የተተው ማስታወሻ ሲሆን የሚለው …ለ5 ቀናት ያህል በርትታሃል ዛሬ እንዳትጀምር ነበር፡፡ በዛች ማስታወሻ በመታገዝ ዛሬም ስፖርት እየሠራሁ ነው ይላል፡፡
በጤና ጥበቃ ድርጅትም በአንድ ወቅት ሲጋራ በሳንባችን፣ በልባችን፣ በደማችን፣ በአፍንጫችንና ጉሮሮአችን በደም ቧንቧ በአንጎል፣ እንዲሁም በቆዳችን ላይ የሚያደርሰውን ጥፋት በአካባቢው እንዲለጠፍ በትኖ በአካባቢያችንም ደርሶ በየግርግዳው ላይ ለእይታ በቅቷል፡፡ በአጋጣሚወድ አጫሾ ማቆም ባይችሉ ሲጋራ በጣም የመቀነስ ሙከራ እንዳደረጉ እማኝነት አግኝቷል፡፡ በአጋጣሚውም አጫሾች ማቆም ባይችሉ ሲጋራ በጣም የመቀነስ ሙከራ እንዳደረጉ እማኝነት አግኝቷል፡፡ በዚያው ሰሞን የካፊ ተጠቃሚ /አጫሽ ያልሆነው/ እፎይ ብሎ ነበር፡፡ አሁን አንደገና ያ ክፋ ስነምግባር ሳያገረሽ፡፡
በጨዋታ የተነሳም …ኃላፊዎቻችንን ማኖ አስነክተን አስጀምርናቸው በዚያው ቀጠል የሚል ንግግርም አድምጫለሁ፡፡ ኃላፊ ሆነ ተላላፊ መንገድኛ ህይወቱን ለመኖር ማንውም ሰው ለመኖር ካለው መብት የበለጠ ያለው አይመስለኝም፡፡ ሌላለውም ሰው አባባሌን የሚቃረን አለ ብዬም አልገምትም፡፡
ህዳር 29/77 በወጣው የአዲስ ዘመን አትምም ከአጫሾ ጎን አትቀመጡ፡፡ በሚል ርዕስ ሥር የሰፈረው ሐተታ ቢጋራ ከሚየዘጨሱ ሰዎች ዘንድ አዘውትረው ሚቀመጡ ሰዎች ላይ የሚደርሰው አደጋ በየዓመቱ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት በዓመት 500 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በሳንባ በሽጻ በመለከፍ ሕይወታችወን የሚያጡ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በአሜሪካ በቅርቡ ተካሂኮ የነበረው አንድ ጥናት እንዳመለከተው በተጠቀሰው ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር 85 መድረሱ ታውቋል፡፡ ስለዚህ ሲጋራ ያለማጨስ ብቻ ሳይሆን ከሚያቸሱ ሰዎች አጠገብ አዘወትሮ መቀመጥም ለበሽታና ብሎም ለሞት ስለሚዳርግ ጥንቃቄ ማድረጉ አይከፋም፡፡ በማለት ያስገነዝባል፡፡
ታዲያ በዚህ ሁኑታ አጫሾችን ለመራቅ ሲል ከካፌቴሪያና ካራምቡላ ተጠቃሚነት ልንወጣ ነው ማለት ነው፡፡ ከየአካባቢው የተሰባብሰብን ስለሆነም ከቤቴሴብ ኃላፊነት የራቁም እንዳሉና የካፌውም የምግብ ድንበኞች የሻይ፣ ቡና አልፎም የቢራ አዝውታሪዎች ለመሆናቸው ተጠቃሚውን በሙሉ አንድ በአንድ ማነጋገር የሚያስፈልግ አይሆንም፡፡ ነገሩ ሁሉ ግልጽ ነውና፡፡ ስለዚህ የሚኖረን ምርጫ አጫሾች ከዚህ በፊት እንደተለመደው በረንዳው አካባቢ ወይም የተለየ ክልክ ተሠርቶላቸው ቢገለገሉ የማህበረሰቡ ምት ተጠነቀ ማለት ይቻል ይሆናል፡፡
ጽዳት ለህብረተሰቡ ጠቃሚ የሆነ ቢሆንም የወጡት መመሪያዎች ተግባራዊ ካልሆኑ ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው፡፡ ሽንት መሽናት ክልክል ነው የሚለውን ጽሑፍ የከተማው ችልተኛ ባየ ጊዜ ተፈጥሮ ያመጣውን ጣጣ አትክልክሉን እያለ ባያሸፍ፣ እንዳንዱም ይህን ጽሕፍ መጠጥ ቤት አካባቢ አይቶ ታዲያ የጠጣሁትን የት ለፍሰው ሳይል ለፅዳት ተጠቃሚነት አንድና ሁለት የለውም፡፡ የሚል የማስታወቂያ ደብዳቤ የከተሞች ጽዳት እያሳሰበ በመጣበት ጊዜ በጋዜጣ ወጥቶ ተነቧል፡፡
የባሕል ዕድገትን ከሥነሥርዓት መከበር፣ ከሥነ ምግባር ነጥሎ መመልከት ወይም ለይቶ ማራመድ እነደማይቻል ዕወቀት የጠለቀላቸው ምሁራን በየጊዜው እንደሚያስገነዝቡን አሸናፊ ዘ፡ደቡብ በአንድ ወቅት አሰታውሰውናል፡፡
በካፊና በካረማቡላው ቤት ውስጥ የሚታየው የአጫሾ ሥነ-ምግባርም ከባህል ዕድገት መንቀርፈፍ ሌላ ሌባል አይችልም፡፡ እናም ይታሰብበት ለማለት ነው እናንተስ?
የባለቤትዎ ስም ማን ነው?
