ማውጫ

  1. በድርሰት በፊልም አዘጋጅነትና በተዋናይነት እስካር ተሸላሚዎች

ሀ. ቻርሊ ቻፕሊን

ለ. ኦርሰን ዌልስ

ሐ. ሲልሽስተር ስታሎን /ታምቦ/

  1. የቱት አባት ፊልም ተሳታፊዎች

ሀ. ፍራንሲስ ፎርድኮፓላ

ለ. ማርሎን ብራንዶ

ሐ. አል ፓኪኖ

መ. ሮበርት ዶ ኒኖ

  1. በፊልም ተዋናይነት የማይረሱ

ሀ. ጃፍ ቻንድለር

ለ. ጌሪ ኩፐር

ሐ. ቻርለስ ኮበርን

  1. ጣልያናዊ ተዋናዮች

ሀ. ጁሊያኖ ጄማ

ለ. ፍራንኮ ኔሮ

ሐ. ሊ ማሳሪ

  1. የሆሊውድ ሴት ተዋንያን

ሀ. ጁሊ አንዲሪውስ

ለ. ጆአን ኮሊንስ

ሐ. ሜሪል ስትሪፕ

  1. የሙያ ልዩ ተስጥኦ ያላቸው

ሀ. ስታቨን ስፒልበርግ

ለ. ቻርድ ቻምበርሊዶን

ሐ. ፒቶር ኦ ቱል

  1. ከሴት ተዋንን ህይወት በጥቂቱ

ሀ. ኤልሳቤጥ ቴይለር

ለ. ጄኒፈር ቢልስ

ሐ. ሜሌኔ ግሪፊትዝ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ቻርሊን ቻፕሊን

ቻርሊን ቻፕሊን ሚያዚያ 16. 1989 በለንደን ከተማ ቻርለስ ስፒንሰር ቻፕሊን የሚለውን ስም መጠሪያው በማድረግ ተወለደ፡፡ ዝናን በማትረፉም በስሙ ላይ ስር የሚለውን ቅጥያ ለማግኝት በቅቷል፡፡ በአሜሪካን ድምጽ አልባ ፊልም ላይ የአሳዛኙ ዘዋሪ ልጅን በመፍጠሩ በዓለም ደረጃ ዝናን ያተረፈ ትውልድ እንግሊዛዊ፣ አሜሪካዊ ዜግነት ያለውን ተዋናይና የፊልም አዘጋጅ ነው፡፡ ወደ ሲኒማው ዓለም በ1917 ከገባ ከሁለት ዓመት በኋላ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት የተከበሩ ሰዎ አንዱ ሆኗል፡፡ በ1920 መጀመሪያዎች ገደማም ችሎውን ለመጠቀም የትኛውም ስቱዲ ስላልደፈረ (የሚከፈለው ገንዘብ በጣም ብዙ ነበርና) ራሱ በሚያቀርባቸው ፊልሞች ብቻ መተወን ጀመረ፡፡ በ1920ዎቹ መጨረሻ ዓመታት ላይ ድምጽና ፊልሞችን በማቀናጀት መስራት ሲጀምር ጥቂት ፊልሞች ቢሰራም እነዚህ ሥራዎቹ ብዙ ሳይቆዩ ዝናውን ቀነሱበት፡፡ ቀደምት ሥራዎቹ ግን በፊልም ስራ ጥንታዊነታቸው አዳዲስ አድናቂዎች አፈሩለት፡፡ ከቻፕሊን ድቅ አስቂ ሥራዎች /1921/ /ትንሹ ልጅ/፣ /1931/ የከተማ መብራቶች /1936/ የሰለጠኑ ጊዜያት እና /1940/ አምባ ገነት የሚሉት ፊልሞ ይጠቀሳሉ፡፡ ከዳግማዊ ንግስት ኤልሳቤጥም በ1975 ስር የሚለውን ማዕረግ ተቀበሏል፡፡

 

የሙዚቃ አዳራሽ ዳንኪረተኞች ከነበሩት ቻርለስ እና ሃና ቻፕሊን ከተማቡት ወላጆች የተገኝው ቻርሊም 8ቱ የላንክቫየር ወጣቶች በሚባለው ቡድን ውስጥ በ8 ዓመቱ ነበር የኪነጥበብ መድረክን የረገጠው፡፡ ይህ የሆነውን አባቱ በሞተና እናቱ አሁንም የአእምሮ በሽተኞች ሆስፒታልን መጎብኝት ከጀመረች በኋላ ነበር፡፡ የቻር ሕይወት የአዳሪ ት/ቤቶች፣ የሕጻናት ማሳደጊያ ቦታዎችና አልፎ አልፎ መንገድ ላይ በሚኖርበት ጊዜ የመድረክ ትዕይንቶች ጋር የተያያዘ ነበር፡፡

 

የ17 ዓመት ዕድሜ እያለ በግማሽ ወገን ወንድሙ በዚያን ጊዜ የእንግሊዝ ቫውዲሺልድርጅት በፍሬድ ካርኖ ካምፓኒ ውስጥ ይሠራ ነበርና ቦ አገኝለት፡፡

 

እስከ 1913 ዓ.ም ድረስ አጫጭር የኩምክና ተዕይንቶች በማቅረብ ከካርኖ ጋር ቆይቷል፡፡ ማክ ሌኒት የኪስቶኖች ስላፕ ስቲክ አቅራቢ በኒውየርክ ከተማ ውስጥ ቻፕሊን ከካርኖ ጋር ሲሰራ ያቀረበውን ትዕይነት ተመለከተና የኪስቶን ካምፓኒ ለሚያዘጋጃቸው ፊልሞች ውል ተዋዋለ፡፡ ይህ የሆነው ከሚያዚያ ወር 1913 ዓ.ም ጀምሮ በሳምነት 150 ዶላር እየተከፈለው ለመስራት ነው፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላ ወደ መድረክ አልተመለሰም፡፡

 

ቻፕሊንም ዝነኛ አለባበሱ ላይ ደረሰ፡፡ የፈረሰ እሽቅድድም ባርኔጣ፣ ጠበብያለ የሴት ኮት፣ ባጊ ሱሪና ወደ ፊት ቮል ያለ ጫማ ሪዝ እና ከዘራ በሳምንት ሁለት ፊልሞች እየሰራ ቢያወጣም ገና ከጅምሩ በግሩም ሁኔታ የተዋጣላቸው ነበሩ፡፡ ብዙም ሳይቆይ የራሱን ፊልም እንዲያዘጋጅ ተፈቀደለት፡፡ ደሞዙም በሳምነት ወደ 1.250 ዶላር አደገ፡፡  

 

ከሁለት ዓመታት በኋላም በጊዜያችን ትል ከሆኑት ሁለት ሌሎች ተዋንያን ሜሪ ፔክፎርድ እና ዳግላስ ፊየርባንክስ እና የፊልም አዘጋጁ ዲ ደብሊው ግሪፊትዝ ጋር በመሆን የናይትድ አርቲስትስ የተባለውን የፊልም ድርጅት ሲመሰርቱ የየራሳቸውን ፊል እያቀረቡ ማሰራጨት እንዲያስችላቸው ነበር፡፡ /1923/ /የሃይማኖት ጉዞ/ ሰርቶ የመጀመሪያው ብሔራዊ ውል ሲጠናቀቅ በ1966 /የሆንግ ኮንግ አንደራሴ/ የሚለውን ለዩ ኒቨርሳል ድርጅት እስከሰራ ድረስ ለራሱ የፊልም ድርጅት ብቻ ነበር የሚያቀርበው፡፡

 

የቻፐሊን በዝና ደረጃ ወደ ላይ መመንጠቅ ከፊልም ታሪክ ሴራና ርዕስ ይልቅ የፊልም አሻሻጥ ስራው በመሪው ተዋናይ ታዋቂነት አየሆነ መምጣቱ የማይናቅ አስተዋጽኦ አድርጎለታል፡፡

 

የቻፕሊን የስክሪን ስብዕናው በሕዝቡ ዘንድ ተናፋቂ ተቀባይነት ከፔክ ፎርድ ፊየርባንክስና የሌሎችም ጋር ተዳምሮ መዋቅሩን ሊያጣናክረው ችሏል፡፡

 

የቻፕሊን የግል ሕይወት ማዕበል እንደበዛበት ባሕር ዓይነት ነበር፡፡ 4 ጊዜ አግብቷል፡፡ ሜልድሪድ ሐሪሰን /1918/ ሊታ ግሬይን /1924/ እና ፓውሌት ጎዳርድን /1936/ እና በ1943 የጸሐፊ ተውኔት ኤውጌኒ ኦ ኒልን ሴት ልጅ እና ኦ ኒልን አግብቷል፡፡

 

የመጀመሪያዎቹ ሁለት ፍቼዎች የጋዜጦችን የመጀመሪ ገጾች አጣበው ነበር፡፡ በ1944 ዓ.ም ፍርድ ቤት የአባትነት መብቱን ለማሳወቅ በተደረገበት ክስም እንዳዘው ነበር፡፡ በ1942 ዓ.ም ቻፕሊን ጀርመንን ለመውጋት በታቀደው ጦርነት በነበረው ፖለቲካዊ አቋም አሜሪካዊ ለመሆን እንዳልቻለ በመጠኑ ነቀፊታ ደርሶት ነበር፡፡

 

በ1947 የስራው /አቶ ቬርዶክስ/ በተሰኝው ፊልም የአሜሪካንና ሌሎችንም ፊልም ድርጅቶች አስቀጥቷል፡፡ ባለፉ ቀረጦች ከፖለቲካ ሰዎችና አንዳንደ የአምድ አዘጋጆች ጋር በማያያዝ የአሜሪካ መንግስት ተጽዕኖ ስላደረገበት በ1952 አሜሪካንን ለቆ ሄዷል፡፡ ወደ አሜሬካን ተመልሶ የመግባት መብቱ በአሜሪካን የፍትህ መምሪያ በኩል እንደሚያስጠይቀው ተነግሮት በ1953 እንደገና የመግቢያ ቪዛውን ጄኔቫ ውስጥ አግኝቷል፡፡ ቻፕሊንገና ቤተሰቦቹም ከዚህ በኋላ በኮርሲየር ሱር ሼሼይ ስዊዘርላንድ ውስጥ ኖሯል፡፡

 

በ1957 /በኒውየርክ ውስጥ ያለ ንጉስ/ በለን ደን ውስጥ አቅርቦታል፡፡ ይህ ፊልም የኮሚኒስቶ ሃሳብ እንዳለው ተደርጎ በመወሰዱ አዲስ ነቀፋ ቢስነዘርበትም ቻፕሊን አልተቀበለው፡፡ በ1966 የሆንግ ኮንጓ እንደራሴ የተሰኝውን በመጻፍ በመዘጋጀትና ለቅጽበት በቀወነበትና ፊልም ዋነኞቹ ተዋናዮች ማርሎን ብራንዶና ሶፊያ ሎሬንስ ተጫወተዋል፡፡ በ1972 ከፊልስ ሰነ ጥበብና ሳይንስ ልዬ ሽልማት ለመቀበል ወደ አሜሪካን ተመልሷል፡፡ ታህሳስ 25 1977 ዓ.ም ከሴዮር ሼሼይ ስዌዘርላንድ ውስጥ አርፏል፡፡ ነፍስ ይማር፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

አርሰን ዌልስ

አርሰን ዌልስ እ.ኤ.አ ሚያዝያ 6/1915 በኬኖቫ፣ ዊስኮንሲን በምትባለው ከተማ በአሜሪካን ሀገር ውስጥ ተወለደ፡፡ የፊልም ጽሁፍ፣ ፀሐፊ፣ አቅራቢ፣ አዘጋጅና ተዋናይ የሆነው ባለሙያ ፈጠራዊ ትረካ ዘዴዎቹና የፎቶግራፍ አጠቃቀሞ፣ ቴያትራዊ ብርሃን አፈነጣጠቁና ከዚህ ጋር የሚያያዙ ሙዚቃዎች፣ ኬን የተባለው ዜጋ የሚለውን ፊልም በ1941 ዓ.ም ሲሰራ ያቀናጃቸው ነገሮ ነበሩ፡፡ ይህንን ፊልም ጽፎ አቅርቦ ካዘጋጀ በኋላ ራሱ በተዋናይነት ተጫውቶታል፡፡ ድንቆቹ አምበርሰኖች በ1942 የተሰራውንም የጻፈው ያዘጋጀውና ያቀረበው እራሱ ሲሆን እነዚህ ሁለት ፊልሞ በሲኒማው ዓለም ባለው የስነ ጥበብ ዘርፍ እጅግ ልዩ ግምት የሚሰጣቸው ነበሩ፡፡

 

ፒያኖ ተጫዋች ከነበረቸው እናቁ አርሰን ዌልስ ፒያኖና ቫዮሊን መጫወት አጠና፡፡ የ6 ዓመት ልጅ እያለ ወላጆች ተለያዩ፡፡ በ8 ዓመት ዕድሜው ደግሞ እናቱ አረፈች፡፡ በ13 ዓመት ዕድሜው በሞት በተለየው ዝነኛ የፈጠራ ሰውና የፈብሪካ ባለቤት በኩል ተዋናዮችና የስፖርት ሰዎ ጋር ተገናኝ፡፡ በ11 ዓመት ዕድሜው ዓለምን እየተዘዋወረ ጎብኝቷል፡፡ ኢሊዬኒስ ውድስቶክ በሚገኝው የቶድ ት/ቤት በሚባለው የወንዶች ልጆች የሚማሩት ገብቶ በግድየለሽነት ቢክታተልም ስለቲያትር በዛያለ ዕውቀትን ቀስሟል፡፡ አየርላንድ ሄዶ በአህያ የሚጎት ጋሪ ጉዞ በሚል የቀለም ቅብ ከመስራትና ቃለ ዘጋቢ ከመሆኑ በፊት በቼካጎ ውስጥ በሚገኝው የስነ ጥበብ ኢንስቲት የት ጥልቅ የሆነ ጥናት አካሄዷል፡፡

 

የትውና መጀመሪያ ሥራውም በ1931 ዓ.ም የበልግ ወራት ዲብሊን ውስጥ በሚገኝው፡፡ ጌት ቲያትር ቤት ሐምሌትን ሆኖ ነበር የተጫወተው፡፡ ዌልስ በጌትና አቤይ ተዋናዮች ጋር የትወና ሥራውን አያካሄደ አየርላንድ ውስጥ ቆይቷል ወደ አሜሪካን ከተመለሰም በኋላ ከካትሪን ኮርኔል ካምፓኒ ጋር ከ1933-34 ዓ.ም ድረስ በሮሜዎና ዡልየት እንደ ሜርኩቺዮ፣ በካንዲዳ ውስጥ እንደ ማርች ባንክስ እና እንደ ኦክታሺያስ ባሬት በዊምፓል ጎዳዎ ላይ የሚገኙት የባሬት ቤተሰቦች ቴያትሮ ውስጥ በመጫወት ትዟዙሯል፡፡

 

በ1934 ዓ.ም ውስጥ በውድ ስቶክ የቴያትር ፌስቲቫል በማዘጋጀት እንደ ሐምሌት ሆኖ ሲሰራ በኒውዮርክ የመጀመሪያ ሥራው ደግሞ በዛው ዓ.ም ታህሳስ ወር ላይ ሮሜዎና ዡልየት ሆኖ ነበር፡፡ በ1936 ዓ.ም በፌዴራል ቴያትር ፕሮጀክት አንዱ ክፍል በሆነው በኔግሮ ሕዚቦች ቴያትር ማክቤዝ ቴያትርን ሙሉ በሙሉ በቁጥር አሜሪካውያን ተዋንያኖች ያዘጋጀው አርስን ዌልስ ነው፡፡

 

በ1937 ሜርኩሪ ቴያትርን መሠረት ይህም ቴያትር ቤት የሼክስፒሩን ጁሊያስ ቄሳር የታወቀውን ዘመናዊ አለባበስ ስልት ያቀረበ ነው፡፡

 

የራድዬ ፕሮግራም ሥራውን በ1934 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ የገጣሚ አርቺባልድ ማክሊይቨን የግጥም ተውኔት አዛምዶ በማቅረብ ጀመረ፡፡ በ1934-35 ዓ.ም የጊዜ ጉዞ የሚሉትን ተከታታይ ዜናዎችና በተከታታይ በቀረበው ጥላው በሚበለው የወንጀል ሚጥር ሥር የለምንት ክራንስተን ባሕርይ ለብሶ አቅርቧል፡፡ በ1938 የሜርኩሪ ተዋናዮች ከተለያዩ ዝነኛ ጽሑፎች የተዛመዱ ድርሰቶን በተከታታይ ማቅረብ ቀጠሎ፡፡ የዓለማት ጦርነት በሚለው የዌልስ ፕሮራም በመገናኛ ብዙሃን መለፈፍ ያለበት ጽሁፍ በግል ባጭ ለማስመሰል የተቀዳውን ከማርስ ፕላኔት ላይ ወራሪዎች በኒው ጄርሲ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የሜርኩሪ ተዋናዮች ሲያቀርቡት በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ማሰመሰያ ግልባጭ እንጂ እውነት እንደልሆነ ሳይረጉት ቀርተው በፍርሃት ተርበድብደው ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታም በብሔራዊ ደረጃ ጥላቻንም አትርፈዋል፡፡

 

