ህይወት ? ክፍል 5
በዓለም ላይ ስንኖር በፈለግነውና ባሰብነው መንገድ ሳይን እያንዳንዷ ቀን ባልተገመተው ሁኔታ ነው እየከነፈች ያለችው፡፡ ምክንያቱ ግን ለብዙዎቻችን ግልፅ አይደለም፡፡ በርግጥ በግላችን ኑሮም ሙሉ በሙሉ ወሰኝ አኛው ባለመሆናቸን ለነገሩ አስተዋጾኦ ይኖረዋል፡፡
ከእኛነታችን ስንነሳ በጤንነትና በማህበረሰቡም ተቀባይነት ኖሮን ለመቆየት የተወሰኑ ያልተጻፋ ህጎችን መጠበቅ ይኖብናል፡፡ ለምሳሌም ብንወስድ የግል ጽዳታችንን የቀን ተቀን ክትትል አድርገን መጠበቅ የሃይዲን ሳይንስ ህጉን በተለይዩ ሁኔታዎ አቀበሉናል፡፡ ይህን ህግ ካልጠበቅን ጥገኛ ነፍሳት ሰውን መቅረብ እስኪያሳፍሩን ድረስ ሊጎዳኙን ነው፡፡ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብም ካልተመገብን የውስጥ ተሃዋስያን ሆዳችን ውስጥ እየጯጯሁ ጤናችንን ሲያናጉትና ከማህበራዊ ህይወት ሊያርቁን ይዘጋጃሉ፡፡
በቤተሰብ የኑሮ ተቋም በእኛነታችን ለቤተሰቡ ፍቀር ስንል የምንከፍላቸው ግዴታዎች ወይም ያልተጻፉ ህጎች ያስጠነቅቁናል፡፡ ከነኝህ ግዴታዎች አንዱ ካልተሟላ ያለን መዋደድና መተሳሰብ አደጋ ላይ መሆኑንም ለማወቅ … ኮሌጅ መበሠስ የሚያሰፈልገው … ጉዳይ አይንም፡፡ እያንዳንዱ አባል የቤተሰብ ፍቅር ፀንቶ መኖር ከፈለገ ከሱ የሚጠበቀውን ግዴታ መወጣት አለበት፡፡
ቤተሰብ ያለ ጎረቤትም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ይፍጥራል፡፡ መኖሪያችን በአጥር ስለተከለለም አትድረሱብኝ የማለት ደረጃ ከባህልና ኤኮኖሚ አቋም እንኳን ስንገመገም አልደረሰንም፡፡ ስለዚህም ቤትና ጎረቤት ዘንከን ሳይግጥማቸው ኑሮን ለመግፋት አሁንም በውስጥ የሚታወቁ ድንጋጌዎ ይኖራሉ፡፡ ጎረቤት ልብስ አያጠቡና አያሰው ከሆነ ቤቶቻችን ጣላቢ ቆሻሻ ለማቃጠል መነሳት የለባቸውም አለያ በዘልማድ የታወቁት ድንጋጌዎች ጥሰው ከጎቤት ይቀያየማሉ፡፡ ከቤት ግብዣ ኖሮ ተጋዛዥ በሙዚቃ መደሰት ካለበት የጎረቤትን የእረፍት ቀን ወይንም የእንቅልፍ ሠዓት ማደፍረስ አይገባም፡፡ ድንጋጌዎች ከተበላሹ ገን የከፋ ቀን ደራሽ የጎረቤት ወዳጆችንን ልቤ እንዲርቀን ምክንያት ሆነዋል፡፡
እንግዲህ ጎረቤት ካስቀየምን ስማችንም ማህበረሰቡ ውስጥ ሲነሳ ነው፡፡ ማህበረሰብ የሰፋ ደረጃ ቢኖረውም በዕቁቡ፣ በዕድሩና ሌላም የመረዳጃ ማህበራት ውስጥ ለመቀጠል ያልተጻፉትንም ሆነ የተፃፍጽን ህግጋት ማክበር ቀዳሚ ግዴታችን ነው፡፡ ከማህበረሰብ መውጣት ማለት ከባህር ውስጥ የወጣን አሣ መሆን ነውና፡፡
ከዚህ ላይ ያልተፃፉት ህጎች ሙሉ በሙሉና ከተጻፍትም በከፊል ሰው በማህበረሰቡ አዛውንቶች ይመከራል፣ ይወቀሳል፣ ይቀጣል፡፡
አንድ ሰው በሌብነት ወንጀል ቤከሰስ ህግ ተላልፏልና በፖሊስ ታድኖ ፍርድ ፊት ይቀርባል፡፡ እዚህ ላይ እንግዲህ እንደ ህግ አስከባሪ ሆኖ ፖሊስ ተጨምሯል፡፡ ሥራውም አጥፊዎን እያደነ ለጥፋታቸው ፍርድ እንዲቀበሉ ማድረግ ስለሆነ ተገቢ ቦታ አለው፡፡ የፖሊስ የስራ ተግባሩ ለማህበረሰቡ በጣም የተቀደሰው ሲሆን በዚህ ሙያ የሚሰማራው ሰው ራሱ ህግ ተላላፊ ወንጀላኛ ለሆነስ? የህግ የበላይነት አበቃ ያስኛል፡፡
ስላልተጻፈም ሆነ ስለተጻፈ ኅግ ከሁሉም በፊት የህሊና ፍርድ ወይም የህሊና ሚዛን ወሳኝነቱን ለሰዎች ልጆች ባይደበቅም የህሊና ሚዛኑ በብዙዎች ዘንድ ከተረሳ መቆየቱ እህህ …… ያስብላል፡፡ ግን ህይወት ምንድን ናት?