ላጤ ከሆኑና ለሚከተሉት ጥያቄዎ ከመለሱ የወደፊት ሚስትዎን ስም አንነግርዎታለን፡፡ ያገቡ ከሆነም ያሁኗን ሚስትዎን ስም፡፡ እናም ትክክል ለመሆኑ ተስፋ አናደርግ፡፡ /አስክሪፕቶና ወረቀት ሊያስፈልግዋት ነው፡፡/
- ከሠንጠረዥ 1 ውስጥ ከተወለዱበት ወር አቅጣጫ የተፃፈውን ቁጥር ይወስዱና ይጻፉት፡፡
- ከሠንጠረዥ 2 ከተዘረዘረት ምግቦች የሚመርጡን ምግብ አቅጣጫ ያለውን ቁጥር ይውሰዱና ይደምሩበት፡፡
- መለሱን በ10 ያባዙትና ያገኙትን ላጤ ከሆኑ 3 ይደምረበት፡፡ አግበተው ከሆነ 2 ይደምሩ፡፡ ፊት ከሆነ ደግሞ 1 ይደምሩ፡፡
- ውጤቱን ከግራ ወደ ቀኝ ይገልብጡትና ከመገልበጥዎት በፊት ከነበረው ቁጥር ላይ ይቀንሱ፡፡ /ለምሳሌ ውጤቱ 521 ቢሆን ሲገለብጡት 125 ይሆናል፡፡ ከ521 ላይ 125 ሲቀነስም 396 ይቀራል ማለት ነው፡፡/
- መልሳችሁን ገልብጡት አሁንም፡፡ እና በፊት ከነበረው ቁጥር ጋር ደምሩት፡፡
- መጠን የሌለው ሀብታም ከሆናችሁ 52፣205፣197 ደምሩበት ካልሆነችሁ ደግሞ 423፣ 571 ደምሩ፡፡
- ከሠንጠረዥ 3 ውስጥ ከስምወ /በእንግሊዝኛ ሲጻፍ/ የመጀመሪያ ፊደል አቅጣጫ ይወሰዱና ከውጤትዎ መጨረሻ ላይ ይጻፉት፡፡ /ለምሳሌ ስምዎ ሰመረ ቢሆን እና ያገኙት ውጤት 123፣ 456 ቢሆን ከስምዊ የመጀመሪያ ፊደል አቀጣጫ ያገኙ /5/ , 60 ስለሆነ ከውጤትዎ መጨረሻ ላይ ሲጽፉት 123፣ 45660 ይመጣል ማለት ነው፡፡
- ከዚህ መልክ በሰማዊ ያሉት ፊደሎች አቅጣጫ ያሉትን ቁጥሮች እንደቅደም ተከተላቸው ያስቀምጡ፡፡
- መልስዎን ለሁለት ያካፍሉት፡፡
- መልሱን በሁለት ቁጥሮች ከፋፍለወው ያስቀምጧቸው፡፡ /ለምሳሌ መልሱን 11/12/13/14/15/ በዚህ መልክ ይከፋፍሉት፡፡ /እያንዳንዱን ክፍል የባለቤትዎን ስም በእንግሊዝኛ ፌደላት ይወክላለ ከሠንጠረዥ 4 ጋር አያስተያዩት ለማለት ነው፡፡
|
Table 1 ሠንረዥ 1 January ………….90 July ………….70 February………….80 August ………80 March …………….70 September……90 April ………………60 October ……….80 May ……………….50 November……..70 June ………………60 December……..60 |
Table 3 ሠንረዥ 3 A-20 H-68 O-26 V-84 B-40 I-24 P-82 W-88 C-48 J-80 Q-90 X-58 D-62 K-54 R-46 Y-86 E-22 L-52 S-60 Z-56 F-50 M-42 T-44 G-64 N-66 U-28 |
|
ሠንረዥ 2 ሥጋ ጥብስ ከትልልቅ ሽንኩርት …………………..8 አሳ ጥብስ ……………………………..……………7 እንቁላል ጥብስ ………………………….…………6 ምንቸት አብሽ ……………………………..……….5 ቦዝና ሽሮ ……………………………..……………4 ምጥን ሽሮ ……………………………..…………..3 ክትፎ ……………………………..………………..9 |
ሠንረዥ 4 10-A 29-X 11-E 30-S 12-I 31-D 13-O 32-G 14-U 33-N 20-B 34-H 21-M 40-J 22-T 41-P 23-R 42-V 24-C 43-Y 25-F 44-W 26-L 45-Q 27-K 28-Z |
ባይገርምዎ ይሄ ጨዋታ ከ12 ዓመት በፊት በሐምሌ ወር Readers Digest ላይ ወቶ ነበር፡፡ ለዛውን አሟጧል ባይሉኝ
የነቀፋ ሐድራ፣
እርዳይታ ከመጣሁ ሰንበትበት ብያለሁ፡፡ የቤተሰብና ዘመድ ናፎቆት አየጀማመረኝ ነው፡፡ ደብዳቤ ስጫጭር ስለአገሩ፣ አየሩ፣ ሰው፣ ከብቱ እንደው ስለኑሮ ባጠቃለይ አየቃቅሳለሁ፡፡ ለዘመዶች ያለሁበትን ሁኔታ በስዕላዊ ድርስት ለማስቀመጥ፡፡ ከደብዳቤዬ ይዘት ዋጋው ክፍል ግን ሕህወትን ማቆያው የምግብ ነገር ነው፡፡ መቼም በዚያን በሞን አይሠራ ዓይነት ምግብ አልነበረም፡፡ ሚኒስትሮኒ፣ ካቻቶራ፣ ስፓጊቲ ቦሎኛሶስ፣ አስፔስቲኒ፣ ሃንጋሪያን ጉለሽ፣ ድሪቶ ምኑቅጡ ታዲያ በዚሁ አጋጣሚ ነበር የሰኃትን ቀልድ ምግብ አብሳያችንን ለምን ለይለንድና ሾ አብሾርበር የሚባሉን ምግቦች አትሠራም ሲባል ይሰራ ነበር ነገር ገን ማቴሪያል አያቀርቡም አል ያሉትን በደብዳቤምያቀለምኩት፡፡ ነገሩ በምግብ አካባቢ ተነሳ እንጂ በየቦታው የሚደመጡ ትችት አዘል ቀልዶች በሽበሽ ናቸው፡፡ ከዛ በኋላ ሳይሆን ይቀራል የምግብ አይነትስ እነስ ብሎ የሚታየው ዋናው ምክንያትም ባይሆን ትንሹ ይሆናል፡፡
በቪዲዬ ትርኢትም በኩል ኅብረተሰቡ በጥሩ ሁኔታ ይጠቀም ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ እየተበለሸ መጣ እንጂ፡፡ ከክፍል ፉክክር አለ ይባላል፡፡ ሁሉም ከፍሎች ለማህበረሰቡ ግልጋሎት መሰጠታቸውን ረስታው በትናንሽ ምክንያት የስልጣን መፈታተኛ አርገውታል፡፡ የሆነው ቢሆን ቋቱ ጠብ ላይል፡፡ ብቻ በተገልጋዩም እንዲህ ነው የማይሉት ነቀፌታ ይቀርባል፡፡ እስቲ አሁን ምናለ እዚህ ዲኩን አምጥተው ቢያሳዩን? በዚህ በብርድ ማን እዛ ሲሄድላቸው ነው? አሁንስ አበዙት የማይረባ ፊልም እያመጡ ገንዘብ ብቻ ይሰበሰባሉ፡፡ ብዙ ብዙ ትችት አለ፡፡ ለነገሩ ትችታችንን እንዳበዛን ሁሉ! ልማድ እንዳደረግ ነው ሁሉ አድናቆታችንን መግለጽ ማመስገንን ለምን እየረሳ ነው መጣን?
ሌላም ምሳሌ አለኝ ማይክ ታይሰን የዓለም ከባድ ሚዛን የቦክስ ሻምፒዬና የነበረ ጊዜ በነበር ባይቀር …እሱማ ጠግቦ ያቺን የመሰለች ሚቱን አባረራት! ትራፊክ ሁሉ ልደባደብ ይላል፡፡… እሱ ጡንቻ ራስ ነው! …ከዚያምከ …በሰተር… ዳግላስ ጋር ከተጋጠመም በኋላ /የቪዲዮ አፕሬተሮቻችን ፊልሙን የግሚያውንም ሆነ ሌላውን ስላሳዩን ምስጋና ይድረሳቸውን/… በስተቀር… አንደገናም ቢጫወቱ ድምጥማጡን ያጠፋዋል፡፡ … እሱብሎ በክስ ለማለት የቀረን ነገር ቢሮር አድማጫችን እንዳይታዘበን በመፍራት ብቻ ይመስለኛል፡፡ የታይሰንን መጥፎ ብቻ ከማውራት በስተቀር ስክብር ኮትሬት መቀበሉን፣ ትምህርቱ ከ2ኛ ደረጃ ያቋረጠውን ስለመቀጠሉ፣ እናት አባት የሌላቸው ህፃናት እንዲረዱ ቦ አድራጎ መሰጠቱን ስንናገር የተደመጥን እንኖር ይሆን?