በ1947 ዓ.ም ከሻንጋይ የመጣችዋ ሴት እና ማክቤዝ የሚሉትን ፊልሞች አዘጋጅቶ በተዋናይነት ሰርቶበቸዋል፡፡ ብዙ ዓመታት አውሮፓ ውስጥ ከዚህ በኋላ ኖሯል፡፡ ኦቴሎን በ1952፣ ሚ/ር አርካዲንን በ1955 ዓ.ም በማዘጋጀት በተዋናይነት የተሣተፈውና ያቀረበው እዛው አውሮፓ ውስጥ ነበር፡፡ በ1958 ሆሊውድ ተመልሶ ሰይጣን የዳሰሰው የሚለውን ፊልም የተጫወተውና ያዘጋጀው እራሱ ነው፡፡ የል ፕሮቼን በ1962 ዓ.ም ዘትሪያል /ፍርዱ/ እና ካምፓናዳስ አሜዲያኖቼ /የሊሊት ደውሎች/ በሚለው በ1966 አሁንም አውሮፓ ውስጥ ነበር ያዘጋጃቸው፡፡ በ1975 ለማስመሰያ የሚለውን አዲስ ስራ ጽፎ፣ አዘጋጅቶ ተውኖበታል፡፡ በ1982 ዓ.ም ደግሞ ቢራቢሮ የተኝውን ፊልም አዘጋጅቷል፡፡

 

አርስን ዌልስ እንደ ተዋናይ ሆኖም በብዙ ፊልሞች ላይ ተካፍሏል፡፡ ከነዚህም ውስጥ፣ ጄን ኤየር /1944/፣ /ሶስተኛው ሰው/ /1949/ /1958/ /በጣም ረዥ     ሙ በጋ/ /1959/ /በ1966/ /ለሁሉም ወራት የሚሆን ሰው/ /1970/ /22 ቁጥር ያዘ/ እና /1978/ /የተጠላለፈ ጎራዴዎ/ ይገኙበታል፡፡

 

በኋላ ላይ ከስራቸው የመድረክ ስራዎም ኦቴሎ /ለንደን 1951/ እና ንጉስ ሌር /ኒው ዮርክ ከተማ 1956/ ጥየቀሳሉ፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ሲልቨስተር ስታሎን

በ1985 በአሜሪካን አገር ባሉ የሲኒማ ቤቶች በሼትናም ውስጥ የተደረገውን ጦርነት አሜሪካኖች እንደገና ተዋገተውበት አሸንፈዋል፡፡ ለዚህ ዓለማም የተመረጠው ተዋናይ ደራሲው ሲልቨርተር ስታሎን ነበር፡፡ ጆን ራምቦ በሚል ስያሜ የቬትናም ጦረኛ በመሆን የመጀመሪያው ደም ክፍል ሁለት ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ የጠላት ወታደሮችን እየተኮሰ ግዳይ በመጣል ከቬትናም እስር ቤቶች ውስጥ የአሜሪካንን ወታደሮች ነጻ ሲያወጣ ያሳያል፡፡

 

የቬየትናም ጦርነትን ተመልካቹ እንደገና እንዲያስበው የሚደርገው ይህ ፊልም መሰሎች ፊልሞች ካስገኙት በበለጠ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ብቻ የበዛ ብር አስገብቷል፡፡ ራምቦን ከ1920ዎቹና 1930ዎቹ የናዚ ሲኒማ የሚወዳድሩት ነቃፊዎች፣ ትችት ሰንዛሪዎች ቢኖሩም የተሳካ ውጤት ላይ ደርሷል፡፡ ስታሎንንም ይህ ትችት አልረበሸውም፡፡ እ ፖለቲከኛ አይደለሁም፡፡ ለአሜሪካን ተሸናፊዜጎች ነው የቆምኩት፡፡ ይላል አስተያየቱን ሲሰጥ፡፡

 

ስታሎን በ1975 የባንክ ደብተሩ ላይ 106 ዶላር ሲነበብ፣ ያረገዘች ሚስቱና የተራበ ውሻው በቤት ውስጥ እያሉ የቤት ኪራዩ ያልተከፈለው ቤት አከራይ ዙሪያውን ሲያንዝብብበት ከአሜሪካን ተራ ዜጎች መሐል አንዱ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ነው ሮኪን ለመጻፍ ብዕሩን ከወረቀት ያዋሃደው፡፡ የመጀመሪያውን ጽሑፍ በሶስት ቀን ተኩል ጽፎ ካበቃ በኋላ የፊልም ጽሑፍ አዘጋጅቶ እንደ ቻርሊ ቻፕሊንና ኦርሰን ዌልስ በፊልም ጽሑፍና ጥራት በድንቅ ተዋናይነት ለኦስር ተሸላሚነት መታጨት በቃ፡፡ ሮኪ የሆሊውድ የበታች ሰራተኞች ባህርይ ቢላበስም፣ ለስላሳ ልቡና ድህነት የተጫነው ቦክሰኛ ነገር ግን ሳይጠበቅ በከፍተኛ ደረጃ ለመቧቀስ ዕድል የገጠመው ባህርይ አድርጎ ስለጻፈው ለዚህ ባህርይ እንዲህ ዓይነት ኃይልና ትኩስነተት ስለ ተጎናጸፈው ሲልቨስተር ስታሎን በሃያሲን ተሞግሷል፡፡ በኋላም ላይ ከሮኪ ክፍል ሁለት /1979/፣ ሮኪ ክፍል ሶስት /1982/ እና ሮኪ ክፍል አራት /1985/ የፊልም አዘጋጅነትን ድርሻ አራ ተወጥቶታል፡፡

 

በ1982 ለመጀመሪያ ደም የጆንራምቦን ባህርይ ይዞ ሲጣወት የፊልሙም ረዳት ፀሐፊም ነበር፡፡ የፊልሙ ትኩረትም በአንድ ያልተደነቀ የጦር ጀግና በአሬጎን ከተማ ዝቃጭ ሕይወት ላይ ሲሆን ስታሎን ራምቦን ሆኖ የተጫወተው ተልጎምጓሚ፣ በማርሎ ብራንዶና በአርኖልድ ስቸዋዜንገር መካከል የሚገኝ ጡንትኛ ሆኖ ነው፡፡

 

እ.ኤ.አ ሐምሌ 6 1964 በኒው ዮርክ ከተማ የተወለደው ስታሎን ታማሚ ልጅ ነበር፡፡ ነገር ገን ወደ ጎርምስና ሲጠጋም የክብደት ማንሳት ስፖርትን ያዘውትር ነበር፡፡ በሚያሚ ዬኒቨርስቲ ውስጥ ድራማ ሲያጠና ለጊዜው የወደፊት ዕድሉ አልታየውም፡፡ በ1985 መጨረሻ ቀዝቃዛ ጦርነት በእቡጃዲ ግርግር ላይ መዋጋቱን ብዙሃኑንም አሜሪካውያን ከተሰደደው የሶቭየት ቦክሰኛ በሮኪ ክፍል አራት ላይ እንደሚያድን ማንስ ከቶ ያስበዋል?

 

የሮኪ መንገድ

ለትንሽ ጊዜ የመጨረሻው መጋረጃ ተቋርቦ ነበር፡፡ ሲልቨስተር ስታሎን ረኪ ባልቦአን ለመግደልና ለማስወገድ ያስበበት ጊዜ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሮኪ የራሱን ባህርይ ሊነጥቀው ትንሽ ነው የቀረው፡፡

 

ማለቴ አለ በቅርቡ ስታሎን አዋቂዎች የተማሩ ሰዎች እኔን ልክ እንደሮኪ አድርገው ይመለከተኛል፡፡ በአሜሪካን ምክር ቤት ጎብኝት ላይ አያለሁ ኤድየርድ ኬኔዲ አይተኝ የተናገረው ቃል ታዲያስ ሮኪ የምል ነው፡፡

 

ሮኪ 5 የፊልም ቀረጻው ጊዜ እንደደረሰ ስታሎን ይህን በዱላ የሰከረ ባህርይ ሊገድል ወጥቷል፡፡

 

ከሌሎች በሙሉ ይኽኛው ፊልም የኀዘን ድባብ ያጠላበት ነው ሮኪ ጊዜው አልፎበታል እንዲሞት ክፍልጋው፡፡ የፊልም አቅራቢዎች ግን አልፈለጉም፡፡ ብሏል ስታሎን፡፡ እናም ተሳክቶላቸዋል፡፡ ሽማግሌው ሮኪ ሪንግ ላይ ተወግሮና ደህይቶም እንደገና ለመቧቀስ ሌላ የፀሐይ ብርሃንን ይኖራል፡፡

 

ሮኪ 5 እንደሌሎች አይደለም ብሎ ስታሎን የተናገረው እውነቱን አልነበረም፡፡ ሮኪ 5 ላይ ያለው ቧክሰኛ ያው የቀድሞው ነው፡፡

 

ስታሎን በጓደኞች ወደ ትክክለኛ ውሳኔ በደመ ነፍስ የሚጓዝ የንግድ ሰው ነው የሚባለው፡፡ በዚህም ፊልም ሮኪን በፊት ወደ ነበረበት ደቡብ ፍላይልፊያ መንግዶች ይወስደዋል ምናልባትም የተጋደመ ስጋ በቦክስ እየመታ ይለማመድ ወደ ነበረበት ኮካንዳ ቤት፡፡ እንደሁል ጊዜውም ስታሎን የፊልም ጽሁፏን ጽፎታል፡፡ ዝርዝር ሁኔታውን ግን ከልቡ ይጫወታዋል፡፡

 

ሰማህ ወይ አለ ስታሎን ስለሉካንደ ቤቱ የፊልሙ ቅንጫቢ ምን እንደሚመስል፡፡ ሲጠይቅ ያንንማ ሰባት ብርሃን ከስክሰህ የምታየው ይሆናል፡፡ በማለት መልሷል፡፡ /በዚህ አጋጣሚም የፊልም መግቢያ ዋጋ በአሜሪካ ያወቅን አይመስላችሁም?/

 

ታሊያ ቫየርን የሮኪን ወድ ፍቅር አድሪያናን ሆኖ እንድትጫወት እንደገና አምጥቷታል፡፡ በርት ያንግንም እንደሚስት ወንድም ፖሉን ሆኖ እንዲሰራ ነገር ግን ሮኪን በማዘጋጀት ኦካር የተሸለመደውንና ሮኪ ፊልሙንም በጥሩ ፊልምነት ለኦስካር እንዲበቃ የረዳው የፊልም አዘጋጅ ጆን አቪልድሰንን ማምጣቱ ከሁሉም በላይ አያጠያይቅም፡፡ ሮኪ 5 ሮኪ መጥቶ ሁኔታ ውስጥ ተዘፍቆ ይጀምራል፡፡ የሻምፒዮንነት ዝናተነጥቋል፡፡ ገንዘቡም እድሜ ለነዚያ አጭበርባሪ የሂሳብ ሠራተኞች ምንም አልተረፈውም፡፡ ወደደቡብ ፊላዴልፊያም ከመሠረቱ ወደ ነበረበት ሄዶ ቁስሉን ያጠጋል /ያክማል/፡፡

 

ከእንዲሪያን መላ በመነሳትም ሮኪ ካለበት የሸንፈት ገዳም መወጣጫ ያገኛል፡፡ ጥሩ አስተሳሰብ ያለውና ከዚህ በፊት የሚያውቀውን ሰው የሚያስታወስበት ግጣት ቢክ ሰኞ ጋር ይገናኛል፡፡

 

ይህ ወጣት ቦክሰኛ የሮኪ ሆኖ የሚሰራውን ባህርይ ሆኖ የሚጣወተው የጆን ዋይን የልጅ ልጆች ጋር ዝምድና ያለው ቶሚ ማሪሰን ነው፡፡ በእርግ የሮኪ ፊልም ስለሆነ ብዙ የሪንግ ላይ እንቅስቃሴዎ ይታያሉ፡፡ ከጆፕ ዌይንም ጋር ባለው ዝምድናም ወጣቱ ማሪሰን ለቡቅሻው በፍላጎ ነው የሚሄደው፡፡

 

ሆሊውድ ውስጥ እንዳሉ ሰዎች በሉስ አንጀለስ ፍርድ ቤት ሞሪሰንን እንደ ሞቱት ከሆነ የአንድኛውን መንጋጋ በመስበር የሌላውን ዓይን በመጨናበስ ነበር፡፡ በትክክልም ከልብ በላይ የሆነ የመቧቀስ ፍላጎት አለው ያሰኛል፡፡

 

ሮኪ ጁኒየርን ሀኖ የሚጫወተው የ15 ዓመት ዕድሜ ያለው የስታሎን ልጅ ልጅ ሲሆን ከአባቱ ጋር ያለው ዝምድናም አደጋ ላይ እየሆነ እንደመጣም ተሰምቶታል፡፡

 

ስታሎን ሮኪን ወደነበረበት መመለሱን ደግፈውለታል የውስጥ አዋቂዎች፣ ይህ ነው ጆን አቪልድሰንንም የመለሰው ሁኔታ፡፡

 

የኦሪጅናል ጽሑፍ አባሮት ነበር፡፡ በጣም ጥሩ ነበር ገንዘቡን ሁሉ አጥቷል፡፡ መቧቀስ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ እናም ይሞታል፡፡ ለታሪኩ አስቀያሚ መዝጊያ ነበር የሆነው፡፡ ይላል ጆን አቪልድሰን ስለመጀመሪያው ጽሁ ሲናገር፡፡

 

እነኝህ ሰዎች ግን ምንድን ነው የሚያስቡ? ምናልባት እናወራ ስለነበረው ሮኪ ባልቦአ እንደሚውቅ ትገምታለቻችሁ?

 

አዎን የ ፈጠሩትስ እነሱ አይደሉ

 

 

 

 

 

 

 

ፍራንሲ ፎርድ ከፖሌ

ከሁሉም ይልቅ ትልቅ የሆነው ማፊያ እንደገና ለእይታ በቅቷል፡፡ የፍራን ሲስ ፎርድ ኮፖላ ያዘጋጀው የጡት አባት ክፍል 3 በሆነው ፊልም ዋና ባህርይ ዶል ሜካኤል ኮርሌዎኔ ነው፡፡

 

የዶን ሜካኤል የባሕርይ ድርሻ ደግሞ የሚጫወተው አሁንም አል ፖኪኖ ነው፡፡

 

ከየጡት አባት ክፍል 2 በኋላ ባሉ 15 ዓመታት ውስጥ ሙያው አጠያያቂ ሁኔታ ላይ ለደመረሰበት የፊልም አዘጋጅ ፍራንሲስ ኮፓላ ፓራማውንት የፊልም ካምፓሊ ከገንዘቡ 50 ሚሊዮን ዶላር ሰጥቶታል፡፡ ፍራንሲስኮፓላ በህዝብ ፊት ከዚህ ፊልም ሥራ አጁን ተጣጥቦ ትቶት ነበር፡፡ በ27 ሚሊዮን ዶላር ሊሰራው የሞከረው አንዱ ከልቤ በሚለው ሙዚቃዊ ፊልም ሳቢያ በደረሰበት ኪሳራና እስካሁን ባልተከፈለው የ8 ሚሊዮን ዶላር ዕዳ በካሊፎኒያ ወይም ምርት የተትረፈረፈበት ናፖ ሸለቆ ውስጥ ያለው የቤተሰቡ መኖሪያን አደጋ ላይ ጥሉታል፡፡

 

ይህ 800 ሚሊዮን በዶላር ገቢ ለፖራማውንት ድርጅቱ ያስገኝለትን የማፊያ ታሪክ ለመቀጠል የድርጅቱ ፕሬዘዳንት ፍራንክ ማንኩስ ጥርሰን ሲነክስ በፍራንሲስ ኮፖላም በኩል እሱ በፈለገው መንገድ ለማቅረብ ስምምነት አግኝቷል፡፡

 

ስቱዲዮውም በዚህ ሁኔታ ስለተስማማ ፍራንሲስ ኮፖሳና ማሪዮ ጉዞ /የመጽሐፍ ደራሲ ነው/ ለሳምንታት በሬኖ ሆቴል ውስጥ ተቀመጡ፡፡ ማሪዬ ጉዞ ወደ ዚህ አዲስ ዕቅድ የመጣው በሼክስፕር ድርሰቶች የተሞላ ጭንቅላት ይዞ ነበር፡፡ ለሳምንታት በቲትስ አንድሮ ኒከስ፣ ሮሚዎና ጁሊየት እና በተለይ ንጉስ ሊርን ተመስጦበት ነበር የከረመው፡፡

 

በቀማር ጨዋታዎች መካከል ባሉ እረፍቶች ጸሐፊውና የፊልም አዘጋጁ የፊልም ጽሁፉን አቅናበሩት፡፡ በፊልሙ ቀረጻ ወቅት እስከመጨረሻው ፍጹ ምስጢር ነበር፡፡ ሁሉም ሰው ሶስት ዓይነት አጨራረስ እንዳለውና በሶስቱም መጨረሻ ላይ ሚካኤል ኮርሌዎኔ እንደሚሞት ነበር፡፡

 

ለፍራንሲስ ኮፖላ ይህ ጽንሰ ሃሳብ ለአደጋ የሚገልት ግለት ነው የሚካኤል ኮርሌዎኔን ባህርይ በትክክል በመመርመር በየቱት አባት ላይ ያለው የስልን አያያዙ ከራሱ ሕይወት ማለትም ወይን የማምረት ሥራው የማምረቻ ስቱዲችና፣ የመጽሔት ክፍሉ እ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የሄደው የንብረት ግዛቱ ጋር አመሳስሎል፡፡ እስከ ተወሰነ ደረጃ ድረሰ እኔ ሚካኤልን ሆኛለሁ፡፡ ይላል የፊልም አዘጋጁ የጡት አባት ክፍል 3 ውስጥ ያለው ሚካኤል የሼክስፒርን ንጉስ ሊር ይመስለዋል ከላይ በኩል ሞት ሲጠራው ከወደ ሥር ደግሞ ግዛት ሲንሸራተትበትና ሲያመልጠው የሚያሳይ፡፡

 