ዛሬ ደግሞ በ14ኛው የዓለም ዋንጫ ሰሞን ማራዶናን በአለፈው የዓለም ዋንጫ ያላስገረመንንና ያላደነቅነውን ያህል …ምን እሱ ትንሽ ሲነካ መንከባለል ሆኗል ሥራው አበዛው እሱ ብሎ… ትንሽ እንኳን አናፍርም አፋችንን ሞልተን ስንናገር? ነው ወይንስ የምንደግፈው የብራዚል ቡድን ስለተሸነፈብን የግድ ዓይናችንን ጨፍነን መንቀፍ አለብን፡፡
…እባካችሁ… ለነቀፋ ስንነሳ መጀመሪያ በነገሩ ላይ ያለንን ዕውቀት እንመርምር አለያ ግልብ ያሰኝናል፡፡ አሁንም እኔንም ሳትታዘቡኝ አትቀሩም፡፡ እስቲ እኔም የነቀፋ ጽሑፌን በአድናቆት ልዝጋው፡፡ በጣም ጥሩ ነቃፊዎች ነን! ነገር ግን ጥሩ ካየን ደግሞ ብርታት በጪዎች ብንሆንስ?
ትንሽ ሂሳብ ጊዜ ቢያሳለፉስ
|
H |
F |
D |
J |
|
E |
* |
G |
F |
|
A |
D |
C |
G |
|
C |
J |
E |
B |
|
*2 |
A |
B |
C |
D |
E |
F |
G |
H |
J |
|
|
|
|
|
|
|
2 |
|
9 |
|
ከ1-9 ያሉትን ቁጥሮች የሚሊትን ፊደሎች ይተኩባቸው፡፡ ‹*› ይሄኛውም ምልክት የትኛውን ቁጥር እንደሚተካ ማወቅ አለብዎት፡፡ ከሠንጠረዡ እንደሚረዱ ጎን በኩል እና ወደ ታች ቢደምሩ የሚሰጥዋት 75 ነው፡፡ ትንሳፍንጭ እንስትዋ ፡፡ ለ የሚያገለግልዋት ቁጥር 2 ነው፡፡ ለ ደግሚ 9 ቁጥር ያገለግልታል፡፡ ለአንድ ፊደል አንድ ዓይነት ቁጥር ብቻ ይጠቀሙ ፡፡ ህን ምልክት የሚወክል ፊደል ማግኘትዋም ስራዋትን ያፋጥነዋል፡፡ መልካም ጊዜ እንመኝልዋታለን፡፡
የሰው ተፈጥሮ
ሰው ማዝራቱ አይታየውም አሉ አበው ሲተርቱ ፡፡ አዋ የራሳችንን ጉደረለት ከማየትና ከመረም ይልቅ በሌሎች ስህተት መሳቅና መሳለቅ ይቀናናል፡፡ የሌሎች መሳሳት የኛን ትልቅነት የሚያጎላው እየመሰለን ይሆን?ብቻ ስለ ሰዋች ደካማነት ካላወራንም ጨዋታም የማይደምቅ የማይመስለን አለን፡፡ አበውስ ሰው ካላማ ዥንበር አያጠልቅም ብለው የለ፡፡ በአንድ ወቅት ማዳም ዶ ፎንቴን .. ስለራሳቸው መልካምነትና ከፍተኛነት ስለሌሎች አጉልነትና ዝቅተኛነት አንዳይናገሩ ቢከለክሉ ስንት ሰዋች ዲዳ በሆኑ ነበር፡፡ .. ብላ ጽፋለች ፡፡ በተለይ ወሬ እንደ ባህል እየተለመደ የመጣበት አካባቢ ይህ ቢሆን የዲዳዋች ከተማ ተንሰራፋ ማለት ይቻል ይሆናል፡፡
አንድ ሰው በማህበረሰቡ ተቀባይነት እንዲኖረው በማህበራዊ ኑሮው አቀራረቡ ሰብዕናው እንዲለይ የግድ ስለሌሎች መጥፎነት መናገር ወይም ደግሞ መረን የለቀቀ /በማንኛውም ረገድ/ ዝላይ ማብዛት አይኖርበትም ፡፡
የኦስትሪያው ስነ ልቡና ተመራማሪ አልፎሬድ አድለር ስለሰብዕና ባለው ንድፈ ሃሳብ የሰው ልጅ ለሥልጣን /የበላይነት ስላው ከፍተኛ ፍላጎትና በጭፍን ከሚሰሩ ይልቅ በማወቅ በሚሰሩ እንቅስቃሴዋች አስፈላጊነት ላይ ትኩረት በመሰጠቱ ይታወቃል ፡፡
ፍሮይድ ታላቁ የስነልቡና ጠቢብ ሰብዕናን ደመ ነፍስ የግል ህይወት ልምድና ለህሊናና ግብረገብ የሚገዛ አስተሳሰብ / በማለት የሶስት ደረጃዋች ውጤት አድርጎ ያስቀምጠዋል ፡፡
ደመ ነፍስ / / መደሰቻ መርሆ / / የሚባለው ሲሆን ህጻን ልጅ ሲርበው የሚጮሀው ጩሀት ዓይነት ነው፡፡ ይሀውም ሲረበው የሚሰማውን መትፎ የረሃብ ስሜት በጣም በማልቀስ እንዲተወው ለማድረግ የሚፈጥረውነው፡፡
የግል ህይወት ልምድ/ / የእውነታ መርሆ / / ሲሆን አንድ ህጻን ልጅ እሳት የሚፋጅ መሆኑን ለይቶ ከእሳቱ ለመሸሳ በሚወስደው ጥንቃቄ ይገለጻል ፡፡
የሚቀትለው ደረጃ ለህሊናና ግብረ ገብ የሚገዛ አስተሳሰብ ሲሆን ይሄ ደግሞ በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ ሊያውቃቸው የሚገበቡት ደንቦች የሚያውቅበት ነው፡፡ ለምሳሌ የማዕድ ስነ ሳርዓትና የመሳሰሉትን፡፡
ከነዚህ ደረጃዋች እንግዲህ ሰብእናን እናገኛለን ፡፡ የሰብዕናው መማላትና አለመማላት ትክክለኛ መሆንና አለመሆን ግን አንድ ሰው ከሚያድግበት ቤተሰብ ት/ ቤትና አካባቢው ጋር በተያያዘ ሁኔታ የወሰናል፡ ቻ
አንድ ህጻን ሁሉንም ያገኘውን ነገር ወደ አፉ የሚከትበት ደረጃ ላይ እያለ አሳዳጊዋቹ መጫወቻዋቹን በንጽህ ሁኔታ አጥቦ በማቅረብ ፋንታ አፉ ውስጥ እንዳይከታቸው ቢቆጡና ዕቃዋቹን ቢያርቁበት በሚያደርገው ትግል በማበረታታት ፋንታ ቁጣና ቁንጥጫ የሚሰጡ ከሆነም ወደፊት በሚኖረው ስብዕና ላይ ተጽዕኖ አድርገዋል ፡፡ ያንን ዕንቡጥ ፍሬ ግን ብዙ በጣም ብዙ ጥሩ ነገሮች ሊያደርጉለት በተገባ ነበር ፡፡
እነዚህ ሁኔታዋች ሁሉ በሰብዕና ላይ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው፡፡ በአካባቢ ልዪነት የባህል የአናናር የአስተዳደግ እና ሌላም ልዩነት ሰብዕናችን የተለያየ ይሆናል ፡፡
ሰው ሩህሩህ ጎነዝ የዋህ ብልጥ ጨዋ ንቁ ታማኝ ቁም ነገረኛ ለጋስ ክፉ ምቀኛ እብሪተኛ ሴሰኛ ስስታም ………… ወዘተርፈ .. ነው ፡፡ የሆነው ቢሆን ግን ይፈልጉት ሳይሆን ከማህበረሰቡ የተማረው ነው፡፡ ማህበረሰቡ በጥሩ ሁኔታ ኮትኩቶ ያሳደረገው ካልሆነ ከሱ ጥሩ ነገር ሊጠበቀወ አይችልም ፡፡
ትንሽ ቆየት ቢልም ከአንዲት ልጅ ማስታወሻ ላይ ያገኘኃቸው ትያቄዋች እነዲህ ይነበባሉ ፡፤ ሰው ምንስ ትልቅና ትንሽ ነገር ነው በቀን ስንት ጊዜ አጥፍቶ ስንት ጊዜስ ያልማል ምን ያህል ከፍተኛና ምን ያህል ዝቅተኛ መንፈስ አለው ምን ያህል አፍቅፎ ምን ያህል ይጠላል ምን ያህል ሩህሩህና ምን ያህል ጨካኝ ክቡርና ምን ያህል ትክክለኛና ምን ያህልስ ስህተተኛ ነው ምን ያህል ክቡርና ምን ያህል ወራዳ ነው ምንያህል ጨዋና ምን ያል ልክስክስ ነው አልፎ አልፎ እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዋች በመጠኑም ቢሆን በህይወት ላይ ሳይጠቀሙን አይቀሩም ፡፡ ለነገሩ ግን እያንዳንዳችን ምን ያህል ጥሩ ነን
ስለ ሰው ተፈጥሮ ብዙም መጠየቁ ባይከፋማ ካሁን በፊት ምንጩን / ትክክለኛውን / ባላውቅውም የስነልቡና አዋቂዋች እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል ፡፡
.. ሰው ወደዚህ ዓለም ሳያስብ ወጥቶ ከፍላጎቱ ውጪ ለቆት ይሄዳል ፡፡ በምድር ላይ በትክክል አይዳኝም ሃሳቡንም የሚረዳው ማንም የለም ፡፡ በሕጻንነቱም መልእክ በወጣትነቱ ሰይጣን ሙሉ ሰው ሲሆን ደግሞ ጅል ነው ፡፡
ሚስትና ቤተስብ ካለው ደስተኛ ነው፡፡ላጤ ከሂነ ኢሰብአዊና የማይታመን የህዝብ መዝናኛ ቦታ ከገባ ሰካራም ካልገባ ደግሞ ስስታም ነው ፡፡ ድሃ ከሆነ ጭንቅላት የለውም ሃብታም ከሆነ በዓለም ላይ ያለ ዕድል ሁሉ ለሱ ሲሆን እሱ ግን ክፉ ነው፡፡ አእምሮ ያለው ከሆነ ብልጣ ብልጥ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል ፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን ከሄደ ዲያቆን ነው ካልሄደ ደግሞ ኃትያተኛ ይባላል፡፡ ከመጸወተ ወይ ጥሩ ነገር ከሰራ ራሱን ለመስታወቅ ይህን ካላደረገ ደግጀሞ ገብጋባ ነው፡፡ ወደዚህ ዓለም ሲመጣ/ ሲወለድ /ሁለሉም ሲስመው ይፈልጋል፡፡ የሕወቱ መጨረሻ ሲቃረብ ደግሞ እያንዳንድ ሊመታው ይከጅላል ፡፡ ወጣት ሆኖ ሕይወቱ ካለፈ የወደፊት ሕይወቱ ብሩህ ነበር ይባልለታ፡፡ እስሽምግልናው ከኖረ ሁሉም ሰው የውርስ ኑዛዜ እንዳደረገ ያምናል፡፡ ስለዚህ ሁሉንም ሰው ማስደሰት አይቻልህም ግዳጅህን ተወጣ ፍርሐት አይደርብህ ያለህን የማስተዋል ችሎታ ተጠቀም ፡፡ ስህተት የሰራህ ከሆነ ምንም ነገር ካለመስራት ይሻላል ፡፡
ማንም ሰው ስላንተ ችግር መስማት የሚፈልግ ስለሌለና /አለመኖሩም ጥሩ ነው፡፡ / ቢኖርም ስላንተ ችግር ምንም ማድረግ ስለማይፈልግ ችግርህን ለራስህ ይዘህ ፈገግታ አይለይህ ፡፡ ..እናንተስ ምን አላችሁ?
መሳም ወይም መሳም
በመንገድ ላይ ሲያልፉ ወይ ቆመው ገደናዋን ሲጠብቁ ወጣቶች ሰላምታ ሲለዋወጡ አይተዋል ? . ከማየትም አልፎ የሰላምታው ተጠቃሚስ አልሆኑም? የገረመኝ ነገር በየአጋጣሚው የሚስተዋለው የሰላምታ ዓይነት ብዛትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ወጣቶች በሙሉ ተግባር ላይ ማዋላቸው ነው፡፡
ካሉን የሰላምታ አሰጣጦች ውስጥ መጨባበጥ ጉንጭ ለጉንጭ መሳሳም /በህላዊ / ጉንጭ ለጉንጭ መነካካት ከንፈር ላይ በተደጋጋሚ መሳም ትከሻ ለትከሻ ማገናኘት /የአሁኑ ጊዜው ነው/ ጥቂቶቹ ናቸው እናህ አንግዲህ ሰላም ታዲያስ ሃይ ኬፍ ሃሎ ከመሳሰሉት ሌላን ጠበቅ ያሉት ናቸው ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ያለው ትከሻ ለትከሻ ማገናኘት ትክክለኛ ታሪኩን ባለውቀውም ሸምገለወ ካሉ የኅብረተሰቡ ክፍሎች ወጣቶች የወሰዱትና መሳሳምን /የሰላምታን ለመተካት ብለው ያደረጉት ለመሆኑ ማወቁ ግን ኮሌጅ መበጠስ የሚያስፈልገው አልመሰለኘም ፡፡