ይህ የጡት አባት ክፍል 3 የተሰኝው ፊልም ተወዳጅነት የማያተርፍ ከሆነ የ52 ዓመት ዕድሜ ያለው የፈጠራ ሙያ ላይ ማተሚያ ማስጠንቀቂያ ደውሉን ያንቃጭላል፡፡ እናም በስቱዲዮውም በፊልም አዘጋጁም ላይ አደጋው ከፍተኛ ነው፡፡

 

የፊልም ቀረጻሥራው በሮምና በኒውዮርክ እንደቀጠለ በኮርሌዎኔ ታሪክ ላይ ያለው የፍራንሲስ ኮፖላ ጉም የሸፈነው እይታ እየጠራ መጣ፡፡ የፊልም ጽሁፉን እየደጋገመ ነበር የፃፈው፡፡ በፊልሙ ላይ የሚካኤልን ባህርይ ወክሎ የሚጫወተው ተዋናይ አል ፖኪኖም ስለዚህ ሁኔታ ይህ የፊልም ጽሁፍ ሳይሆን ጋዜጣ ነው፡፡ በማለት ቀልዷል፡፡ ተደጋግሞ የተጻፈው ጽሁፍ ግን ፈሩን ይዟል፡፡

 

ስትዲው ፊር ስለያዘ በሁኔታው ተደስቷል፡፡ ብዙ ገንዘብ ይፈጃል ተብሎ የተገመተውም ከተያዘለት በጀት በላይ 6 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው የጨረሰው /የና አስቴር ፊልም ያስወጣው 500 000 ብር እንደሆነ የተነበበ ጽሑፍ አለ/

 

የጡት አባት ክፍል 3 በብዙ መንገድ የአንድ ሰው ሲኒማ ብቻ አልነበረም፡፡ ተመልካች ፍርዳቸውን የሚሰጡበት የፍራንሲስ ፎርድ ኮፖላ ሕይወት ነው፡፡

 

ከሁሉም አቅጣጫ የሚኖረውን ሚዛን ፊልሙ እንደሚያልፍ ኮፖላ ሙሉ እምነት አለው፡፡ በፊልም ቀርጻው ወቅት ሲናገርም በጣም በጣም ድንቅ ይሆናል፡፡ እናም በሰው ልጅ መሀን ምን ማለት እንደሆነም የሚናገረው አለው፡፡ ይለናል፡፡

/እስካሁን ያልተባለ ይሆን እስቲ ይቅናው፡፡/

ማርሎን ብራንዶ

በሲኒማ ዓለም ውስጥ የወንድነትን ምሳሌነት ከያዘ ብዙ ጊዜያት አልፈዋል፡፡ ይህ ወሳኝ ችታው በተለያዩ ባሕርያትን /የጀግና/ ውክሎ በተጫወተባቸው ፊልሞች ተንፀባርቀዋል፡፡ በጡንቻ የተገባው ወጣት የተወለደው እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 3/1924 ዓ.ም ነው፡፡

 

ይህ ተዋናይ በተለይ ሁኔታ የፈጠራ ችታው በጊዜው ከነበሩት የሰፋ ነው፡፡ ለእያንዳንዱ ባሕርይ የማይደገም ዓይነት ሰውነት ይዘራበታል፡፡ ከሁሉም በላይ አርኪ ባህርይነቱን እንዲወመርበት ያደርገዋል፡፡

 

ከታወቀው የኒወዮርክ ተዋናዮቸ ስቱዲ በሌ ስትራስበርግና አሌያ ካዛን በሚመራው የስታኒስላብሰኪን ዘዴለትዋናይነት ፈጠራ በመቅሰም ጠንካራ ስብዕናውን ያደበረው ተዋናይ ማን ይሆን በማለት ሳታወጡ ሣታወርዱ አልቀረችሁም፡፡

 

ታዋቂው ስቱዲ ካፈራቸው ትልቅ የፈጠራ ችሎ ካላቸውና ከመጀመሪያዎቹ ከጀምስ ዲንና ፓል ኒውማን ጋር የሚጠቀሰው ማርሎን ብራንዶ ነው፡፡

 

ስለረዥሙና ፍሬያማ የፈጠራ መንገዱ፣ ከሌሎች ለየት የሚያደርጉ ባህርያቱ፣ የትውና ባለሙያነቱና የግሉ አተዋወን ስልቱ ለማወሳት ጊዜውም ቦታውም ሌጠብ ይችላል፡፡

 

ማርሎን ብራንዶ በልጅነቱ የስነጥበብ ዝንባሌ ባላት ጠንካራ እና ተቀርጿል፡፡ ከልጆቻ መካከል ሁለቱን ብቻ አልነበረም ወደ ተዋናይነት ሙያ እንዲገቡ የገፋፋቻቸው፣ ከእነሱም በፊት ወጣት የነበረውን ሔንሪ ፎንዳን ጭምር እንጂ፡፡ ያለዕድል ሆኖ ግን ይቼ ሴት ከጊዘ ወደ ጊዜ ከአልኮል መጠጥ ፍቅር በመቆራኝቷ የሚወዳትን ልጇን አሳዝናዋለች፡፡

 

በ1943 ዓ.ም ማረሎን ቤተሰቦችን ትቶ /ከአባቱ ጋር ከበፊትም እንደባዕድ ነበር የሚተያዩት/ ለብቻው በኒውዮርክ ውስጥ መኖር ጀመረ፡፡ ብቸኝነትና የመደነቅ ስሜ የሆዱን በሆዱ የሚይዝ ሚስጥራዊ ባሕርይ መፍጠር ቀጠሉሉ፡

 

ማርሎን በትኩረት የቴያትር ጥበብና ታጠና የነበረች ጆስሊን ከምትባለው አህቱ አካባቢ ማንዣበብ ጀመረ፡፡ የሕይወቱ መንገድ ይህ የስነ ጥበብ ዘርፍ መሆኑን ከልቡ ከማመኑ በፊት በተለያዩ ትንሽና ትልቅ ባህርያት ውስጥ ተካፍሏል፡፡

 

ጥገኝነት የማይፈልግ ነጻ መሆኑን ለማስመስከር                                                                                                                                                                                                                              ሲል በሚያሳየው እጅግ በጣም ስነስርዓት የሌላው ባህርይ ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት አስቸጋር አያደረገው መጣ፡፡ አያደር ግን አንድ ነገር ግልጽ ሆነ፡፡ እርግጠኛ ያልሆነ፣ በስነጥበቡም ዘርፍ ምንም ዓይነት ትምህርት የሌላው፣ ገን ራሱን በራሱ የትውና ችሎውን የፈጠረ ወጣት መሆኑ ታየ፡፡

 

በ1947 ዓዓም ነበር የዕድሉ በር የተከፈተለት የቴኒሲ ዊሊያምስ ፍላጎት የሚባለው ባቡር የተሰኝው ተውኔት ለመድረክ ሲቀርብ አዘጋጁ ኤሊያ ካዛን የስቴንሊ ኮቫልስኪን ባህርይ እንዲወክል ማርሎንን አጫው፡፡ የዚህ የቴያትር ታሪክ ውስጥ ቦታ ይዟል፡፡

 

እንዳነድ ሃያሲያን ማርሎን ከዚህ ቴያትር በኋላ የኮቫልስኪን ባህርይ ሆኖ የተጫወተውን ያልህ አይጫወትም፡፡ ብለውወአሰተያየት ሰጥተው ነበር፡፡ ይህም አሰተያየት ቢሆን ለዛ ድርሻው በጣም ትልቀ ግምት እንደሰጡት የሚስገነዝብ ነው፡፡ ቴሊሲ ዊሊያምስም ኤሊያ ካዛን ለዛ ባህርይ ድንቅ ሰው እንዳጨ መስክሮታል፡፡ ቆየት ብሎ የጻፈው ጭልፊት ወረደ የተባለው ተውኔት ማርሎንን በዋናው ገጽ ባህርይ ቦታ እንደሚጫወት ግምት ውስጥ በማስገባት ነበር እየተባለም ይነገራል፡፡ አዘጋጁም ሆነ ጸሐፊው ፈጽሞ የማይደክመውና ለፈጠራ ጥልቅ ትርጉም ያለው መሆኑ አስደንቋቸዋል፡፡

 

ሰማርሎን ብራንዶ ወደ ሲኒማ ዓም የገባው በ1949 ዓ.ም በፍሬድ ትሲሜን ወንዶች በሚለው ፊልም ነው፡፡ ይህ ፊልም እውነት ያዘለ ንፁህ፣ በዘገባዊ ስልት የተሰራ ሲሆን ስለሁለተኛው ዓለም ጦርነት አግራቸው ሽባ የሆኑ ጎዳተኞች ዕድል ያወሳል፡፡ በባህርይ ወህደት አሳማኝ ለመሆን ሲል ማርሎን እነዚህ ዓይነት የጠር ጉዳተኞች ያሉበት ሆስፒታል ውስጥ አንድ ወር ሙሉ አሳልፏል፡፡ በመጨረሻም ተማሚዎች እራሳቸው ከተዋናይነት ይልቅ በአግረ ሽባ በሽተኛነት ተቀበለውታል፡፡

 

በሁለተኛው ፊልሙ መጀመሪ መድረክ ላይ የሠራው የኤልያ ካዛንፍላጎ የሚባለው ባቡር በ1951 ዓ.ም በፊልም ሲቀርጽ የመድረክ ባልደረቦ እንዳሉ ሆነው በብላንሽ ድየቦኤ ባህርይ ዕውቋ እንግሊዛዊት ሺሺያን ሊስትሳተፍ ማርሎንም በሲኒማ ዕውቅናን ያገኝ በዚህ ጊዜ ነበር፡፡

 

ፍላጎት የሚለው ባቡር የሚለውን ፊልም ከሰሩት ውስጥ አራት ማርሎንን ጨምሮ ለኦስካር ሽልማት ቀርበው ነበር፡፡ 3ቱ ሽልማቱን ሲያገኙ ማርሎን በአፍሪካዊቷ ንግስት ፊልም የሚታወቀው በሃምፍሬይ ቦጋርት ተተክቷል፡፡

 

ይህ ቅስም ሊሰብር የሚል ዱላ በማርሎን ላይ ብዙ ችግር አልፈጠረምም፡ እንዲያውም ራሱን በደንብ ወደመቅረጽና የስራ ፍላጎቱን ለማጠንከር ረድቶታል፡፡

 

በሚቀጥለው ዓት በ1952 ዓ.ም ኤሚሊያዎሳፖታ በሚለው ታላቅ የሜክሲኖች መሪ የህይወት ታሪክ ላይ ዛዛንና ብራንዶ ሺሻ ሳፖታ በተባለው ፊልም ተገናኙ፡፡ ለስልን የመኖር ጥማት ባዕድ የሆነውን ጠንካራ የሜክሲኮን ንቅናቄ መሪ ባሕርይ ለመያዝ ወደር ያሌለው ጥረት አሳይቷል፡፡ ለኮስካር ሽልማትም ታጥቶ እንደገና በሌላ ሰው ተቀምቷል፡፡ ሽልማጹን የወሰደው ጌሪኩ ፕር የተባለው ተዋናይ ነበር፡፡

 

ተከታዩ በ1953 ዓ.ም የተሰራው ቹሊየስ ቄሳር የሚል ስያሜ ያለው የሼክስፒር ትራጄዲ ሲሆን በዕውቀቱ የሚታወቀው ጆሴፍ ማንኬቪች ነበር አዘጋጁ፡፡ ማዕሎን ብራንዶም የሚገርም ሐቀኝነት እና ለየት ያለ ስሜታዊነት የሚታይበተን የማረክ አንቆኒዮ ባሕርይ ይዞ ነብር፡፡ የፊልሙ አቅራቢ ግን የማርክ አንቶኒን ድርሻ በአፍንጫው ለሚነፈነፍ ተዋናይ ለመስጠት አያመነታ ስለነበር ማንኬቪችና ብራንዶ ቄሰሩን ማምገሻ የማርክ አንቶኒኝ ንግግር በክር ቀርፀው ለፊልሙ አቅራቢ ሲያስሙተ በደስታ የተቀነጠነተው /አቅራቢ የማርሎንን ድምጽ ባለማወቅ የሉወረንስ ኦሎቪዬን ወይም የጆን ጊልጉድ ድምጽ አድራጎ ወሰዶት ነበር፡፡/ በዚያን ጊዜ የሼክስፒር ድረሰቶቸን በጥሩ ሁኔታ ይጫወቱት የነበሩት ሎውራንስ ኦሊቪዮና ጆን ጊልጉድ የእንግሊዝ ተዋናዮች ነበሩሩ፡ ለማርክ አንቶኒ ባህርይ የተደረገው ጦርነት በነበራንዶ አሸናፊነት ሲዘጋ የፊልሙ ስራ ጥበባዊ ውጤትም አመርቂ ነበር፡፡

 

የሚቀጥሉት ሁለት ባሕርያት ማርሎን ብራንዶን ከወጣቱ ትውልድ በሚያወላዳ ሁኔታ ኮከብ ያደርጉት ናቸው፡፡ እነዚህም በላስሎ በኔዲክ ፊልም ያልተገራው 1953 ዓ.ም ጆኒን እን በ1954 ከኤሊያ ካዛን ጋር ሶስተኛውና የመጨረሻው ገንኙነታቸው በባሀር ዳርቻው ግንባር ቴሪ ማሉይን ሆኖ ነው፡፡

 

በመድረክና በስክሪኑ ዓም በጥቂት ዓመታት ስሙን በአንድ ጊዜ ታዋቂ አድርጎታል፡፡ በባህር ዳርቻው ግንባር ላይ በተጫወትም ችሎታው የኦስካር ተሸላሚ ለመሆን የበቃ ነው፡፡

 

ከዚያ በቀጠለው ህይወቱ ጋዜጠኖች በሚሰረጯቸው አሉባልታዎችም የመተውን ጭሎወን ሊጎዱት አልቻሉም፡፡ የበራንዶ ታዋቂነት ከችሎታው በላይ ተሰምቶት የአንድ አይነት ትወና ፈርአላስያዙውም፡፡ በጉሮሮው እየተሰነቀረ የሚወጣው ድምጽም በነዚህ ሁሉ ዓታት ለውጥ አላሳየም፡፡

 

የሚጫወታቸው ባህርያት ግን ተለዋወጡዋል፡፡ የመሰልችተ መረብ ውስጥ ሳለመግባት ብራንኮ የዓመፀኝነት ባሕርይ መጫወቱን ገለል አድርጎ ባህርያት መምረጥና መፈለጉን ታዋቂነትን አደጋ ላይ በመጣል ተያይዞታል፡፡ አዲስ የፈጠራ ሥራዎችን፣ የሼክስፒር ስራዎችን፣ የታሪክ፣ እስቂኝ፣ አልፎም ጃፓናዊ ባህርይ የችሎውን አድማስ የሚያስፈለትን ዓይነት ፊልም ሁሉ ይመርጣል፡፡

 

ማርሎን ብራንዶ በዚህ ጊዜ ነበር በጣም ድንቅ የሆኑትን አከራካሪ ባህርያትን ወክሎ በፊልም ሙያ ሥራው ታዋቂነትን ያተረፈው፡፡ ያም ሆኖ ግን ብራንዶ ኮከብ ነኝ የሚል ዓይነት ስሜት ተሰምቶት ራሱን ክፍሉ አያውቅም፡፡ ሁልጊዜም ራሱን ከዚንተርቪው፣ ከፎቶግራፍ ወክቢያ ሌሎች መሰል ሁኔታዎች ያርቃል፡፡ ስለዚህ ሲጠየቅ የሚመልሰው፡፡ አንድ  ተዋናይ ለተመልካች ያለበት ብቸኛ ግዴታ ቢኖር ተመልካችን አላማስቀየም ነው፡፡ ይላል፡፡ እናም ነጻ ሆኖ ከስቱዲዮ ስቱዲዮ እየተዘዋወረ በሱ ግምት ጥሩ የሆነ ማህበራዊ ጥያቄን ያዘለ ወይም ደግሞ እስካሁን የማይታወቅና ተዋናይ ያልተፈተነበት ዓይነት ባህርይ ይመርጣል፡፡ በዚህም ባልተጠበቀ ሁኔታም ስኬት ገጥሞታል፡፡ ለምሳሌ፡- እንደነገሩ የሚዘፍነው ብራንዶ ነገር ግን ፈጽሞ ዳንስ አይቸልም በአንድ ሙዚቃዊ ፊልም ውስጥ ጥሩ ነገር ይሰራል ብሎ የሚብቅ ይኖራል? ነገር ግን በጥሩ ሁኔታ ተዋጥወ3ለት እስከዛሬ ድረሰ በተለ ሁኔታ አዝናኝ ፊልም ሆኖ ቆይቷል፡፡

 

ብራዶን የፊልም አዘጋጆች ሁኔታ ብዙም የትወና ጥሙን ስላለረካለት ይመስላል፡፡ አንድ ዓይን አይነተቶች የሚል በሃይለኝነትና በወሲብ ሁኔታ ላይ የተመረኮዘ ፊልም አዘጋጅቷል፡፡ አንዳንድ ሃያሲያን ድፍረት የሞላበትና የጣም ረዥም የካው ቦር አፈታሪካ በማለት ተችተውታል፡፡

 

በአርተር ፔን የወንጀል ክትትሉ በሚለው ፊልም ውስጥ ብራንዶ የአንድ ትንሽ ከተማ የፖሊስ ሹም ሆኖ የህዝቡን ስነልቡና ለዘር ልዩነት ፍትህ በማስከበር ወሳኝ ባህርይ ሆኖ ችሎውን ሙሉ በሙሉ ተጠቅሞበታል፡፡ ለዚህ ፊልም ስኬት አብረውት የሰሩት ጄን ፎንዳ ሮበት ሬድፎርድ፣ ጀምስ ፎክስ፣ ሮበርት ዲዩቫል ይጠቀሳሉ፡፡

 