እስቲ ለሌላው በሌላ ጊዜ ቀጠሮ እንያዝለትና ዛሬ ስለመሳሰም ታሪክ .. ምላዴዝ.. ከምባ ምጽሔት ያገኘሁትን አጠር ያለ ጽሑፍ በዚህ መልክ ላስነብባችሁ፡፡
የሰው ልጅ የፍቅርን አሳሳም ብቻ አይደለም የሚያውቀው ፡፡ የማክበር አሳሳም የመልካም ምኞት አሳሳም የሰላምታና የመለያያ አሳሳምም ያውቃል፡፡
በአንድ ወቅት በምስራቆቹ ገዝዋች ብህል እግር መሳም ግዴታ ነበር ፡፡ አንግዲያው ተገዝው ህዝብ ለገዝው እግር ክብሩ ስለማይበቃ የገዝው እግር የረገጠበትን ዱካ ከዛም አክፈው የገዝውን ፈረስ ዱካ ይሙም ነበር ፡፡
በዱሮ ጊዜ የነበሩ በገስታት ከነሱ በላይ ማንም ጀእንደሌለ አድርገው ጀለሚመለከቱበት ይህ አንድ ምክንያት ይሆንል፡፡ በባላበቶችን ቄስ ገበዞች ደግሞ ጀእጅ መሳም ተስተውላል፡፡
ቀስ በቀስ ሴቶችም አጃቸውእንዲሳም መጠየቃቸውና በኃላም የራሳቸው አርገው ማስቀረታቸው አልቀረም ፡፡በዚህ ሁኔታ በወንዶች በኩል በዳንስ ጊዜ ከእራት በኃላ በመንገድ ላይ ወ.ዘ.ተ ሴቶቹን ለማክበራቸው እጃቸውን በመሳም መግለጻቸው ወደ ግዳጅነት ተለውጣል ፡፡
ባለፉት ጊዚያት ሴቶች እንግዳ ሲሸኙና ሲቀበሉ መሳም ነበረባቸው፡፡እየቆየ የቤተሰቡ አባል የሆነቸ ሴት ሁሉ ይህን ልማድ መከተል ነበረባት፡፡ ኤራዝም ፓተርዳም ስኪ እንግሊዝን በሚጎበኝበት ወቅት እንዲህ ሲል ጽፋል፡፡ ..እዚህ ልጃገረዶች በጣም ጥሩና ሰው ወዳጆች ናቸው ፡፡ እዚህ ያለውን ባህል መግለጫ ማመስገኛ ቃላት አይገኝም ፡፡ አንድ ቦተ በደረስክ ቁጥር ሴቶቹ በመሳም ይቀበሉሃል ሲሸኙህም ስመው ነው እንደገና ብትጎበኛቸውም እንደገና ይስሙሃል፡፡ የትም ቦታ መሳም ነው፡፡
ፈረንሳይ ውስጥም መሳም እንደ ፋሽን ነበር፡፡ ከሞንቴን ቃል ከፈረንጅ እኛጋ ያው ባህል መሳምን ዋጋ ያሳጣዋል ፡፡ ለሴቶቹ ክብርን የሚያሳንስ ልማድም አለበት ፡፡ ይህውም ማንኛውም ዓይት ሰው ከሦስት አሽከሮች ጋር ከመጣ ከንፈሩ ላይ እነዲስሙት ይገደዱ ነበር ምንም ያህ አንካን አስቀያሚ ቢሆን እኔ በግሌ ከዚህ ባህል ምንም ጥቅም አላገኝም፡፡
ምራቁን የዋጠውን ማስተማር ማንም ዋጋ የለውም ፡፡ ጥሬውን ደግሞ በቲዮሪ ማስተማር ደደብነት ነው፡፡ ስለዚህ በቀላሉ ስለአሳሳም ቴክኖሎጂና ቴክኒክ አንድ ሁለት ቃላት እንበል ፡፡
አንደምስራቆቹ አባባል መሳሳም ማለት የሁለት ነፍሶች መገናኘት እነደ ትሲኒትሲዋች ደግሞ መስኮቱን ማንካካት በበር ለመግባት አንደ ሂፓሐንድሪትሲዋች የአገላለጽ ኢላማ፡፡ ገጣሚዋችን የፓለቲካና የግብረገብ ሰዋችን ሳንጠቅስ ሁላችንም ግን ልምዱም አስተያየቱም አለን፡፡ አንድ ጊዜ መሳም ምን ያህል ያወጣል?ይሄን ጥያቄ ለመመለስ አስቸጋሪ ይሆናል ፡፡ በአንድ ነገር ግን እርግጠኞች ነን፡፡ መንም ቢሆን የመጀመሪያ ፍቅሩን አሳሳም አይረሳም ፡፡ ሌላው እውነታ ግን ብዙ የሚስም መሳምን ዋጋ ያሳጣዋል፡፡ እንደ ፈገግታ መጨባበጥ ፍቅር ቅናት ሁሉ መሳምም የሰው ፈጠራ ሆኖ በሰው ልጅ ፈጣን ዘመን ውስጥ ነው፡፡ ከፈጣን የዕድገት ደረጃ ጋር የግብረገብ ሕግጋቶችም በዙሪያችን አሉ፡፡
ነገር ግን በሁሉም አቅጣጫ ዛሬ የመሳም ንረቱ ጨምራል ፡፡ ዋጋውንም አጥታል ፡፡በየአይሮፕላን ማረፊያ ስለሚሳሳሙት /የፓለቲካ/ ሰዋች ወይንም ፊልም ላይ ስላሉት የአርቲስቶች መሳሳም እይደለም የምናወራው ፡፡ ከመጨባበጥ ትይዩ ባለውና በአንድ ጥርጣሬ በጸብራቅ የተወለደውን መሳሳም ነው፡፡
..ይህው እጄ ቢላ አልያዝኪም ያንቺን ደግሞ ልየው ፡… ..በተጨማሪ ሌላ ምን ሊባል ይቻላል ? ማናልባት አንድ ጠቃሚ ምክር፡፡
.. የሚስምህን /ሽን ውድድ/ጅ/ እና
የምትወደውን /ጅውን /ሳም /ሚ / ! ..
አቦ ሰለቸሸን ትሉ ይሆን? እናንተ ባይወጣችሁም እኔ ተሰምቶኛል ብቻ ስለመሳሳም ከተነሳ ዘንድ ሌሎች ጠበብቶች ደግሞ የመሳምን ትርጉም ያሉትን እንደሰማሁት ላካፍላችሁ ብዮ ነው፡፡
አንዳ ጉብል ፍቅረኛዋ እጃን ቢስም የጠለቀ ግምትና ክብር እንደ ሰጣት ትከሻዋን ደግሞ ከሳመ ለሳ ፍላጎት እንዳለው ጉንጫን ቢስም ደግሞ ጥሩ ጋደኛው እንደሆነች አርጎ እንደሚያስብ ከንፈራን ዓይኑን ከድኖ ከሳማት እንደሚያፈቅራት ግንባራን ከሳመ እነደሚናፍቃት ጸጉራን ሲስም እንደመያስብላት ጆሮዋን የሳማት ከሆነ ደግሞ ለብቻቸው ቢሆኑ ደስ እንደሚለው ምላሱን አውጥቶ ከሳማት ደግሞ እንድትስመው እንደሚፈልግ አርጋ ትወስደዋለች ፡፡
እናንተ በኑሮ ልምዳችሁ የተጠቀማችሁበት ከዚህኛው አተረጋገም ጋር ይዛመዳልን መልሱን በያላችሁበት አጣጥሙት፡፡
ብስራት ሰላም
መ ጠ ሪ ያ
..ስማ አንተ ..ብሎ የሚጠራ ሰው እንዴት ያበሽቀኛል መሰላችሁ ፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ሰው ማንኛችንም ብንሆን የምን ገምተው ስነስርዓት የሌለው በጭንቅላቱ ከሚያስብ ይልቅ በጡንቻው የሚያስብ አርገን ነው፡፡ ሁለችን ማንሆን እንካን አብዛኞቻችን ፡፡
አዋ የስም ነገር ይከነክናል ፡፡ በየትኛውም አገር በሚገኝ መዝገበ ቃላት ውስጥ ከስማችን የሚበልጥ ቃል እናገኛለን? አይመስለኝም ፡፡ ስማችን አብሮን ይወለዳል አብሮን ይኖረል ፡፡ በመጨራሻም አብሮን ይሞታል ፡፡ የአንዳንዶቻችን ማለቴ ነው ፡፡ የአንዳንዶች ስም ደግሞ ባለቤቱ ከኖረበት የሕይወት ዘመን በላይ ይኖራል ፡፡ ይሄም የስሙ ባለቤት ለስሙ መዘከሪያ የሚሆን ስራ ሰርቶ አልፋል ማለት ነው፡፡
ስሞች እንደ ጊዜው የመልክዓ ምድር አቀማመጥ ፋሸን መደብ/ የኑሮ አቃም / ሙያና ትምህርት የተለያዩ ናቸው፡፡
በውሉ አስተዳደር ክልል የስሞች አደራደር ትንሽ ለየት ያለ ነው፡፡ አባትና ልጅ የክርስቲያን ስም ኖራቸው አያት ላይ ሲሰልሙ አንስማለን ፡፡ መላኩ ጌታቸው ሁሴን መሐመድ ይመር ..ወዘተርፈ ፡፡
በደቡብ ሸዋ ስንመለከት በከምባታና ሐድያ ዮሐንስ ሐንቆሬ ዳዊት ላጲሶ የመሳሰሉትን ስሞች እንሰማለን ፡፡ይሄ ሁኔታ በአካባቢው ካሉደት የወንጌላውያን ትምህርት ሥርጸት የስሞች ሁኔታ እየተዳቀለ መምጣቱን መገንዘብ ይቻላል ፡፡
ቆየት ባለው ጊዜ አንድ ህጻን ሲወለድ የአያቱን ስም ካልሆነም የቅርብ ዘመዶቹን ወይም ደግሞ በተወለደበት ቀን ጋር በሚገጥመው በመልአክ ስም ስያሜ የጠራ ነበር ፡፡ ስም አውጪዋቹም ክርስትና አባት ቄሶች እና ለቤተሰቤ ጥሩ የሚመኙ ሁሉ መሆን ይችላሉ፡፡
የስሞች አሰያየም ከጊዜው ጋር እየተቀያየረም ይመጣል ፡፡ በአንድ ወቅት ዳዊት የሚለው ስም በዛ ያለ ሆኖ ቢታይም በሌላ ጊዜ ደግሞ ሰለሞን የሚለው በልጦት ይታያል ፡፡ በየጊዜው ዝና የሚያገኙ ሰዋች በአንዳንድ አካባቢዋች ላይ ተጽጽኖ ይኖራቸዋል ፡፡ ከዚህ ሌላ በሀገራችንም ቢሆንክ ጊዜው ጋር እየመጡ ያሉ ስሞች ይስተዋላሉ ፡፡ እንደ አብዮት ታገል የመሳሳሉት ፡፡
የዘመኑ ልጆች ሌላም ዓይነት የስም አሰያየም በፍቅር ይዘውታል ፡፡ ቲቲ ቢቢ ቺቺ ኩኩ ቡቡ ኬቲ ቤቲ ናቲ …. ወዘተ አንዳንድ ስሞች በእውነቱ ከሆነ የውሻ ይሁን የድመት ወይም የመኪና መለያ የላቸውም ፡፡ ለነገሩማ ከበቡሽ ታደለ የምትባለዋም ወጣት የስማን የመጀመሪያ እንግሊዝኛ ፊደል ከአባታ ስም የመጀመሪያ እንግሊዝኛ ፊደል ጋር በማገናኘት ኬቲ ተሰኛለች፡፡ የዘልማድ ሆኖብን በፈረንጅ ስም የሚጠራ ሁሉ መልኩም ቆንጆ እየመሰለን፡፡ /ፈረንጅ ሁሉ ቆንጆ ነው ያለን ማን እንደሆነ ባላውቅም ኬቲ ወይም ሱዚ /በጋደኞቻ / ተሰኚዋን ግንባር ለግንባር ስናገኛት በሳ ቦታ የምናፍር አለን ፡፡
ልጆች ሆነን ካስ ስንጫወት አንድ ጋደኛችንን ሳሚ እያልን ነበር ፡/ሳሙኤልን / በማሳጠር የምንጠራው፡፡ ይሔን የሰማ አንድ ተንኮለኛ ካሱን ትቶ ወገቡን በመያዝ …አሁን አንተን ነው ሳሚ ቢገዛማ ቡቡ ነበር የምትባው ..ያለው ትዝ ይለኛል ፡፡ አሁን ቡቡ የሚለው ስምም ቆንጆና ተፈላጊ ስም /በዘመኑ ልጆች/ ሊሆን ፡፡
ወላጆች አልፎ አልፎ ልጆቻቸው ከሌሎች ልጆች ለየት ያሉ እንዲሆኑላቸው ስለሚፈልጉ የተለየ ስም ያወጡላቸዋል፡፡ የኃላ የኃላ ልጆቻቸውን ሊጎዳም እንደሚችል ባለመገንዘብ፡፡ እነዚህ የተለየ ስም ያላቸው ልጆች በማህበራዊ ኑሮአቸው ወስጥ ከእድሜ ገደኞቻቸው ለየት ባ ሁኔታ ያድጋሉ ፡፡ ተነጫናጭና ለየት ያሉ፡፡
እንዲህም ሲባል ለየት ያለ ስም ያላቸው ሙሉ በሙሉ ጸባያቸው በዚህ መልክ ይቀረጻል ማለትም አይደለም፡፡ ብዙዋቹ ግን ስማቸው የሚሰጣቸው ስሜት አናናራቸውንም በዛው ያድጋል ፡፡ በሴት ስም የሚጠሩ ወንዶችን ብንወስድ በልጅነታቸው መሰቂያ ስለሚሆኑ ለየት ያሉና ዝምተኞች ይሆናሉ ፡፡ ብዙ ጊዜም ከማህበረሰቡ የሚገለሉበት አጋጣሚም አለ፡፡ ደም መላሽ ገነነ…የመሳሰሉት መጠሪያ ያላቸው ልጆች በአብዛኛው ጠበኞች ናቸው፡፡ ሌላው ቢቀር እኔን ያገጠሙኝ ፡፡
በቺካጎ የሎዮላ ዮኒቨርስቲ የስነ ልቡና ጠበብቶች ዶ/ር ሮበርት ኒኪላይ አርተር ሃርትማን እና ጄሴ ቨርሊ የስነ ልቡና ህመም ፍርድ ገዳዮችን ሲመረምሩ ሰማንያ ስምንት የተለየ ስም ያላቸውንና እንዲሁም ሰማንያ ስምንት የአዘቦቱ ቀን ስም ያላቸውን በማጥናት ፡፡….