በ70ዎቹ ዓመታት የማርሎን ብራንዶ ወደ ነበረበት ደረጃ መመለስ ለሱም ሪፕብሊክ ለነጻነት በሚዋጉ ህዝቦች አካባቢ ባለው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የቅኝ ዘዥዎችን ፖለቲካ በማራመድ የእንግሊዝ ወኪል /ሹም/ ሆኖ መስራት ለችሎታው ክብር ያሰጠው ፕሮጀክት ነበር ማለት ይቻላል፡፡

 

በሄንሪ ጀምስ መጽሐፍ ላይ በመመርኪዝ ማይክል ዌነር ያዘጋጀው የምሽት ጉብኝዎች ላይም የመጥፎ ባህርይ ያለው ኩዊንትን ሆኖ ተከፍሏል፡፡

 

ፍራንሲስ ፎርደ ከፐላ ነበር የጡት አባት ላይ የማሪያ ሹም /ለጡረታ የደረሰ/ ሆኖ እንዲሰራ ብራንዶን የመረጠው፣ እንደ ዶን ኮርሌዎኔ ብራንዶ ወካኙን ግዳይ በሰው ፍቅር ወደ ተሞላ የቤተሰብ መሪ ቀይሮታል፡፡ በጉሮሮው የሚሰነቀረው ድምጽ ለዛውን እንደጠበቀ የወጣበት፣ ጥቃቅም ባሕር በደን ኮርሌዎኔ /ጠንካራው ሽማግሌ/ ግንባርና የእጅ እንቅስቃሴ ጎልቶ የታየበት ፊልም ነበር፡፡ ለዚህም ፊልም ትወና ሁለተኛውን የኦስካር ሽልማት ለማግኝት በቅቷል፡፡

 

በብራንዶ አጨዋወት የአንድ ሕይወት የመኖር ትግል ታሪክ፣ ተቀናቃኝን በምንም መንገድ ለማስወገድ ወደ ኋላ የማይባልበት ነው፡፡ በዚህ በጭካኔና በግድያ የተሞላ የህይወት ታሪክ ተዋናዩንም ሆነ ተመልካችን የአንድን ሽማግሌ ለህይወት ያለወን ፍላጎት መጋራት የሚያስችሏቸውን ጥቃቅን ባህርያት ተዋናይ እንዳይፈልጋቸው አላገዱትም፡፡

 

በጣም ትልቅ ገፀ ባህርይ ማርሎብራንዶ በህይወት ዘመኑ በሙሉ ከሰራቸው ፊልሞ ፖል - /በመካከለኛ ዕድሜ ያለ ሰው/ በፓሪስ የመጨረሻው ታንጎ ላይ ያለው ገፀ ባህርይ ነው፡፡ በርናንድ ቤርቶሎቼ ብራንዶን የተዋናይነት ችሎውን ብቻ ሳይሆን የሲኒማ ሕይወት ታሪኩንም የፖልን አስቸጋሪ ባህር በጥሩ መንገድ ለመግለጽ ስል ተጠቅሞበታል፡፡ በፊልሙ ውስጠ የፖል አገልጋይ የነበረቸው ሴት ስለፖል የፖሊስ ሪኮርድ ስታስተውስ ቦክሰኛ እንደነበረ ያውቃሉ አይደል? ከዚያም ተዋናይ ሆነ፣ በኋላም የቦንጎ ተጫዋች፣ የሜክሲኮ አመጸኞ፣ በጃፓን ጋዜጠኛ፣ ዙረት ያበዛል፣ ፈረንሳይኛ ይማራሉሉ፡ ስትል ትናገራለች፡፡ የፖልና የበራንዶ ባህርያት ቅንጅት በፊልም ሙያ የሚታወስ ትልቅ ነጥብ ሆኖ ይወሰዳል፡፡

 

የታዋቂው ተዋናይ ማርሎን ብራንዶ ፈጠራ በሙያው ዘርፍ ወደፊት መመንጠቅና ወደ ኋላ መቅረት በአብዛኛው የሚያሳየን የመጀመሪው አካባቢ ሕይወት ግንዛቤ እንደሰጠን በመገመትበሌላ ጊዜ ደግሞ የሌላ ተዋናይ ይዤ እስከምቀርብ ደህና ሁኑ፡፡ በቸር ይግጠመን አላለሁ፡፡

 

 

ደምስ በቀለ

ከአርዳይታ

 

 

አል ፓኪኖ

አሜሪካዊው የፊልም ተዋናይ አል ፓኪኖ በሀገራችን ላሉ የፊልም አፍቃሪዋች በጥሩ ሁኔታ የታወቀ ነው፡፡ በፊልም ውስጥ ብዙ ጊዜ ተሳታፊ ባይሆንም በተሰተፈባቸው ፊልሞች ላይ በሚጫወተው ባሕሪይ ተቀበይበነት አትርፋል ፡፡ ከተመልካቹም ከፊልም ባለሙያዋችም ፡፡

 

 በለፉት ትቂት ዓመታት ውስጥ በተሰራው . አመጻ . በተባለው የ18 ኛውን ክፍለ ዘመን የአሜሪካን እርስ በርስ ጦርነት ለማስታወስ በተዘገጀው ፊልም ላይ በትውልድ ስኪትላንዳዊ የሆነና እንደሌሎች ብዙ ሺህ ሰዋች በአዲሱ ዓለም ውስጥ በአጋጣሚ የወደቀ ባሕርይን ወክሎ ነው የሚጫወተው ፡፡

 

 ለአንድ የፈረንሳይ ፊልም መጽሄት ጋዜጤኛ አል ፓኪኖ  የሰጠውን አስተያየት በዚህ መልኩ አቀናብሬዋለሁና ተቀበሉኝ ፣

 

በሕጻንነቱ ፊልም ማየት ይወድ የነበረው ፓኪኖ እቤቱ ሲመለስ ያየውን ፊልም እንደገና ቤተሰቦቹ ጋር መጫወት ነበረበት፡፡ ወላጆቹ ሲለያዩም አባቱ ቤተሰቦቹ ጋር ተወስዳል ፡፡ በአባቱ ቤተሰቦችም ፊት ከፊልም ላይ የሚያያቸውን ገጸ ባህሪትና ቃለ ምልልሳቸውን ይደግመዋል፡፡ አያቶቹ ባበረታቱትበና ባሳቁለት ቁጥር የሱም ፍቅር እየጨመረና አዳዲስ ነገሮችን እያሳበና እያስታወሰ መጣ ፡፡አሁንም ቢሆን በዚያን ጊዜ ያያቸውብ ፎልሞች ከነቃለ ምልልሳው የስታውሳቸዋለወ ፡፡

 

 በዚህ ሁኔታ ያደገው አል ፓኪኖ ነበር በ30 ዓመቱ እድሜው ኮከብ የተሰኘው አል ፓኪኖ በሃያሲያን ላይ የራሱ አመለካከት አለው፡፡ ለአንድ ሙያ የሚነካን ነገር እራሱን ሳይነካው ሊያልፍ እንደሚችል ይስማዋለወ ፡፡ በአንድ የተወሰነ ድርሻ ላይ ቢሰራ ጋዜቶች የፈለጋቸውን ቢሉ በመትፎም ሁኔታ ቢሆን ተጽዕኖ ሊያደርጉብኝ ይችላሉ ብሎ ስሚያስብ ትኩረት አይሰጣቸውም ፡፡

 

. አመጻ. በተባለው ፊልም ውስት የ80 ዋቹ ኪከብ የሆነችው ናስታስያ ኪንስኪ /ካት ፔኝልና፣ቴስ በሚባሉት ፊልሞች እናስታውሳታለን ፡፡/ተሳታፊ ናት፡፡ ከአልፓኪኖ ጋር ያላቸው ቅርርብ ብዙም አያወላዳም፡፡ በጥሩ ሁኔታ አይተዋወቁም ፡፡ አንድ ላይ መስራት ሲጀምሩ ናስተስያ የሚሰጣትን ደርሻ በትክክል ተወጣዋለች ፡፡ እስከ ፊልሙ መጨረሻም አብረው ሰርተዋል ፡፡ አንዳንድ ቀን ለሰዓታት ይለማመዱ ነበር ፡፡ ምልልሶቹን ደጋግመዋቸዋል ፡፡ ለዚህም ትሩ ዘዴ ቀይሰው ነበር፡፡ ዘዴውም የበለተ እንዲተዋወቁና ዲርሻቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዲወጡት አድርጋቸዋል ፡፡

 

አል ፓኪኖ በተሰጠው ድርሻ ውስጥ  ጥልቀት ባለው መንገድ ይገባል ፡፡ ተመልካቾች ብዙ ጊዜ ወክሎ የሚሰራው ገጸ ባህርይ ከሱነቱ ጋር እደተዋሃደ ይነግሩለታል፡፡

 

. አመጻ. የሚባለው ፊልም የድርጊት ጊዜው በ18 ኛው ክፍለ ዘመን ቢሆንም ከአሁን ጊዜ ጋር ያለውን የዘመናት ልዪነት ለማሰወገድ አል ፓኪኖ በመሰለው መንገድ ተጠሟል፡፡ ለዚህም ስለዚያን ጊዜ ብዙ መጻሕፍትን አንብቧል በዚያን ጊዜ የነበሩትን ሰዋች አኗኗር ለመረዳት ወደ ለንደን ለፊልም ቀረጻው በሚሄድበት ጊዜ ብዙ እውነታዋችን አጥንቷል፡፡በዚያን ጊዜ የነበሩትን አልባሳት አይቷል ፡፡ ይዋጉበት የነበረውን መሳሪያ በእጅ ዳስሶታል ፡፡ የድሮው ዘመን እንግሊዝኛ ካሁኑ በጣም ይለይ ስለነበር የድሮውን የአነጋገር ዘይቤ አጥንቷል ከሱ ወክሎት የሚጫዋተውን ባሕርይ ልብስም ረዘም ላለ ጊዜ ለብሶት ተዟዙሯል ፡ጸጉሩን ወደ ኃላ ሸብ መድረጉን አልተወውም ፡፡ ምክንያቱም አለው፣ በተሰጠው በሕርይ አዕምሮው በሥራ ሲጠመድ ከዛ ብሕርይ ቶሎ ለመላቀቅ ይከብደዋል ፡፡ ይህ እንግዲህ ከመልኩና ውጪያዊ ሁኔታ ሳይቀር ነው፡፡ ቀስ በቀስ የባሕርይውን አንዳንድ ነገር መውረስ ይጀምራል ፡፡ ከባሕርዪ ጋር እየተለመደ ሲመጣም አንድ እስኪሆን ድረስ ጥረቱን አያቆምም ፡፡

 

አልፓኪኖ አንድ ገጽ ባሕርይን ወክሎ ሲጫወት እሱነቱ ይቀራል ይላሉ ፡፡ ከጧት እስከ ማታ እሱ እሱን አይደለም ፡፡ እሱ ገጸበሕርዩን ነው የሚሆነው፡፡ ተዋናይ መሳሪያ ነው፡፡

ሁልጊዜ ለስራ ዝግጁ የሚሆን መሳሪያ በማንኛውም ሰዓት የሚል አመለካከትም አለው፡፡

 

ኮፐሰለሰ የ. ጡት አባት . የተባለውን ታዋቂ ፊልሙን 3ኛ ክፍል ለመቅረጽ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተባራሪ ወሬ ይሰማል፡፡ እርስዋን ለ3 ኛው ክፍል ለመሳተፍ ቢጠራዋ በአንድ ወቅት እጅግ ዝነኛ ያደረገዋትን ባሕርይ ይጫወቱታል ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ሲመልስ ፡-በዚያን ጊዜ ኮፓላ ስለ ..ማይክል ..አንድንነጋገር ጠርቼ ስንነጋገር ለመስራት የተስማማሁባቸው በገሮች ብዙ ነበሩ ፡፡ አሁንም የሚኖረው ሁኔታ ከሙያ አኳያ ጥሩ ከሆነ በደስታ ያለማወላወል እስማማለሁ ፡፡ ይህ ሁሉ ግን ያልሆነ የወደፊት ዕቅድ ነው በማለት ገልጻል  ፡፡

 

 በሚቀጥለው ጹሁፌ ደግሞ አባት ላይ የዶን ኮርሌዋኔን ባሕሪይ ለብሶ ስለተጫወተው ማርሎ ብራንዶ የሞላችሁ አለኝ እስከዚያው ሰላሙን ለሁላችን ፡፡  

 

ደምስ በቀለ

ከአርዳይታ    

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የሮበርት ዶ ኒሮ የህይወት ጎዳና

እ.ኤ.አ. ነሐሴ 17 1944 ዓ.ም ከሰዓሊ ወላጆቹ በኒውዮርክ ውስ ተወለደ፡፡ በግሪንዊች መንደር መንገዶች ላይ ያደገው ይህ ልጅ በአሁኑ ጊዜ በፊልም ዓለም ዕውቅናን አግቷል፡፡

 

አባቱ ግማሽ ጎኑ ኢጣሊያዊ በሌላ ጎኑ አየርላንዳዊ ሲሆን የሚስላቸው ስዕሎች ተፈጥሮን በተመለከተ ነው፡፡ የናቱ ስዕሎች ደግሞ ከኢምፕሪሽኒስቶች /ዝርዝሩ ውስጥ የማይገቡ መሳጭ ሰዓሊያን/ ወገን ትመደባለች፡፡ እጅግ በጣም ቢደዱም በአንድ ጣራ ስር ለመኖር አልታደሉም፡፡

 

ሮነበርት ዶ ኒሮ በአስር ዓመት ዕድሜው ለወላጆች ተዋናይ መሆን እንደ ሚገልግ ገለፀ፡፡ በድራማ ት/ቤት ገብቶ ለሁለት ዓመታት ያህል ሕልሙን ዕውን ለማድረግ በትጋት ይሰራ ነበር፡፡

 

በ16 ዓመቱም ሊስትራስበርግና ስቴላ አድለር እንዲያስጠኑት የተዋናዮች ስቱዲዮ ውስጥ ተመዝግቦ እነዚህ ሰዎች በቴያትር ዓም ስላለው የኃላፊነት ስሜት አስልጠኑት፡፡ አንድን ባህርይ ድርሻ መጫወት ከመጀመሩ በፊት አስከተቻለው ድረስ ወደ ገፀ ባሕርይ እንዲቀርብ፣ ልክ እንደ ገፀባሕርይ እንዲራመድ፣ እንገቱን እንዲነቀንቅና ባሕርዩን ሆኖ እንዲያስብ ያህል ጥረት ማድረግ እንዳለበት አስተማሩ፡፡ እሱም ፍላጎት ስነበረው በውስጡ ለነዘህ ነገሮች ዝግጁ ነበርር፡ የልጅነት ጊዜው በግሪንዊች መንደር ዙረቱ ብዙ ሰዎች ጋር እንዲገናኝ አድርጎታል፡፡ ከዚያም የተለያዩ ገፀባሕርያትን ለምዷል፡፡

 

ሊስትራስበርግ ጋር ከወሰዳቸው ኮርሶች ከኋላ ሮነበርት ከ ኔሮ በብሮ ድዌይ መድረኮ ተጫውቷል፡፡ የቴያትር ሃያሲያን ብቅ ያለውን አዲስ ተሰጥኦ ያለውንም ወጣት በዚህ አጋጣም ዓይናቸውን ጥለውበታል፡፡

 

በ1965 ዓ.ም ሮበርት ዶ ኒሮ አውሮፓን ለማየት አሜሪካንን ለቆ ለ6 ወራት ለንደን፣ ፓሪስ፣ ሚቶንሔን፣ ቢየና፣ ዳብሮቭኒክ የግሪክን ባሕር ዳርቻዎች፣ ዛግሬቭ፣ ትሪየስት፣ ሮምን ተዟዙሮ ጎብኝቶል፡፡ በመጨረሻም ፓሪስ ተመልሶ የማሴን ካርኔን በማንዛታን ውስጥ ያሉ ሶስት ክፍሎች የሚለውን ለራሱ የመጀመሪው የሆነውን ፊልም ሠራ፡፡

 

ወደ ኒው ዮርክ እንደተመለሰም ብራየን ዶ ፓልማ እና ማርቴን ስኮር ሲዚ ባዘጋጁት ፊልም ላይ ተዋናይ እንዲሆንላቸው ጠየቁት፡፡

 

ስ እየታወቀ ሄደ፣ በዚህ ጊዜ ለነበሩት መጀመሪያ ዓመታት የሚኖረው በምስራቅ ብሩክሊን ነበር፡፡ በገንዘብ በኩል የነበረው ሁኔታ ያን ያህል አልነበረም፡፡ መኪና የለውም፡፡ የሚከፍለው ትንሽ ነው፡፡ ብዙ ቁጠባ ያደርግ ነበር፡፡ በኋላም ሆኖውድ ውስጥ ለመሥራት እንጂችል ተቀባይነት አገኝ፡፡

 

ጥሩ ለመስራት በሚያደርገው ጥረት ተዋናይ የኦስካር ሽልማት አገኝቷል፡፡ የታክሲ ሾፌር የሚለውን ፊልም ከመስራቱ በፊት ከኒውዮርክ ታክሲ ሾፌሮች ጋር ብዙ ጊዜን አሳልፏል፡፡ ያለበለዚያማ የነበርሱን የአነጋጋር ዘይቤ ስሜቶች እንዲት ሊረዳው ይችል ኖሯል፡፡ የጡት አባት ለተሰኝው ፊልምም የኮርሌዎኔ ቤተሰብ መኖሪያ ሰፈር አካባቢ ባለች ትንሽ የገጠር መንደር በመኖር ነዋሪዎቹ አካሄዳቸውን አነጋገራቸውን ቀልዶቻቸውን ሁሉ ይመለከት ነበር፡፡ አንዳንድ ስሜት የማይሰጡ አረፍተ ነገሮችንም በክር እየቀረጸ ማታ ማታ ልክ እንደነሱ ለመናገር ለማለማመድ የነሱን ዘዴ ለማወቅ ችሏል፡፡ ለእያንዳንዱ ፊልም በዚህ መንገድ ነው ራሱን የሚዘጋጀው፡፡ የሚሰጠው ባሕርይ እስኪዋሃደው ድረስ ብዙ ጥረትና ትግል ያደረጋል፡፡ ከራዝያሬንያት ቢ ፊልም ቀረጻ ከመጀመሩ በፊት ለአንድ ዓመት ያህል ተዘጋጅቶበታል፡፡ ከዋናው ባህርይ ጋር በአካል ለመመሳሳል 30 ኪ.ግ ያህል ክብደት ጨምሯል፡፡