……የተለዪ ስሞች ከጤነኞች መህበራዊ ግነኙነቶች ጋር ይጋጫሉ ፡፡ ይህም የተረበሸ አቃም ይፈጥራል አንድ ህጻን ልጅ የሚያርፍበት ዓይነት ስም የሚያደናግር የወንድ ወይም የሴት መሆኑ የማይታወቅ ዓይነት ስም ቢሰጠውና መሳቂያ ቢሆን ለስሙ ሁልጊዜ እንደተጣላ መኖር ስላለበት ስሜታዊ እግሮች ሊከሰቱበት ይችላሉ፡፡ .. የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል ፡፡
ስሞችን ለህጻናት በምንሰጥበት ወቅት ካደጉ በኃላ በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ በምይዙት ቦታ የስነልቦና ችግር እንዳይገጥማቸው የግዜውን ሁኔታ(ፋሽኑ )በመከተል በጣም የተለየም ስም ሳይሆን በጣም ብዙ ህጻናት የሚጠሩበትም ያልሆነ ለጆሮ ደስ የሚል ሲያሜ ልናደርገው ለነገው ማሙሽ ቨስነልቦናዊ አቃም ይረዳዋልና እናስብበት ፡፡
የስም ነገር ከተነሳ በቅርቡ የሰማሁት ደግሞ ጊምቢ /በወለጋ አስተዳደር ክልል / የምትገኝ አውራጃ/ አካባቢ ሚስት ባላን በጣም ትልቅ ችግር ላይ ካልሆነች በሰተቀር በስሙ እንደማትጠራው ነው ፡፡ ሌላው ቀርቶ ጎረቤት አካባቢ የባላ ሞክሼ ትንሸ ልጅ እንካን ቢኖር እራሳ ስም አውጥታ ትጠራዋለች እንጅ በውነተኛ ስሙ አትጠራውም ይባላል፡፡ ሆስፒታል ልጃን ለማሳከም ሄዳ የልጃን ስም አስመዝግባ የአባቱን ስም ስትተየቅ እንካን በአካባቢም ዘመድ ወደ ጎረቤቶች ከሌሉ እሳ ጨጥ ነው ፡፡ ብቻ አሁን አሁን የሴቶችንም ማህበር ስለተመሰረተ በስብሰባቸው ላይ ማህበራዊ ጉዳዮችን እያነሱ መወያየት ስለጀመሩ ይህ ልምድ እየተተወ ነው፡፡
እናቶቻችንስ በየቤቱ የማታጠፋዋን እህል ፈጅ ያቺ ሴትዮ የእከሌ ሚስት እመቤቲቱ እያሉ የሚጠሩት ለምንድን ነው ? ተስታችሁ እንካን ……… አይጣ ካላችሁ ስምህን ቄስ ይጥራው እሳ በሰም አትጠራም ተብላችሁ አልተገሰጻችሁም? የጊምቢ አካባቢ ሴቶች ባሎቻቸውን በስም አለመጥራታቸው ከእህል ፈጃ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ነገር ይኖራል ?
እኔ እስካሁን የደረስኩበት ነገር የለም እናንተ ካወቃችሁ ግን አደራ ሹክ በሉን ጣጥፋችሁ፡፡
ሃያስውና ትችቱ
ሃያሲያን ብዙ አይነት ቢሆኑም በአንድ ነገር ይመሳሰላሉ ፡፡ ተቃውሞአቸውን በመግለጻቸው አልፎ አልፎ ሃሞታቸው መረር ያለው ሃያሲያን አልታጡም ፡፡ ጃክ ሻቼ የተባለው ስረ ፓሪስ ቲያትር ቤት መድረካ ላይ ሸጉጥ ይዞ በመውጣት እሱ በጠላው ድራማ የሚያጨበጭቡትን ተመልካቾች ያስፈራራ ነበር በዘመናችን ያሉ የስነጽሁፍ ሃያሲያን በቃላት ብቻ መወሰናቸው ተመስገን ነው፡፡
አንዳንድ ሃያሲያን የጽሁፍን ባለቤት በግል የሚያውቁትን የማይወዱት ከሆነ የጭቃ ጅራፋቸውን ያነሱበታል መተቸት ያለበት ግን የተጻፈው ጽሁፍ ብቻ ነበር ፡፡ በሀገራችን ቆየት ባለው ጊዜ በእንደዚህ አይነተ ሃያሲያን መብዛት ሳይሆን ይቀራል መንግስቱ ገዳሙ.. አሳማና ድመት.. በምትለው መጻህፋቸው ውስጥ ባስቀመጡት ማስታወሻ .. አንድም የሚያስቀው አንዱን ያስተከዘው ይሆናል ፡፡ አንዱን የሚያስደነግጠው አንዱን ወደግል ስሜቱ ያመራውና የገዛሀሳቡን በመዘርጋት ልዩ ትርጉም ይሰጠው ይሆናል ይሁን እነጂ ደራሲው በትርፍ ሰአቱ በፊደል አጣጣል አንደመጣለት የጻፈው ነውና ምናልባት ተሳስተሀል የሚለኝ ቢገኝ እኔ እሱ እሱ እኔን ያለመሆኑ ለማስረዳት አልሰንፍም ፡፡ ብለው የጻፉት ወደው አይደለም ፡፡
ሌሎች ደግሞ ከጸሐፊው ጋር ባላቸው ትውውቅ የተነሳ እንዲያው በደፈባው4 የሙገሳ ጽሑፍ ያቀርባሉ፡፡ ወጣም ወረደ ግን ጽሁፍ ያዘለውን ፍሬ ነገርም ሆነ ፍሬ ፈርስኪ ቅንጣት ያህል አይለወጥም፡፡ መልእክቱ በተደራሲው የማገናዘብ ችሎታ እየተጣራ ይሰለቀታል ፡፡
ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋባው ነጥብ የአንድ ጋደኞዮ የየጊዜው ትችቱ እያስገረመኝና እያሳቀኝ ሲኖር በሮበር ኤንድ አዘር ኪዮሩሪ የዚቲስ በምለው መጽሀፍ ውስጥ ስለ ሃያሲያን የተጠናከረውን ካነበብኩ በኃላ ነው፡፡ ያነበብኩትን የጹሑፍ መጨረሻው ላይ አጋራችኃለሁ ፡፡ አሁን ግን ስለ ሃያሲው ጋደኛዮ በጥቂቱ ፡፡
ስለጋደኛዮ መልኩና ቁመናው ባልነግራችሁ ይሻላል ፍቅ ር እንዳያሲዛችሁ ፡፡ አቀራረቡም እንደው ዝም ነው፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ ገና ሰላም ስለው ትችቱ ከሰላምታዮ ይጀምራል በሳቅ እየተጀበ /በመጥፎ አይደለም ከመቀራረብ የተነሳ ነው/ ትንሽ ወረቀት ብጤ በጄ ከያዝኩ . መቼም የሚነበብ ነው. በማለት በፈገግታው ይቀበለኛል ፡፡ ፈገግታው እንግሊዞች disarming የሚሉት ዓይነት ነው፡፡ ትቅ አስፈቺ የሚለው አማርኛችን ይፍታው ይሆን?የተገናኘ ነው በምሣ ሰዓት ከሆነ እራት ሰዓት ላይ ብመልስልህስ ?ይላል ከዛ ፈገግታው ጋር . እሽግን አስተያየትህንም በጽሁፍ ብጤ ጨምረህ ብትሰጠኝ . እለዋለሁ ፡፡ እኔም አንደሌላው ጊዜ ከአስተያየቱ ጋር ሲመልስልኝ ታዲያ ማታውን በሙሉ መሳቅ ነው፡፡ ኮስተር ያለ ጸሐፊ ነኝ የምል ብሆን ኖሮ ገና በመጀመሪያው አስተያየት ገመድ ልፈልግ ሳልሄድ ቀረሁ ብላችሁ ነው ፡፡
አንድ ጊዜ የመድረክ ዝግጅት ነበረብኝና ያጠፋሁት ካለ ብታርመኝ ብዮ ጋብዝኩት ፡፡ ዝግጅቱ ሲያልቅ ምን አለኝ መሰላችሁ ..ደህና ትፈጨረጨሪያለሽ ..
ደህና ነው ያልኩትን አጭር መጣጥፍ ካነበበ በኃላ በጻፈልኝ ማስታወሻ ….. ብለህ የሰየምከው ጹሁፍህ በዚያ ሰሞን ጠፍቶብኝ እነደ ነበርና በኃላ እንዳገኘሁት ያወጋሁህ ይመስለኛል ፡፡ አስተያየቴን በአንድ አጭር ጨረፍተ ነገር ላጠቃለው ፡፡
..አንደጠፋ ቢቀር ይሻል ነበር ፡፡.. የሚል የነበባል ፡፡ ያልጠበቅኩት ዓይነት ትችት ስለሚሆን ብቻ የሳቅ ሴሌቼን ይኪረከኩራቸዋል ፡፡ በቀልድ መከሸንም ያውቅበታል ትችቱን ፡፡
ስለሌላ ጽሁፍ ደግሞ ትችቱን ነጥብ በነጥብ ከደረደረ በኃላ … እስካሁን የጻፍኩትን መለስ ብዮ ሳነበው . ሒትለር በዚህ ዓይነት ቅቤ አይደለም እንዴ! እያልክ የምታስቀኝ ትዝ አለኝ፡፡ እግረ መንገዱንም አንድ ታሪክ አስታወሰኝ ፡፡ እንዲህ የምል ነው፡፡ ….
ሰውዮው የወታደሮች አሰልጣኝ ነው ፡፡ ታዲያ የምስጋና ቃል ካፉ ይወጣል ማለት ዘበት ነው አሉ ፡፡ አንዱ እልክ የያዘው ምልምል ቀን ከሌት እየታተረ ሲዛጅ ከርሞ በፈተና ዕለት ዕጽብ ዱንቅ የተሰኘ ትርኢቱን ለአሰልጣኙ ያቀርባል ፡፡ አሰልጣኙ፣ እነደተኮሳተረ ተመለከተውና ..ካንተም የከፋ አይቻለሁ ፡፡. ብሎ ሸኘው አሉ፡፤ ..በማለት አስቆኛል፡፤ መቼም አሰልጠኙ ራሱ ገደኛዮ እነደሆነ አርጋችሁ እንዳልገመታችሁ እርግጠኛ ነኝ ፡፡ ምክንያቱም ገደኛዮ አስተሳሰቡ እንጂ ዕድሜው ገና አንድ ፍሬ እምቦቃቅላ ነው ፡፡
እኔም አያርመኝም ትንሽ ነገር በጫርኩ ቁጥር ለሱ መስነበቤን አልተው እሱም መሳደቡን አይተው ነገሩ ደግነቱ በቃለት ሆነ አንጂ ቃላት ወደ ዱላነት የሚቀይሩ ቢሆን የምጸፍባቸው ጣቶች እርሳስም መያዝ ያቃታቸው ነበር የሆነ ነገር ጫጭሬ የሱን ሂስ ለመጫር ባገኘሁት አጋጣሚ እሞክራሁ ፡፡ ኦስካር ዋይልድ .. ሃስ ማለት ሻማ ነው፡፡ በሌሎች ለመለኩስ የሚጠብቅ ሻማ .. አንዳለው የሱን የሂስ ሻማ ለመለኮስ ባለኝ ፍላጎት ሻማው ከተለኮሰ ግን በጣም ይቀጣጠላል ፡፡ ማረጋገጥ ከፈለጋችሁ የሆነ ነገር ጣጥፉና እባክህን ፈራችሁ ? አይዞን የሂስ በትርን እነሾክስፒር ሳይቀሩ ቀምሰዋለወ ፡፡ ለዚህም ሮበርት ሄንድሪክሰን ከላይ በተገለጸው መጽሀፉ ላይ ያቀናበረውን በዋቢነት እነሆ፡፡
ሼክስፒር ስድስት መስመሮች ያለስህተት አይጸፍም ሣሙኤል ጆንሰን፡፡
ቶማስ ባቢንባተን ማካውሌይ ስበር ትራንድ ባሬር ስራ ሲጽፍ፡- የትሮፒክ አየር ጸባይ ውስጥ ያልኖረ ሰው ነጎድጋድን አያውቅም የኒያጋራ ፋፋቴን ያላየ ደግሞ ስለፋፋቴ ትንሽ ቢያውቅ ነው ፡፡ የባሬን ማስታወሻ ያላነበበ ግን ውሸት ምን እንደሆነ አያውቅም ማለት ይቻል ይሆናል ፡፡ ብላል ፡፡
ማንነቱ ያልተዘገበ ሃያሲ የቶማስ ሃረዲን .. ያልታወቀችዋ ጁድ .. የሚለውን መጽሀፉን አቃጥሎ አመድን ልኮለታል ፡፡
ልምድ የሌለው ገጣሚ ደግሞ .. ለምንድን ነው የምኖረው ? ...በሚል ርዕስ ረዝም ግጥ ለኤውጌኔ ፊልድ / የመጽሄት አዘጋጅ / ልኮለት ፊልድ አንዳልተቀበለው ለማስረዳት.. የምትኖረው ግጥምህን በፐስታ ስለምትልክ ነው፡፡ ብሎ መልሶለታል ፡፡
ኦስካረ ዋይልድ እስር ቤት ውስጥ እያለ ማሩ ኮሬሊ / የብቀላ ደራሲ the one who’s forgotten / ጥሩ ጸሓፊ ስለመሆና ሲጠየቅ.. እንደ አጻጻፈ ከሆነ እስር ቡት መግባት ነበረባት፡፡ .. የሚል መልስ ሰጥታል ፡፡
ጌርትሩድ ስቴይን ሰውሻዋ ሔሚን ገ ዋይ ምስል አሸባሪ ሁን ፡፡ .. ስትል መክራለች፡፡ ሔሚን ግዋይ በስነጸሑፍ የቦሼክ ተሸላሚ ነበር ፡፡
ማርክ ትዌይን ለኔ የፓ ገጥም አይነበብም ልክ እንደ ጂን አውስቲን ፡፡ እንደውም ልዪነት አለ ፡፡ የፓን ግጥም ደመወዝ እየተከፈለኝ ባነበው እችላላሁ ፡፡የጂንን ግን በፍጹም ፡፡..
እስቲ በመጨረሻ ቲያትር አዘጋጁ ሃሮልድ ፒንተር የደረሰው ደብዳቤው የጻፈውን መልስ ላስነብባችሁና ልሰናበት ፡፡
ውድ …………..
. የልደት ቀን ግብዛ ስለሚለው ቲያትር አንዳንድ ያልገቡኝ ነጥቦች ስላሉ እንዲያብራሩልኝ በትህትና እጠይቃለሁ ፡፡
- ሁለቱ ሰዋች እነማን ናቸው ?
- ስታንሊ ከየት መጣ ?
- ሁሉም ግን ጤነኞች ናቸው ?
ለነኝህ ጥያቄዋች መልስ ካላገኘሁ ትያትርዋን ሙሉ በሙሉ ልረዳው አልችልም ፡፡
የርስዋው ታማኝ
ወ/ሮ ……………
ውድ ወ/ሮ …………………
የደብዳቤዋን ትርጉም ቢያስረዱኝ ያልገቡኝ ነጥቦች እነዚህ ቸናቸው ፡፡
- እርስዋ ማን ነዋት ?
- ከየት ነው የመጡት ?
- ጤነኛ ነዋት?
ለነኝህ ጥያቄዋች መልስ ካላገኘሁ ደብዳቤዋትን ሙሉ በሙሉ ልረዳው አልችልም ፡፡
የርስዋ ታማኝ ፡፡
ሃሮልድ ፒንተር
በሉ ደሞ እንግዲህ እርስዋ ከማንበብዋ በፊት ትችቱን ቢሰጠኝ ሃያሲው ጋደኛዬን ልፈልገው መቼም አላርፍ አይደል ?