 

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተሠራው ተዋናይ የሚሳተፍበት ፊልም እንደገና ለፍቅር መሸነፍ የሚል ሲሆን ገፀ ባሕርይ ያገባና ሁለት ወንዶ ልጆች ያለው የሕንጻ መሐንዲስ ሆኖ ዓይቷት በፍቅር የሚወድቅላት ተዋናይም አግብታ ልጆች ያልወለደች ገፀ ባሕርይ ናት፡፡ /የዚህችን ባሕርይ ወክላ የምትጫወተው ሴቷ ተዋናይ ሜሪል ስትሪፕ ናት/፡፡

 

ፊልሙ ስለሁለት ሰዎች የአንድ ወቅት ግንኙነት ያለው ከሕይወታቸው አብዛኛው ጊዜ ባለፈበት ወቅት ስለሚሆን ነገር ነው፡፡ሮበርት ዶ ኒሮ ስለፊልሙ ሲናገር በሕይወት ስሚያጋጥሙ ችግሮች ነው፡፡ የራስዎን ሕይወት በአካባቢዎ እንዳለ ማንኛውም ሰው ሳይታሰብ ልጅቷን ያገኟታል፡፡ እና ሁሉም ነገር ባልተጠበቀው መንገድ ይሄዳል፡፡ ፊልሙ ስአውነተኛው ትልቅ ፍቅር ማለትም መሰናክልዎ ጊዜያዊ ስምምነትም ስለማያግደው ትልቅ ፍቅር ነው የማኛየውን ዓይነት አውነት ፍቅር፣ ፍትህ፣ በስክሪንና በመድረክ ላይ ስመስክር የአደርካታችን ጥልቀት ሊለካ ይችል ይሆን? ደም እስቲ በሌላ ጊዜ በሰላም ያገናኝን፡፡

 

የናንተው ደምስ በቀለ

እርዳይታ

 

የጄፍ ቻንድለር ሚስጥራዊ አሟሟት

ገዘፍ ያለ፣ መልከ መልካም፣ ድምፀ ጎርናና የ42 ዓመት ጎልማሳ ነው፡፡ አሟሟቱ ሲሰማ ዓለም ተደናግጧል፡፡ ማንም ቢሆን ይሞታል ብሎ አልጠበቀም አሟሟቱንም መንም ሊረዳው አይችልም፡፡ ለመጨረስ ከነበረው ጉጉት ያለውን ጎልበት ሁሉ የጀመረው ሪልም ላይ ስለዋለው የሚሉ በሌላ በኩል ደግሞ በሆስፒታል ውስጥ የተሰጠው እንክብካቤ ማነስ ለሞት እንደበቃው በአሎባልታ መልክ ይሰማል፡፡

 

ቻንድለር በብሩክሊን የድሆች መንደር የተወለደ እናም ለሆሊውድ የተዋናይነት ሙያ እንደሚቀናው ምን ጊዜም ቢሆን የሚያስብ ነገር ግን በጣም ረዥም ጊዜ ሶስት ዓመት መውሰዱ /ተደናቂ ለመሆን የፈጀበት ጊዜ/ የሚስገርመው ድንቅ ሰው ነበር፡፡

 

የታይፓወር ዓይነት ቁንጅና ከወንዳወንድነት ገጽታ ይል ተመራጭ ባልሆነበት ጊዜ ወደፊልም ዓለም መቀላቀሉ በጅቶታል፡፡ ወደ ጉርምስናው ዓም እየገባ ሲሄድ ነበር የፀጉሩ ቀል ወደ ግራጫነት መቀየር የጀመረው፡፡ በመኪና አደጋም ምክንያት ፊቱ ላይ ጠባሳ ይታያል፡፡ ስመልክ በተነሳ ቁጥርም ጆን ዌይንም ቢሆን እኮ ቆንጆ አይደለም፡፡ በማለት ለተነሳው ርዕስ አልባት ያበጅለታል፡፡

/ሰባራው ቀስት/. በሚለው ፊልም ላይ በግዙፉ ጡንቻማ ሰውነቱ ስክሪኑን ይሞላዋል፡፡ ኪቺስ የሚባለው የቀጥ ህንዶች መሪ ባሕሪይን በመወከል ነው የተጫወተው ፡፡ በዚህም ተደናቂነትን አትርፏል ፡፡ በኢሊኖይስ በሚገኝ ካምፓኒ ውስጥ ማርጆሊ ሆሼልን አግብቷት ከ14 ዓመታት የትዳር ዘመንት ሁለት ሴቶች ልጆች በኃላ በ1960 ፊቺያቸውን አጽድቀዋል ፡፡ ይህቺው የቀድሞዋ ሚስቱ ከወላጆቹና ከሚወዱት ሰዋች ጋር ሆና ሞት ህይወቱን እስከሚነጥቃት ድረስ ከጎኑ አልተለየችም ፡፡ የሱ ጸሃፊ ላውራ እኒህ መሆን ፈልገናል፡፡ ብላለች፡፡

 

ቬይላ ግራሐም የተባለችው ጋዜጠኛም ቃለ መጠየቅ አድርጋለት .. ያፉትን በ40 ዓመቴ ውስጥ የነበሩትን ውጥንቅቶች ለማስተካከል እየሞከርኩ ነው፡፡ አሁን 42 ዓመቴ ቢሆንም በሁለት ዓመት ያነስኩ መስሎ ይሰማኛል፡፡ቀልጣፋ የሆነኩ ይመስለኛል..ብሏታል ፡፡

 

ጃፍ ቻንድለር በመጨረሻ የተጫወተበትን                              / የሜሪል ዘራፊዋች / ያዘጋጀው ሚልተን ስፔርሊንግም ..ግዙፍና ጠንካራ፣በአቋሙ ኩራት የሚሰማውና በፊልም ላይ ለሚያጋጥሙት አስቸጋሪ ድርሻዋች ሌላ ሊደበል /ከሱ ጋር ተማስሎ አስቸጋሪውን ክፍል የሚሰራ ተዋናይ / የማይፈልግ ነበር ፡፡ .. በማለት ሰለጄፍ የሚሰማውን ገልጻል ፡፡

 

በፊልፒንስ ውስጥ በነበረው የ10 ሳምንታት ቆይታው ጀርባውን እያመመው በጫካ ውስጥ እየተሸለከለ፣ ተራራዋችን እየወጣ፣ በረግረግ ቦታዋች ላይ እየቀዘፈ ሕመሙ ማታ ላይ ሲጠናበት በክላርክ አየር ኃይል ሰፈር ሆስፒታል ተኝቶ ሌሊቱን ያሳልፍ ነበር፡፡ የጀርባው አጥንት ነርቮቸ እንዲደነዝዙና ሥራ መስራቱን እንዲቀጥል መርፌ ይወጋ ነበር፡፡ በሚዝያ ወር ላይ ሆሊውድ ውስጥ ሆስፒታል ገባ፡፡ ቀዶ ጥገና ተካሄደ እናም ከአምስት ቀናት በኋላ የወገብ መድማት ተከተል፡፡ 7፡30 ሠዓት የፈጀ ቀዶ ጥጋና ተደረገ፡፡ ከብዙ ቀናት በኋላም ቻንድለር ቸስጊ ሁኔታ ላይ ተመዝግቦ ቆይቶም እያገገመ መስሎ ታየ፡፡ ሚያዝያ 27 መድማቱ ጀምሮ ሌላ ቀዶ ጥገና ቢረግለትም ሰኔ 17 ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

 

በካሌፎርኒያ የሚገኙት ጓደኞቹ ስለ ጄፍ አሟሟት ምንም ሰው አጥጋቢ የሆነ ማብራሪያ ስላልሰጠ ሁኔታውን ለመመርመር ልመና አቅርበዋል፡፡ ሲል ክሊንት የከር ተናግሯል፡፡ ለሆስፒታሉ የጆፍ ቤተሰቦች ሊክፍሉ የሚባቸውን ፍርድ ቤቱ ቢያዝም እናም የትኛውም ሆስፒታል ወይም ዶክተር ለቻንድለር ሞት ተጠያቂ ሆኖ ቢገኝ እንኳ ለቻንድለር ላይለስ ሄዷል፡፡ ምርመራውም መልሶ ሊያመጣው አይችልም ሲል የሆሊውድ ዓመታዊ ጽሑፍ /1961/ ዘግቦታል፡፡ ነፍስ ይማር፡፡

 

ደህና ሁን ኩኝ

…ሌላ መንም ተዋናይ ሊተካው የማይችለውን ቦታ ክፍቱን አድርገህ ትተህን ሄድክ፡፡…

በ1961 ዓ.ም የወጣው                        መጽሔት ነበር በጌሪ ኩፕር

የህመም ሞት ምክንያት ዘገባውን የጀመረው፡፡

 

የብዙ ጀግና ባህርያትን ተጫውቷል፡፡ የብዙ የማይበገሩ ሰዎችን፣ በህይወት መጨረሻ ላይ የራሱ ጎበዝናና ትጋት ለዓለም በቀረው ምስሉ ሞገስን እንዲናጸፍ አድርጎታል፡፡ በካንሰር በሽታ የሞት ጥላ ባንዣበበት ወቅትም በአካባቢው ላሉሰዎች ዛናቸውን ለመክፈል ከመጣር አልቦቦነም፡፡ አንድ ጊዜ ኤርነስት ሄሚንግዌይ /ታላት አሜሪካዊ ደራሲ/ እራሱም ሆስፒታል ገብቶ ተኝቶ እያለ ስለኩፕር ይደውልለታል፡፡ ኩፕርም ቀለል አርጎ …ወደ መቃብር ስፍራ ካንተ ቀድሜ እንድምሄድ እወራደረዳለሁ፡፡… ኩፕርም ቀለም አርጎ …ወደ መቃብር ስፍራ ካንተ ቀድሜ እንደምሄድ እወራረዳለሁ፡፡… በማለት ስማይቀረው ሞቱ ነገሮታል፡፡ ከዚህ በኋላም በመላው ዓለም ያሉ ሰዎች የእጦት ስሜት ተሰማቸው፡፡ አንድ የኢጣሊያ ጋዜጣም እንዲህ ሲል አትቷል፡፡ …ምናልባት ከኩፕር ጋር እስካሁን ያለው አሜሪካን አብቅቶለታል፡፡ ገንባር ቀደሙ ክፍል በጥሩ እና በመጥፎ ነገር ድንበር ላይ የሚገኝው ንጽሕና እከተመ፡፡ … አንድ የስዊድን ጋዜጣም … ንጹህ፣ ቀለም የሚል፣ ጥሩ፣ ሞቅ ያለ የልጅ ዓይነት መንፈስ ነበረው፡፡… ሲል ጽፏል፡፡

 

በትክክለኛው ሁኔታ ጌሪ ኩፕር ቀለም ያለ ከሚለው በጣም የራቀ ነበር፡፡ ቤንትሊ መኪና የሚነዳ፣ የፔካስ ስዕሎች ባለንብረት፣ በዕውቅ የተሰሩ 200 ድንቅ የነበሩ ሱፎች ባለቤትና እና ለሚስቱ ሚሊዮን ብር ትቶላት ያለፈ ካውቦይ ነበር፡፡ በጣም የሚወደው የባሕርይ ድርሻም ፈረስ አላስጋለበውም፡፡ ይህም የባሕርይ ድርሻው …ሚ/ር ዲድስ ወደ ዋሽንግተን ይሄዳል… በተሰኝው ፊል የሎንግፌሎው ዲድስ ሲሆን ስለዚህም ባሕርይ ኩፕር ሲናገር፣ በጣም ጥሩ ሰው ይመስላል እናም ይህን ዓይነት ሰው የሆነ ቦታ ቢያጋጥመኝ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ብሏል፡፡

 

ግሪ ኩፕር በምንታና ውስጥ ሄሎና የምታባል ቦታ ተወለደ፡፡ ነገር ገን የልጅነት ጊዜው የምዕራቡ ዓለም ገደብ የሌለው ጉዳይ አልነበረም፡፡ 9 ዓመት ሲሞላው ወላጆቹ … ተገቢውን… ትምህርት እንዲከታተል ወደ ኢንላንድ ልከውት የመጀመሪያው ዓለም ጦርነት ሲጀመር ወደ ትውልድ ሃገሩ ተመልሶል፡፡ ይህ ጦርነት ባይጀመር ኖሮ ወደ ቴቱ ቶሎ ላይመለስ ይችል ነበር የሚል ግምትም አለ፡፡ በምንታና ውስጥ ስለ ፈረሰ ግልቢያ፣ ፈረሰ መግራትና የመሳሰሎትን ሁሉ አጠና፡፡ በሆሊውድ ውስጥ ቶም ሚክስ የተባለው በሳምነት 17,000 ዶላር ስለማግኝቱና ቆናጃጅት ሴቶች መኖራቸውን ሲሰማ ትውና ለመሞከር ወይዘሮ አማራ፡፡ በዚያን ጊዜ ወንዲች የሚጠቀሙበትን ሜክአኝ ሊመለከት ይገርም ነበር፡፡ በሏም …ዊንግስ… የተባለውን ፊል በመስራት ዝናን ሲያተርፍ ሕሊናውን ጠቅ ያረገው ነገር የሜክአፑ ሁኔታ ነው፡፡

 

በድንገትም ቀይ የስፖርት መኪና መያዝ ጀመረ፡፡ እናም በከተማው ያሉ ቆነጃጅትም ይማልበት ገቡቡ፡ ዓመተ ምህረቱ 1927 ኩፕርም በደህና ሁኔታ ላይ ነበር፡፡ ሉፔቬሌዝ የምትባል ሜክሲካናዊት ተዋናይ ጋር ፍር ላይ መሆናቸውንና ለሁለት ዓመታት ያህል በድብቅ የሚኖሩበት ቤት እንደነበራቸው በወቅቱ ላየፍ የተባለው መጽሔት ገልጾታል፡፡ ከዚህ በኋላም ከካውንቴስ ዲ ፍራሶ ጋር ይገናኛል፡፡ በሚሊዮን ዶላር የሚገመተውም ቪላዋ ውስጥ መኖር ሲጀመር የሚለብሳቸውም ልብሶች በሮማውያን ልብስ ሰፊዎች የተዘጋጁ ነበሩ፡፡ ነገር ግን እውነተኛው የኩፕር የፍቅር ጊዜ በ1933 ልጃቸው ማሪያ ተወለደች፡፡ ትልቅ ክብሩም ነች ወ/ሮና አቶ ኩፕርም ለሁለት ዓመታት ያሀል የለያይተው ኩፕር የሚስቱን ሃይማኖ የካቶሊክ እምነትን ከተቀበለና የራሱን እምነት ሲቀይቀር እንደገና ትዳራቸውን አደሱት፡፡

 

ኩፐር ስለተቀበለው ሃይማኖት ለሎዊላ ፓርሰንስ እንዲህ ብሏታል፣ …የሚያጽናና ስሜት፣ ምቶችና መግባባትን አምጥቶለኛል፡፡… እናም አሟሟቱን ለተመለከተው እነዚህ ቃላቶች በእርግጥም ትክክል ነበሩ ያሰኛል፡፡

 

ክኪፎርድ አይትስ የጠባለው ፀሐይ ሲኒማ …እሱ የትክክለኛው ነገር ገጣሚ ነው፡፡ ስላላሞች፣ ወይፈኖች፣ መኪኖችና፣ የባህር ሞገዶች ሁሉንም ነገር ያውቃል፡፡ እሱ የልጅ ጉጉነት ያህል ስሜትና የድሮ ጊዜ ትህትናን የተላበሰ ነው፡፡ …ይላል ስለ ጌሪ ኩፕር አስተያየቱን ሲያሰፍር፣

 

ኩፐር የሥራ ድርሻውን ለመወጣት በጣም ይጥር ነበር፡፡ …ሜተድ… የትወና ጥናት ዘርፍ የመጀመሪያው ተዋናይ እንደሆነ አድርገው የሚገምቱ ሰዎች ነበሩ፣ ትክክል ናቸው፡፡ ፍልማቸሁን እንደሚያበላሸው አውቁ፡፡ ለመጀመሪ ጊዜ ከእሱ ጋር ለስራ የሆነ ትክክል ያልሆነ ነገር እንዳለ አስቤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ብሮች እሳት ላይ እንደወደቀ ቅቤ ባክኑ በማለት አስብ ነበር፡፡ በኋላ ስክሪን ላይ ስመለከተው በጣም ተደንቄያለሁ፡፡ …ብሏል የፊልም አዘጋጁ ሳም ወድ፡፡ በሚሊዮን የሚቆሩ ናቸው ለ30 ዓመታት የሰራቸውን ፊልሞች አንድ ሳይቀር የተመለከተለች፣ ፕሪዚዶነቶች ንጉሶች፣ ሕጻናት ሁሉም ሰው፡፡ እናም ሲሞት ማንም የፊልም ተዋናይ ሊተካው የማይችለውን ክፍት ቦታ ትቶ አለፈ፡፡ ነፍስ ይማር፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ቻርለስ ኮበርን

ቻርለስ ኮበርን 64 ዓታት በትወና ዓለም 84 ዓመታት የሕይወት ዘመን እንደጨረሰ ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ፡፡ በ74 ዓመት ዕድሜው የሌሊት ካርታ ጨቁማር ላይ ተይዞ ታስሯል ፡፡

 

የተወሰኑ ሰዋቹ ናቸው የደስታ ሕይወት ያሳፉት፣ እሱ ግን ሞት በቀረበ ጊዜ እንኳን ኀዘንን ለማራቅ የሞከረ ሰው ነው ፡፡ ..መቃብሬ ላይ ለመገኘት የሚመጡት ሰዋች ሁሉ ፈገግታ ከተላበሰ ፊትና ደስታ የሞላባቸው ልቦች ይዘው መገኘት እንደሚገባቸው ይታወቅ .. የሚሉ ከተለየችው ሚስት ኤሻህ ዊሊስ ጋር አመዱ እንዲቀላቀል ጠይቋል፡፡

 

እጅግ ቆንጆ የሆነ የፍቅር ታሪክ የነበራቸው ፣ በ1905 ኦርላንዶና . ሮዛሊንድ የተባለው ፊልም ላይ ያሉትን የባሕርያት ስሞች በ31 ዓመታት የጋብቻ ዘመናቸው እርስ በርሳቸው ይጠራሩበት ነበር ፡፡ ባለቤቱ በሞት ከተለየችው በኃላም ኮበርን ወደ ሆሊውድ መጣ ፡፡ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ፊልሞችን ባለመስራት አቋም ጸንተው ቴያትሩን ብቻ አጥብቀው አብረው ሰርተዋል፡፡ ኮበርን ሮማንቲክ እንደመሆኑ እንደ ሮዛሊንድን ኦርላንዶ የለበሱ ወንድና ሴት በሆሊውድ የሚገኘው ቤቱ ለጉግስ የሚሆኑ ፈረሶችን ስለሚያፈቅር ብዙ አሰባስቧል ፡፡ በ70 ዓመቶም የፈረስ ግልቢያ ውድድር አካባቢ መገኘትን አዘውትሮታል ፡፡ ስኮች ዊስኪን ፣ ቆንጃጅትን አፍቅሯል ፡፡ ሌሊቱን ሙሉም ሲጨፍር ማደር ይችል ነበር፡፡ ከሱ ጋር አንድ ቀን ሙሉ ያሳለፈ ቃል አቀባይም ‹‹ ሰውየው የሚበገር አይደለም ከእንቅልፉ ረፈድ አድርጎ ይነሳል ፡፡ የምሳ ግብዛ ከቆናንጅት ጋር ያደርጋል፡፡ከሰዓት በኃላውን በስራ ያሳልፋል ፡፡ ጂንና ስኮች ጸሀይ መጠለቂያው ለይ ከእራት ቀጠሮዋች በኃላ ዳንኪራ በመርገጥ ክለቦችን ሲዘጉም የቀረውን ሌሊት የካርታ ቁማር ላይ ይቆመጣል ፡፡..በማለት ዘግቦ ነበር ፡፡ በአንድ ኣይናማዋ መነጽርየተነሳ በትውልዱ ጂኦርጂያዊ የሆነውን ተዋናይ እንግሊዛዊ አድርገው የወሰዱት ብዙ ሰዋች አሉ ፡፡እለዚህችም አንድ ዓይናማዋ መነጽር‹‹በ35 አመቴየቀነኝ ዓይኔ ችግር ነበረበት በዚህ ወጣትነቴም መነጽር ማድረግ ስላልፈለጉሁ አንድ ዓይና መነጽር መረጥኩ፡፡ ሩቅ ለማየት ያስችለኛል ፡፡ በሱ ማንበብ አልችልም ስበላም አልቀጠምበትም ሾርባዬን ውስጥ ስለሚወድቅብኘ፡፡ ይላል ወደ ሲኒማ ዓለም የገባው በ60 ዓመት ዐ4ድሜው ቢሆንም .ዘ.ሞር.ዘ ሜሪየም .በሚለው ፊልም የኦስካር ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል ፡፡ ከ6 ዓመታት በኃላም ለሁላተኛ ጊዜ ዊኒ ፍሬድ ጂን ክሌሌንትስ ናትዝካ የተባለች በ41ኣመት ዕድሜ የሚበልጣትን ሴት አገባ፡፡ ..ሻማውን በሁለት ጫፎች ለኪሼዋለሁ ነገር ግን የሻማው ክር እስካሁን እየተቀጣጠለ ነው ..ብሎም ነበር፡፡ አንድ ነሐሴ ወር ላይ ግን ከልብ ድካም በኃላ የጉሮሮ ቀዶ ጥገና ተደርጎለት የሕይወቱ ብርሃን ጨልሟለ፡፡

.. ሃዘን አይኑር፣መኖሬን በማወቄ ረክቻለሁና፡፡ ..የሚለውን ዓይነት ኑዛዜም ጥቂት ሰዋች ብቻ ናቸው ማለት የሚችሉት፡፡ ነፍስ ይማር፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ጁሊያኖ ጄማ

ይህ ጣሊያዊ ተዋናይ ለኛም ተመልካቶች ዝነኛ ነው፡፡ በፊልም ዓለም ውስጥ ባሳለፋቸው 30 ዓመታት በማንኛውም ዓይነት የፊልም ቅርጾች ውስጥ ፈልፏል፡፡ ታሪካዊ ፊልሞች በብዛት በሚወጡበት ጊዜያት አዚያው ነበር፡፡ ለተመልካቶች የግማሽ አምላክ ያህል ነበር፡፡ …የምዕራቡ ስፖጌቲ… ሲመጣም የማይበገረው ካውቦይ፣ በፖሊሶችም ፊልም ውስጥ ወንጀልን በመዋጋት ተሳትፏል፡፡

 

የፊልም አዘጋጆች፣ ሀያሲያንና ተመልካቶች ጂሊያኖ ጂማን ቀለል ያለው የስነጥበብ ዘርፍ ተዋናይ አርገው ይመድቡታል፡፡ በኮሜንቼኒ …እውነተኛ የፍቅር መጨረሻና… በሻሌሪና ድዙርሊኒ ፊልሞች አማካኝነት …ቅጥያውን… ለመለወጥ ተገደዋል፡፡ በነዚህ ፊልሞች ላይ ጁሊያኖ ጂማ መሳጭ ተወናይ ሆኖ ነበር የቀረበው፡፡

 

ፈረስ በመግራት ኑሮውን አያሸነፈ እያበቺኒቼታ ውስጥ ከታወቁት አንዱ ነበርና ሙያውን ለመወለወጥ አስቦትም አያውቅ ደህና ይከፈለው ነበርና፡፡ ነገር ግን ዱቼዬ ቴሳሪ ቀረበውና …ቤን ሑር… ለተባለው ፊልም አትሌት የሆነ ተዋናይ አንደሚፈልግ ገለፀለት ጊዜው 1961 ዓ.ም ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ባለው ጊዜ ተዋናይ ሆኖ መጫወቱን ቀጥሏል፡፡

 

በጣሊያን ሲኒማ ዕድገት ስላለው ቀውስጥ እንዲህ ይላል፡፡ …አዳዲስ ነገሮች መቅረብ ትተዋል፡፡ ዛሬ ብዙ የፊልም ፀሐፍት አሉን፡፡ ዕውነተኛ አዘጋጆች ግን ያንሱናል፡፡ የፊልም ችግር ግን አሁን አለብን፡፡ ተመለካቶችም መመልከት የሚመርጡት የአሜሪካን ፊልም ብቻ መሆኑ አሳሳቢ ነው፡፡

 

በሁለት ፊልሞች ላይ ሞንት ገሞሪ ውድ በሚል ስም ተጠቅሟል፡፡ ምክንያቱም ፊልም የአሜሪካን ሲሆን ለጣሊያኖች የመጀመሪያ ነበሩ፡፡ ዱቼዬ ሳሪም አሜሪካዊ ስም አንዲመረጥ ይነግረዋል፡፡ ሞንትግሞሪ ውድ የሚለውን መረጠ፡፡

 

ቺሊያኖ ጂማ ሉኪኖ ቪስኮንቲ የተባለውን አዘጋጅ አብሮ ከሠረቸው ሁሉ ባልተለመደ ሁኔታ የሚያደንቅ ነው፡፡ ከሱ ጋር መስራቱ ከደስታ በላይ እንደሆነ በአንደነቱ ይናግራል …ጌፓርደት… በተባለው ፊልም ላይ ያለው የባሕርይ ድርሻ ትንሽ ስለሆነ ጊዜ ሰይፈጅበት ጨርሶታል፡፡ ነገር ግን የቪስኮንቴ ሥራ በሚሳድርበት ደስታ ፊልሙ ተሠርቶ እስኪያበቃ ድረስ ከዛው አካበቢ አልጠፈም ነበር፡፡ እስከ ዛሬ ድረስም ከዚህ ፊልም ጋር የተያያዙ አንዳንድ ነገሮችን ያስታወሳል፡፡

 

በአሁን ጊዜ በሚወጡ ፊልሞ ብዙም አይታይም፡፡ በፊልም ዓም ተሳትፎውን የቀነሰ ይመስላል፡፡ ሁኔታው ግን ወዲህ ነው፡፡ ለፊልም ሥራ ስዙ ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡ የመምረጥ መብትም አለው፡፡ ከቀረቡለት የፊልም ጥያቄዎች ውስጥ እየመራረጠ ነው፡፡ በአንድ የፈረንሳይ፣ ጀርመንና ኦስትሪያ በኅብረት በሰሩት የቴሌቪዥን ፊልም ላይ የመኪና እሽቅድድም ተወዳዳሪ ሆኖ በሥራ ባልደረባው ላይ በደረሰበት አደጋ ምክንያተ ከሥራው የሚለቅ ባሕርይን ሆኖ ይሳተፋል፡፡ ወጣት የፊልም አዘጋጆችም ለት/ቤት መመረቂያ ሥራቸው በሚያዘጋጁት ፊልም ላይም ይከፈላል፡፡ ከአያንዳንዳቸን የሚበቀው ግዴታ እነዚህን ወጣቶች የራሳቸውን በሥነጥበብ ዘርፍ ውስጥ ያላቸውን ቦ እስኪያገኙ መርዳት ነው፡፡

 

በቴያትር የመሳተፍ ፍጎቱም ችሎታውም አለው፡፡ ነገር ግን በጣሊን አገር ያለው የቴያትር ሁኔታ ለዚህ አላደለውም፡፡ ለምሳሌ በፈረንሳይ አንድ ተዋናይ በቴያትርም ሆነ በፊልም በሁለቱም ላይ የተሳካ ተሳትፎ ማድረግ ይችላል፡፡ በጣሊያን ገን … በማለት ጁሊያኖ ጂማ በሀገሩ ስላለው የቴያትር ስነጥበብ ዘርፍ ስለተቀናጀበት የመዋቅር ዓይነት ተችቱን ይዘነዝራል፡፡

 

እስቲ ለዛሬ በዚሁ ይብቃን ሳምን ደሞ እንገናኝ፡፡

 

ደምስ በቀለ

ከእርዳይታ

 

 

 

ፍራንኮ ኔሮ

…የሕይወት መመሪያዬ ለውጥ ነው፡፡… ይላል፡፡ ስሙን ከፍራንኪ ስፐራኒሮ ወደ ፍራንኮ ኔሮ ያሳጠረው፡፡ እ.ኤ.አ. ኖቬምበር /ኅዳር/ 21,1941 ዓ.ም በሳን ፕሮሳኤሮ በሞዬና ክፍለ ሀገር ውስጥ ተወለደ፡፡ አባቱ ፖሊስ ሆኖ ያገለግልበት በነበረው ፖርማ ከተማ አደገ፡፡ በአጥቢው ቄስ በተደራጀው የቴያትር ክበብ መሰል ቡድን ውስጥ እንደ አዘጋጅ ተዋናይና ሁለገት ሠራተኛም ሆኖ በትናንሽ  ድራማዎች ከልቡ ይካፈል ነበር፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥም ብቻውን እንዲና ንይነት ሲያዘጋጅ ብዙ ጊዜ ምን ለማግኝት ነው? እየተባለ ሊሳቅበት የሁል ጊዜ መልሱ አንድ ቀን ታያላችሁ፡፡ ብቻ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜያ አንድ ቀን በጣም ከቅ ይመስል ነበር፡፡

 

በጦርነት ጊዜ ግዳጅም ብቻውን ቴያትር ማደረጀቱን ቀጥሎ በኋላም ወደሚሳኖ ሄዷል፡፡ የምጣኔ ሀብት ትምህርት ሊያጠና፣ ያም ሆነ ግን በውስጡ የተጻፈ ነው የስነ ጥበብ ፍጹም ስላልሰጠው አብረውት የሚመሩትን ጓደኛች በማስተባበር በየክለቡ በምሽቶች ዘፈናቸውን ማሟሟቅ ተያያዙት፡፡ ይ የሚሆነው የትምህርቱን የጥናት ጊዜ በመስዋት ሰለነበረ በወላጅ እናቱ ልመና መየምሽት ክለቦች መዝፈኑን አቋረጠ፡፡ ትምህርቱን ገን መጠናቀቅ አልቻለም፡፡ …ፈተና እየተሰጠ እያለ እኔ ሮም ውስጥ ፊልም ሥራ ላይ ነበርኮ፡፡ በማለት ይገልጻል ፍራንኮ ኔሮ በራሱ እንደበት፡፡

 

ወደ ሮም የመሄዱን ሃሳብ አስቀድሞ የተቀበለው ሮቤረቶ ሮዜሊኒ ከተባሎው የፊልም አዘጋጅ ጋር ለመነጋገር ነበር፡፡ ነገር ገን በዚያ ጊዜ ጆን ሂዮስተን የተባለው የፊልም አዘጋጅ መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ፊልሙን በቼኔቼታ ውስጥ እያዘጋጀ ስለ ነበር የአቤልን ባህርይ ሆኖ እንዲሠራ ሰጠው፡፡ ይህ የሆነው በ1983 ዓ.ም ነበር፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ለመሥራት የተቀበለው ገፀባሕርይ ከመጀመሪው በጣም የተለየ ነው፡፡ ጁንጎን ሆኖ ለኢጣሊ የመመሪያው ኮቴክስ …ደግነት በልቡ የሌለ፣ በፈረሱ፣ በሸጉጡና በፍትህ የሚተማመን አንድ ሰው… አንድደሃያሲ እንዳስፈረው፡፡

 

በጃንጎ ፊል ውስጥ ያለ እንዳንድ የጭካኔ ድርጌት የሃያሲያን ብዕር በመዘዝበትም በአሜርካን ሀገር ጭምር የገንዘብ ሳጥኖ እየሞሉ የጀንጎ ፊልምም ቀጣይ ፊልሞች እየሠሩለት ወደ ሴሪያል ፊልምነት ተቀይሯል፡፡ ሌላው ጣልያናዊው ተዋናይ ጁሊያኖ ጂማ እና አሜሪካዊው ክሊንት ኢስትውድ በተመሳሳይ ጃንጎ ፊልሞች ተሳትፈዋል፡፡ ፍራንኮ ኔሮን በመከተል፡፡

 

በዚህ የጃንጎ ፊልም ዕውቅና ፍራንኮ ኔሮ ታታሎ በምዕራቡ ዓለም ግትር ጀግና ተዋናይ እንደሆነ አልቀረም ልዩ ግምትና ክብር ያለው የሰር ላውረንስ ኦሊቪዬን ምክር በመቀበል፣ መጀመሪያ እውነተኛ ተዋናይ መሆን እናም ከዚያ በኋላ

 

በፊልም ሥራ ውስጥ የተለያዩ ባሕርያትን አፈላልጓል፡፡ በ1987 ዓ.ም በዳሚያኖ ዳሚያኒ አዘገጅነት …ዶን ማርያኖ ምንም አያውቅም፡፡… በሚለው ፊልም ውስጥ ኢንስፔክተር ቤሎዲን ሆኖ በአመርቂ ሁኔታ ተጫውቶታል፡፡ በዚያው ዓመት ውስጥ …ካሜሎት… በሚለው የአሜሪካኖች ሙዚቃዊ ፊልም ላይ ለመጀመሪ ጊዜ ጎልህ ድርሻ የተጫወተበትን ቦተ አገኝ፡፡ በፊልም ቀረጻው ላይ ቫኔሳ ሬድግሬቭ የምትባለውን እንግሊዛዊት ተዋናይ አግኝቶ በሕይወት ጉዞው ላይ ረዳት ጓደኛ ሆነው ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፡፡

 

ከዚህ ጊዜ በኋላ ነበር የሙያ ታሪኩን ምን ጊዜም ለውጥ ለሚለው መርሆ መግንባት የጀመረው፡፡ …አደጋና ኪሳራ ላይ ሊጥል የሚችል ኃላፊነት መውሰድና እራሴን ከሁኔታዎች ጋር ማዛመድ እፈልጋለሁ፡፡ የዚህ ሚስጥር ምንጊዜም አዲስ ነገርን መሞከር ነው፡፡ ከእያንዳንዱ ፊልም በኋላ የምሳተፍበትን ፊልም ይዘት ለመቀያየር እሞክራለሁ፡፡ ስለዚህም በሙዚቃዊ፣ በወንጀል ነክ ፊልም፣ አንድ ወጥ ፊልም፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ሁኔታዎችን በሚተቹ ፊልሞችም ተሳትፊያለሁ ብሏል ፍራንኮ ኔሮ በባህርይ ሁለገብ መሆኑን በማስመስከር፡፡ ከ75 በላይ በሚሆኑ ባሕሪያት /በፊልም ውስጥ/ ተጫውቷል፡፡ ሁሉም በእኩል ደረጃ የሚታወቁ አለመኖናቸውን ቢገነዘብም እሱ ግን ሁሉንም ይወዳቸዋል፡፡ በብዙም የውጪ ፊልሞ የተሳተፏና የሚሳተፍ ጣልያናዊ አክር /ተወናይ/ መሆኑም ሳይሰማው አለወቀረም፡፡ በደቡብ አሜሪካ፣ በሰሜን አሜሪካ፣ በእንግሊዝ፣ በስፔን፣ በፈረንሳይ፣ በምዕራብ ጀርመን፣ በቀድሞዋ ቦቭየት ኅብረትና በየጉዝላቪያ ፊልችን ሰርቷል፡፡ በየጎዝላቪያ በኔሬትቫ የተካሄደው ጦርነት የሚለውን ፊልም ከሰርጌይ ቦንዳርችክ ጋር በ1970 ዓ.ም እውን እንዲሆን አድርጓል፡፡ በመቀጠልም ሜክሲኮ በእሳት ነበልባል ውስጥ በተባለው ፊልምም የጆን ሪድን ባሕርይ ተላብሶ ተጫውቷል፡፡

 

በዚህ ሙያ የቀረውና መሆን የሚመኝው ለሚለው ጥያቄም የፊልም አዘገጅነት በማለት ሀሳቡን ብዙ ጊዜሲገልጽ ይሰማል፡፡

 

በሲኒማ ስክሪን ላይ ብዙ ባሕርያት ተላብሶና ችሎታውን ያስመሰክረው ተዋናይ ፍራንኮ ኔሮ በዋናው ምኞቱ ይሳካለትይን፡፡ ዕድሜና ትዕግስቱን ከሰጠን ወደፊት እናየዋልን፡፡

 

ደምስ በቀለ

ከእርዳይታ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ሊያ ማሳሪ /ጣሊያናዊት ተዋናይ/

በአንድ ወቅት ላይ በፊልም ትወና ሥራ ላይ የተሰማሩት በተለይ ዋና ገፀ ባሕርይን ቦታ ተዘው የሚጫወቱ ሰዎች ዘመናዊ ትምህርትን የቀሰሙ /ከፍተኛ ትምህርትን ማለቴ ነው/፣ ከአገርኛ ቋንቋ ሌላ አንድ ሁለት ቋንቋዎችን የሚችሉ አርጌ መወሰዴ ትዝ ይለኛል፡፡ ፊልምን ከማዝናናት ጎኑ አልፎ በገባኝ መንገድ ትምህርት ሰጪነቱንም ከማመን ጋር፡፡

 

ፊልምን የመከታተል ዝንባለው ካደረብኝ በኋላ በተለያየ አጋጣሚ የማግኛቸውን ስለፊልም የተጻፈ ጽሁፍችን ማገላበጥ ከጀመረኩ በኋላ ግን አልፎ አልፎ የተዋጣለቸው ተዋንያን በአጋጣሚ ወደዚህ የሥነ-ጥበብ ክፍል የተሳቡ መሀናቸውን እየተገነዘብኩ ነው፡፡ ከትወና የተፈጥሮ ስጦታ በሻገር በልምድና በሙያው ትምህርት በመታገዝ የሚደብር መሆኑን ተረድቸዋለሁ፡፡

 

ዛሬ አልፎ አልፎ ከሚዋጣላቸው ተዋንያን መካከል ስለ ሊያ ማሳሪ/ጣሊያናዊት ተዋናይ/ በጥያቄና መልስ መልክ የቀረበውን ዘገባ እንዳለ ወደ እማርኛችን መልሼ እነሆ ብያለሁ፡፡

 

ጥያቄ፡-      እስቲ ሥል ሥስዎ ይንገሩን? ከአጀማመርዎ በስነ-ጥበብ ውስጥ ከሕይወትዎ አብዛኛውን ክፍል አሳልፈዋል አይደለም?

ሊያ፡-        ሁሉንም ማወቅ የምትፈልፉ አይመስለኝም ወይንም ሁሉም ነገር እንዲገችሁ፡፡ ስለራሴ ልንገራችሁ፡፡ አያቴ 12 ልጆች ነበሯት፡፡ ብቻዋን የምትንከባከባቸው፡፡ ባሏ በ25 ዓመት ይበልጣት ስለነበር የሙት ሚስት የሆነቸው መካከለኛ ዕድሜ ላይ እያለች ነው፡፡ ልጆቿንም ለማሳደግም ልብስ እያጠበችና ያገኝችውን ሥራ በመስራት ነበር አባቴ 5ኛ ልጇ ነው፡፡ የማታ ትምህርት እየተከታተለ በኋላ ደግሞ ሥራ ልይ ተሰማርቷል፡፡ ልጆቿ ሁሉ አያቴን ያመልኳታል፡፡ በጦርነቱ ጊዜ አባቴ መንግሥትን ከሚቃወሙ ወገኖች ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ ወደ እስር ቤት ገብቷል፡፡ እቴ ለልጆቿ ሙት ለቤተሰቧ አሳቢ ቅን ሴት ነበረች፡፡

 

ስለእኔ ባሕርይ አቀራረጽ ማንም ቢሆን በተለየ ሁኔታ አልተከታተለውም፡፡ ወንድሜ መሐንዲስ ነው፡፡ እህቴ ፒያኖ ተጫዋች ናት፡፡ እኔ በባህርይ የተባለሽሁ መጥፎ ነበርኩ ከቤተሰቡ ሁሉ፡፡ በ19 ዓመቴ ከፍተኛ ጭንቀት ደረሰብኝ ከጋብቻ ዕለቴ 15 ቀን ቢት እጮኛዬ በመኪና አደጋ በሞት ተለየኝ፡፡ በከፍተኛ ደረጃ የበችኝነትና የእርጅና ፍርሃት ተሰማኝ፡፡ ከዚህ ሁኔታዬ የቤተሰቤ የቅርብ ወዳጅ ፔትሮ ጄራርዲ አወጣኝ፡፡ ስለ እሱ አልሰማችሁ ይሆን? የታወቀ የጣሊያን ለፊልም የሆኑ ድርሰቶች ፀሐፊ ነው፡፡ በፊሊኒ ፊልሞች ላይ የፊሉኒ ረዳት ነው፡፡ /ፊሊኒ ዕውቅ የጣሊያናዊ ፊልም ዳይሬክተር ነው፡፡/ እሱጋ መስራት ጀመርኩና አሁን ያለሁበት ደረጃ ደረስኩኩ፡

 

እና በዚህ ሁኔታ የማሪዬሞኒቼሊ ፀሐይ አልባው ደሞ የሚለው ለመጀመሪያ የተሳተፍኩነበት ፊልም ሊታይ ጊዜው ተቃረበ፡፡ ሞኒቼሊ ከጃራርዲ ጋር ትውውቅ ስለ ነበረው ለብዙ ጊዜ እኔን በሱ ፊልም ላይ እንደሰራለት እንዲግባባኝ ይጠይቀው ነበር፡፡ እኔም በጠበቃ ሁኔታ ተቃውሞዬን ገለጽኩኝ ወላጆቼ ምን ብለው እንደሚናገሩ ልትገምት ትችላለህ? በቀጥታ ይገሉ ነበር፡፡ ነገር ገን ተስፋ የማይቆርጥ ሰው ስለነበር በመጨረሻ እኔም ተስማማሁ፡፡ ከዚህ ፊልም ጋር ብዙ ስቃይ አሳልፊአለሁ፡፡ ሞኒቼሎ እኔ እንዳልጫወት ይፈልግ ነበር፡፡ እ ግን ከሌሎች ድጋፍ እፈልግ ነበር፡፡ በፍርሃትና በጭንቀት እየተንቀጠቀጥኩና እየተዋጥኩ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ተራና ግምት ውስጥ የማልገባ ጣልያናዊት ኮረዳ ነበርኩ፡፡ ጎበዞች ተዋናዮች ከሁኔታዬ ልገባቸው አልቻልኩም፡፡ ረዳት የለሸነት እየተሰማኝ የፊልም ሥራውን አቋርቨጬ ወደ ልብስ መረጣዬ መመለስ አስቤ ነበር፡፡ በኋላ ደግሞ ከእኛ ከሁለታችን ቢቀር በሚለው የሬናቶ ካስቴላኒ ፊልም ላይ ተሳተፍኩ፡፡ ከሬናቶ ጋር ለ4 ወራት ያህል ስሠራ በኮሜዲ ተዋናይነት እንደሚዋጣልኝ ነግሮኛል፡፡ ከሱም የትወና ባለሙያነት ምን እንደሆነ ተምሬያለሁ፡፡ ከበታችነት ስሜቴ አላቅቆኛል፡፡ እናም በሙሉ ልቤ መተንፈስ ጀመርኩ፡፡

 

ጥያቄ፡-      አብሬው ከሰረዋቸው የፊልም ዳይሬክተሮችን ማንን ያደንቃሉ?

ሊያ፡-        አንቶኒ ፊላጭ ቆራጭ ነበር፡፡ ከተዋናዮች ጋር ሲሰራ ልክ ከአሻንጉሊቶች ጋር እንደሚሰራ ዓይነት ነው፡፡ ነገር ግን አጨራረሱ የሚለው ፊልሙ በኔ ግምት በጣም ቆንጆ ነው፡፡

ጥያቄ፡-      እርስዎ በፈረንሳይም ሆነ በጣሊያን በሚሰራቸው ፊልሞች በአንድ ዓይነት ደረጃ ተሳክቶልዎታል?

ሊያ፡-        በሁለቱም ቦታዎች ጥሩ ስሜት ይሰማኛል፡፡ በፈረንሳይ ብዙ ድንቅ ባለሙያዎች ጋር ተገናኝቻለሁ፡፡ እዚህ በሥራ ላይ ነገሮች በግልጽና በትክክል ነው የሚነገሩት፡፡ በሕልማዊ ሁኔታ የሚከሸኑት ጥቂቶች ናቸው፡፡ በክሎድ ኮሜ …ነገሮች በሕይወት… ስለሚለው ፊልም በጣም ቆንጆ ትዝታዎች አሉኝ፡፡ ዲዮቪልን፣ ግራን ዲፊርን እና ሊዊ ማልን እወዳቸዋለሁ፡፡

ጥያቄ፡-      የሚሳተፉባቸው ፊልሞች የገዘፈ ናቸው፡፡ የሚጫወቱትን ባሕርይ እንዴት ነው የሚመርጡት?

ሊያ፡-        እንዴት? የመጀመሪያው ነገር ለፊልምነት የተዘጋጀው ጽሑፍ ነው፡፡ አዘጋጁስ? እሱም ትርጉም የሌለው አይሆንም፡፡ ምንያቱም የተዘጋጀውን ጽሑፍ ዳር የሚያደርሰው እሱው ነውና፡፡ ሌላ? ከማን ጋር እንደምጫወት፣ በሥራ ጊዜ የማራኪነት ሁኔታ መኖርም አነስተኛ ግምት አልሰጠውም፡፡

ጥያቄ፡-      ይህ በእንዲህ እንዳለ ደካማ የፊልም ጽሑፍ ነገር ግ ከጥሩ አዘጋጅ ጋር ቢሆን ሌቀበሉት ይችላሉ?

ሊያ፡-        ብዙ ጊዜ፡፡

ጥያቄ፡-      የፊልሙ ሥራ በመካሄድ ላይ እያ ስፊልሙ አስተያየትዎን ይግልጻሉ?

ሊያ፡-        ይ የአዘጋጁ ሥራ ነው፡፡ እኔ የፊልሙ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ረዘም ላላ ጊዜ ሥራ ያስፈልገኛል፡፡ የታሪክ ዶክመንተሪ ፊልሞችን በጣም እወዳለሁ፡፡ ከፍራንቼኮ ሮዚ ጋር በዚህ ዓይነት ፊልም በመሳተፌ እስደስተኛል፡፡ የታቪያኒ ወንድማማቶችም በጣም ጥሩ ሰዎ ናቸው፡፡ በእውነት ትንሽ ነካ /ገለብ/ የሚያደርጋቸው ሰዎች ቢሆኑም አዋቂ ነታቸው ልክ የለውም፡፡

ጥያቄ፡-      ከዚህ በፊት ስላልተሳተፉባቸው የሚፀፀቱባቸው ባህርዮች የትኞቹ ናቸው?

ሊያ፡-        ጣፋጭ ሕይወት የሚለው ፊልም ላይ እኑክ ኤሚ የጠጫወታቻትን ባሕርይ በጠታጣቴ አዝኛለሁ፡፡ ሌሎችም ጥሩ ፊልሞ ላይ የመሳተፍ ዕድል አጥቻለሁ ይሄ ሁሉ እንግዲህ እንግሊዝኛ ቋንቋ አለመቻሌ ነው፡፡

ጥያቄ፡-      በብዙ የቴሌቪዢን ፊልሞች ላይ ተጫውተዋል?

ሊያ፡-        አዎን በእናካረኒና፣ በአንድ ንጉስ፣ በሳካራማዞቭ ወንድማማቶች እና በሌሎችም በዛ ባሉት ተካፍያለሁ፡፡

ጥያቄ፡-      የርስዎ ምርጫ ኮሜዲ /አስቂኝ ድራማ/ ነው ወይንስ ትራጂዲ /አሳዛኝ ድራማ/ ነው?

ሊያ፡-        ኮሚዲ /አስቂኝ ድራማ/ ለኔ ይቀርባል ትራጄዲው /አሳዛኙ/ የእንትውና ላይ ጥላውን ያጠለበታል፡፡ በፈረንሳይ ውስጥ ቀላል ያለ ኮሜዲ ተዋናይ ክፍል ውስጥ መድበውኛል፡፡ በጣሊያን ውስጥ የትራጄዲ ተዋናይ፡፡ ሆኛለሁ፡፡ ይህንን አውደዋለሁ፡፡ ለማለትም የተለያዩ ገፀ ባሕርያትን ወክዬ መጫወት መቻሌን ይመሰክርልኛል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ጁሊ አንድሪውስና ቤተሰቦቿ በመድረክ ላይ

በሱስ አንጀሊስ ውስጥ ለብዙ ሰዎች የጁሊ አንድሪውስ ስም ሲነሳ በቆዩት ፊልሞች ሜሪ ፖሊንስ እና የሙዚቃ ድምጽ ብዙ የልጅነት ጊዜ ዓለም ትዝታዎችን የመቀሰቅሱ ሃሳቦች በአእምሮአቸው ይታወሱአቸዋል፡፡

 

የአፈታሪኮች ተዋናይዋ ለብዙ ሕልማዊ ባሕሪያት ነፍስ ከዘራች በኋላ አሁን ደግሞ በባለቤቷ ብሌክ አድዋርድስ በተዘጋጀ ፊልም ላይ የራሷን ሕይወት ክፍል እንደገና እየተጫወተችው ወይንም በፊልም እየኖረችው ነው ለማለት ያስችላል፡፡

 

/ሕይወት እንዲያ ነው/  በባልና በሚት፣ በተዋናይነት እና ፊልም አዘጋጅ ትብብር የተሠራው አዲስ ፊልም ነው፡፡ ከራሳችው ሕይወት ክፍል    ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ ደስታና ኋዘናቸውን በተመለከተ ለማቅረብ ባልና ሚስቴ የታሪካቸወን ቅንጫቢ ለእይታ አብቅተውታል፡፡ ሕይወት እንዲያ ነው፡፡ የተሰኝው ፊልም ተረጻው የተጠናቀቀውም በፖስፊክ ባሕር ዳርቻ ማቡ ውስጥ በሚገኝው መኖሪያ ቤታቸው ነው፡፡

 

ልጆቻቸው ኤመ /ጂሊ ከመጀመሪያ ባልዋ ቶኒ ዋልተን የወለደቻት/ እና ጄኒፈር /ብሌክ/ ከመጀመሪያ ተዋናይት ሚቱ ፖትሪሲያ ዎክር ያገኛት /በፊልም ውስጥ ተካፋዮች ናቸው፡፡ ጃክ ሌመን የኤድዋርድ ቤተሰብ የጥንት ወዳጅም መሪውን ወንድ ገፀ በሕርይ፣ ማለትም ዝነኛ መሐንዲስ ባሕርይ ሆነ እና ክሪስ የሚባለው ልጁም በፊልሙ ላይ ቦታ አለው፡፡ መሐንዲ ዕድሜው ወደ 60 እየተጠጋ ሕመም መሆኑን የሚገልጽ ጅማቷ ተቆርጦ የምርመራውን ውጤት የምትጠባበቅ ዘፈኝ ድርሻ አላት፡፡

 

ባልና ሚቱ በችግረ በተጠመዱ ሶስት ልጆቻቸው ተከበው ልጆቻቸው ሳያስቡበት ችግራቸውን እናታቸው ላይ የሚያሸክሙ ዓይነት ባሕርያት ናቸው፡፡ ይህ ተራኪ የፊልም መወቀቅር ከተለያዩ ክፍሎች መገናኝቱ በልምድ የዳበሩ በልና ሚስት ስለዘጋጁት ሜኑ አሌ የሚል አይሆንም፡፡ ነገር ግን ምን ያህል ለሚለው ጁሊትነግ ረናለች፡፡

 

ከእንዳንድ ማስተካከያዎ በስተቀር ፊልሙ ከሕወት በተወሰዱ እውነተኛ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ አልፎ አልፎም ከትክክለኛ ሁኔታ ወጣ ይላል፡፡ ለምሳሌ ባለቤቴ መጻፍ አይተው የወደፊቱን የሚነግሩ ጂፕሲዎች ጋር ሄዶ አያውቅም፡፡ በአራት ጠረጴዛ ዙሪያ ያለው ጨዋታ፣ ውይይት አለመግባባቶችና ሌሎች ጥቃቅን ዘርዘር ያሉ ሁኔታዎች በአብዛኛው ፊልሙን ከእውነተኛው ሕይወት ጋር ያቀራርቡታል፡፡

 

አረ ከልጄ ጋር መኝታ ቤት ውስጥ የምሰራበት ክፍል ልጄ ትከሻዬ ላይ ታለቅሳለች፡፡ ይህ ሁኔታ ስሜቴን ይቀሰቅሰዋል፡፡ ምክንያቱም ከአመታት በፊት ይህንኑ ዓይነት በሕይወቴ አልፌበታለሁ፡፡

 

በዚህ ፊልም ላይ ዋናው ነገር ጁሊ አንድሪውስ ልቧን ገልጻ ማሳየቷ አይደለም፡፡ አላማው ከኢኮኖሚና በጣም ልዩነት በአንድ ተራ ቤተሰብ ውስጥ ከሟታየው፣ ውጪ ስላለው የጋራ ችግር፣ የቤተሰቡ አባላት በውስጣቸው ስላለው አስቸጋር ግንኙነት፣ ማንም ሰው ሌለያቸው የሚችለውን ሁኔታዎች መግለጽ ነው፡፡ በማለት በፊልሙ ማሰላለፍ ስለፈለጉ መልዕከት አስረክታለች፡፡

 

የፊልም ቀረጻው በሚሊቡ ቤታቸው ውስጥ መደረጉ የምቶት ጉዳይ ወይስ የበጀት? ተብላ ለተጠየቀችው ስትመልስ፣

 

በጀትም አንዱ ነገር ነው፡፡ ዋናው ምክንያት ግን ብሌክ ከአልጋው እንደወጣ የሥራው መድረክ ላይመገኝትን ያፈቅቀራል፣ የሱ ስንፍናም የአገልግሎትና የመሳሪያዎች የሚያሟላ ድርጅት (ሎጂስቲክ) ችግር በቆንጆ መንገድ አቃሏል፡፡

 

ኤስ ኦ ቢ የተሰኝው ፊልም የተቀረጸውም ከመኖሪያችን ዝቅ ብሎ ባሰራው ቤት ውስጥ ነበር እናም የሚያዝናና ነገር ነበር፡፡

 

ያ ፊልም ልክ እንደኛ ዓይነት ስለሆነ ቤተሰብ ታሪክ ስለነበር  የሚወራው በምንኖርበት ቤት ውስጥ ብንሰራው ለታሪኩ መዋጣት ትልቅ ግልጋሎት ይኖረዋል በማለት ስላሰብን ነው ብላለች፡፡

 

የፊልም ዝግጅት ክፈል ሠራተኞች ለረዥም ጊዜያት በመኖሪያችሁ አካባቢ መሆናቸው ችግር አልፈጠረባቸሁም? የሚል ጥያቄ ቀርቦ ነበር፡፡

 

አይደለም፣ ሠራተኞች በጣም ጥሩ ናቸው፡፡ በእርግጥ ወጥ ቤት ውስጥ ወይም መኝታ ቤት ውስጥ እንዳ ሰታወቁ ቀላል አይደለም፡፡ ስንተኛም በኤሌክትሪክ ገመዶችን ዘለን ሌሎችንም ዕቃዎች በማለፍ ነው ወደ አልጋችን የምንሄደው፡፡ ነገር ግን ቀረታ ስምንት ሳምንታት ብቻ ነበር የፈጀው፡፡ ሥራቸውን ጨርሰው ሲሄዱ ዕቃውን በሙሉሉ የነበረበት መልሰውና አስተካክለው ነበር፡፡ ሁለቱ ትንንሽ ልጆቼ የተዘናኑበት ጊዜ ነበር፡፡ ምክንያቱም ልክ በፊልም ላይ ሁሉጊዜ ጠዋት ላይ የምሳ ጋሪ ቡና፣ ኬክና ትኩስ ችሎሌት ይዞ ስለሚመጣ ወደውታል፡፡ እኔ ሳላይ ቀስ ብለው ኬክ ይሰርቁም ነበር፡፡ ስትል መልሳች ጁሊ፡፡

 

አዲሱ ፊልምሽ                  /ለሁለት እንደ አንድ በአንድሬ ኮንቻሎቨስኪ የተዘጋጀ ነው፡፡ ነገር ገን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከባለቤትሽ ጋር ነበር በተጠናከረ ሁኔታ የምትሰሪው፡፡ የምርጫ ጉዳይ ሆኖ ነው?

 

እንዲህ አይደለም፡፡ በጣም ጥሩ የባሕርይ ድርሻዎት የሚቀርቡልኝ ከባሌ ነበር፡፡ አንድ ሰው መጥቶ ቪክቶር ቪክቶሪያን ቢሰጥዎ አይ አልፈልግም አመሰግናለሁ አይሉትም፡፡ ብሌክ በጣም ደግ ሆኖ እነዚህን ባሕርያት እንድጫወትባቸው ሲሰጠኝ አልፈልግም ብዬ ብመልሳቸው በጣም ጅል ሆንኩ ማለት ነው፡፡ ባሁን ጊዜ ጥሩ የፊልም ጽሑፍ ማግት ቀላል አይደለም፡፡ ከዚህ ጋር አብረን በመስራታችን በጣም ደስተኞች ነን፡፡

 

ለሁለት እንደ አንድ በሚለው ፊልም ላይ ከኮንቻሎበስኪ ጋር ስትሰሪ ልምድሽ እንዴት ነበር?

 

ከሁሉም በፊት የፊልሙ ጽሑፍ ቀንጆ ነበር፡፡ በተለይ ለሴት፣ በዛ ታሪክ ላይ የሆነ ጥልቀት ያለው ነገር አለ፡፡ በከባድ ሕመም ምክንያት ሙዚቃ ለማቆም የተገደደች ቫዬሊ ተጫዋች ታሪክ ነው፡፡ ለዚህች ባሕርይ ተስማሚዋ እኔ ነኝ ውይ?  በማለት እራሴን መላልሼ ጠይቄያለሁ፡፡ የራሴ ጥርጣሬዎች ነበሩኝ ታሪኩ በጣም ኃይል አለው፡፡ ጠቆር ያለና አሳዛኝ፣ እናም እስካሁን ከተጫወትኳቸው ባህርያት የተለየ ስለ ነበር ለኔ በተዋናይነቴ ድንቅ ፈተና ነበር፡፡

 

ሜሪ ፓፔንስ እና የሙዚቃ ድምጽ በተሰኙት ፊልሞች ተጫውተሻል፡፡ በሌላ የሙዚቃ ፊልም ውስጥ ትሳተፊያለሽ በቅርቡ ወደ ፊት?

 

አዎን በማለት መልስ ብሰጥ አመኝ ነበር፡፡ ያለዕድል ሆኖ ገን እውነት አይደለም በሙዚቃ ፊልሞች በኩል ያለው ችግር ብዙ የገንዘብ ወጪ ማስወጣታቸው ነው፡፡ ከአስርና አስራ አምስት ዓመታት በፊት በነበረው ደረጃ እንኳን የሙዚቃ ድምጽ የሚለው ፊልም ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል፡፡ ዛሬ ሁለት ሦስት እጥፍ ያስፈልገዋል፡፡ የፊልም ስቱዲዮዎቸም ኃላፊነቱን መውሰድ አይደፍሩም፡፡ ሌላው ምክንያት የሙዚቃ ፊልሞች ስልት ባሁኑ ጊዜ ተለውጧል፡፡ በፊልም ላይ መነሻ ሳይኖር መዝፈን የሣይቻልነበት ሁኔታ ነው፡፡ ካባሪት እና ቪክቶር ቪክቶሪያ በመሳሰሉት ፊልሞችና በሙዚቃ መሐል ተፈጥሯዊ ቁርኝት አለ፡፡ በግል ስሜት የሙዚቃ ፊልሞች እንደገና እንደውም በፊት ከነበረው ሙዚቃ በበለጠ ሁኔታ መስራት እንደጀመረ ይሰማኛል፡፡ ምናልባትም ከመጀመሪያው እስከመጨረሻ ሙዚቃ ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ ቢያንስ እኔ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

 

ለምን እስከዛሬ ድረስ የሙዚቃ ሸክላ አላሳተምሽም?

ምክንታቱ ሰዎች እንደ ሊንዳ ሮንሰታድ ወይም ባርባራ ስትሬይሳንድ ራሴን የቻልኩ ዘፈኝ እንደሆንኩ የሚገምቱኝ ስለማይመስለኝ ነው፡፡ እንደ ሜሪ ፖፒንስ እና የሙዚቃ ድምጽ ውስጥ እንዳለቸው ሚሊ ባህርያት ዓይነት ጋር ይወስዱኛል፡፡ ከሙዚቃዊ ፊልሞች ባሕሪያት ነጻ የሆንኩና ራሴን የቻልኩ ዘፋኝ አድርገው ሰዎች እስኪያስቡ ድረስ ብፈልግም ሸክላ አላስቀርጽም፡፡ ለገና ጊዜ የታተመ ማንዲ የተባለ የልጆች ዘፈኖች ቴፕ አስቀድቻለሁ፡፡

 

ሚስት፣ እናት ተዋናይ፡፡ በዚህ ሁሉ ግዴታሽ በግልሽ ሕይወት የተጫወትሻቸውን ባሕርያት በአግባቡ ለመጫወት እንዴት ቻልሽው?

 

በእርግጥም ሁልጊዜ ብዙ የሚሰራ ነገር አለ፡፡ ጆአናና አሚ ለተባት የ11 እና 12 ዓመት ዕድሜ ሕጻናት /ከሕጻንነታቸው እኔና ብሌክ ያሳደግናቸው ናቸው/ ጥሩ እናት ለመሆን እክራለሁ፡፡ የሳምንቱን ብዙ ቀናት ከጠዋቱ በ12 ሰዓት አነሳና ቁርስ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ በ1፡30 ላይ በት/ቤታቸው አውቶብስ አሳፍራቸዋለሁ፡፡ ከዚያም ወደ ቢሮዬ እሄዳለሁ፡፡ ወይንም ወደ ስቱዲዮ እንዳንዳ ከጋዜጠኞች ጋር ሥራ ይኖረኛል፡፡ ስዊዘርላንድ በሚገኝው ቤታችን ከሆነ ደግሞ የበለጠ አዝናኝ ነው፡፡

 

በደንብ ከታሰበማ አልፎ አልፎ የጽሑፍ ሥራ፣ እንዳንዴ ዘፈኝ መዝፍን ከብዙዎች አንድ ቀን ፊልም መስራት እና በዚህ ጊዜ ሚስትና እናት ለመሆን መመክር እንግዲህ ሚስት በቤት ውስጥ ያለባትን የሥራ ግዴታዎች ግምት ውስጥ በማስገባት የሐኪም ቀጠሮ፣ ከጥርስ ሐኪም እና ከልጆቼ አስተማሪዎቸ ጋር መገናኝተ ብቻ የየቀኑ ፕሮግራሜ ሙሉ ነው በእርግጥም፡፡

 

በሜሪ ፖፒክስ የምትታወቀው ጁሊ አንድሪውስ የአራት ፊደላት ቃላትን ስትናገር በካሜራ ፊት ልብስ ስትቃያይር ማየት የሚያስደንቅ ትዕይንት ነው፡፡

 

ምናልባት ጁሊ ሜሪ ፖፔንስ እንዳልሆነች ተመልካች  እንዲገባው ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው ብላ ታስባች ይሳካለት ይሆን?

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ጆአን ኮሌንስ

ሪትዝ ሆቴል በለንደን የሚኖሩ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ የማኅበረሰብ አባላት ምሳ የሚበሉት ነው፡፡ ባሁኗ ደቂቃም ጆአን ኮሊንስ በአርማኔ የተሰፋውን ቤት ለብሳ ከወደ ጥግ በኩል ያለ የፀሐይ ብርሃን ወደረፈበት ጠረጴዛ የፊልም ኮከብ ተዋናዮች የሚያደርጉትን የፀሐይ መነጽር  ዓይኗ ላይ አድርጋ ታመራለች፡፡ በአካባቢ ጠረጴዛዎች ላይ የሚመገቡት ሰዎች ሰላምታ ስትሰጠኝ ይመለከታሉ፡፡ ይህች ያሁን ጊዜ የቴሌቪዢን ጣኦት ወደፊት የት ትደርሳለች እያሉ መብሰልሰላቸውን ግን አያቆሙም፡፡ ሙያዋን ግን መስቀልያ መንገድ ላይ ነው ያለው፡፡

 

ጆኦን ዳይናስቲ ከሚለው ፊልም በኋላ ታዋቂነቷ ያሻቀበውን ያህልም አየወረደ ይመጣል፡፡ መልኳ፣ ቀመናዋ ውበት የተላበሰ ሲሆንም የቀድሞ ባልዋንና የሥራ ኃላፊዋን እርዳታ አተገኝውም የጋብቻ ወረቀታቸውን ቀደዋልና፡፡

 

ዕውቅናን፣ ሀብትንና ውበትን ባተረፈችበት ጊዜ ከአራት ባሎች ሶስት ልጆች፣ 58 ፊልሞች በኋላ የሚቀጥለው ምን እንደሆነ እያሰበችበት ነው፡፡

 

ከአባባሏ እንደተረዳሁትም ዳይናስቲ የሚለው ተከታታይ ፊልም ለሷ በጣም ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግንአሁን በትክክል መስራት የምትፈልገውን ለመስራት የምትችልበት የሕይወት ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡ የፊልም አቀራቢው አሮን ስፔሊንግ የሚላትን ሳሆን እሷን ሳይሆን እሷ ለራሷ የፈለገችውን፡፡

 

ጆአን ብዙ ሀሳቦ አሏት የቴሌቪዥን ፊልሞች፣ የራሴ የሆኑ ተከታታይ ፊልሞች በለንደን መድረክ ላይ ምናልባትም ኖኤል ካዋርድን የመጀመሪያዋን ረዥም ልብወለዷን /ሶስተኛ መጽሐፏ ነው/ጽፈለች፡፡ እናም ሌሎች አዳዲስና በዛያሉ የጆአን ኮሌንስ የምርት ውጤቶችንም ጀምራለች፡፡ ልብሶችንና ሽቶዎችን ጨምሮ፡፡

 

የዛሬው ከሠዓት በኋላም የ5 ወረ ዕረፍት ጊዜዋ አጋማሽ ለይ ነው፡፡ ለንደን ውስጥ የራት ግብዣ ትከፍላለች ይህንንም ሰታደርግ ለጤንነቷ የሚበጃትን የሀኪም ትዕዛዝ በመጣስ ነው፡፡ 55ኛ ዓመት የልደት በዓሏንም ሞሮኮ ውስጥ ለሳምንታት ስታከብር የቅርብ ጓደኞቿ ተዋናይ ጆርጅ ሀሚልተንነጋዴው ማልኩም ፍሬዘር እና ቢል ዊጃንስ ተገኝተዋል፡፡

 

ይህ የዕረፍት ጊጊ ለጆአን ብዙ ያረፈችበት አይደለም፡፡ በዛ ያሉ ማባራዊ ግኑኝነቶች ነበሯት፡፡ በቤልግራቪያ ለሚገኝው አዲስ ለተከራየችው ቤቷም የ18ኛው ክፍለ ዘመን የፈረንሳይ የቤት ቁሳቁስ በመግዛት ፈታ አላገኝችም፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ፍቼ በሆሊውድ ዓይነት

የቴሌቪዥኗ የንብ ንግስት በነዚህ ጥቂት ዓመታት ውስጥ በቀፎዋ ብዙ ችግሮች አይታለች፡፡ ሰዎችን ብዙ እንዳታምን ትምህርት ስለመውሰዷም ትናገራለች፡፡

 

በዕውነተኛው ሕይወቷ ውስጥ ሰዎች በሷን ከአሌክሲስ ጋር ማመሳሰላቸው ይገርማታል፡፡ ድብቅ፣ የማይታመን፣ ባህርይ እንዳላት ዓይነት ሴት፣ እሷ ግን ፍፁም ተቃራኒዋ ናት፡፡ ምክንያቁም በስሜቷ የምትመራ አፍቃሪና መንግድ ከመቫገሯ በፊት እንኳን ግራና ቀኝ ማየጥ እንደማትችል ዓይነት ልጅ ናት፡፡ በቅርቡ ካጋጠማት ሁኔታም በጣም ብዙ ነገሮች መማር እንዳለበት ታስባለች፡፡

 

ያጋጠማትም ነገር የትዳሯ መፍረስ ነው፡፡ ከፒተር ሆልም ጋር ለ13 ወራት ያህል በባልና ሚስትነት ቆይታ ፍቺው ከብዙ ክርክር በኋላ በካሊፎርኒያ የፍቼ ሕግ መሠረት ፀድቋል፡፡

 

ፒተር ሆልም በጋብቻቸው ወቅት ያገኝቸውን 5 ሚሎዬን ብር እኩል ለመከፈልና የፍቼው መጨረሻ እስኪፀድቅ በወር 80,000 ዶላር እንድትሰጠው ጠይቅ ነበር፡፡

 

ነገሩ በፍርድ ቤት በመታየት ላይ እንዳለ ልክ በሶስተኛው ቀን የጆአን ጠበቃ ከፔተር ሆልም ጋር ከጋብቻቸውም በፊት ሆነ በትዳር ላይ እያለም ፍቅር ነበረን ብላ የመሰከረች የ23 ዓመት ተዋናይ ይዞ ቀረበ፡፡

 

ይህች በትውልድ ኢጣሊያናዊና ኢራናዊ የሆነች ቆንጆ እንደገለፀችው  ከሆነፔተር የፍላጎት አባባ ብሎም ቅጽል ስም እንዳወጣላት ተናግራለች፡፡ ከጆአን ጋር የነበረው ትዳርም የህብት ማግኛ መንግድ ነው ብሎ እንደነገራትና ከሱም ልጅ እንድትፀንብለት መጠየቀን ለፍርድ ቤት አስምታለች፡፡ ከዚህ በኋላ እንባዋን አንዥቅዥቀቸውና የምስክር መቀመጣ ወንበር ላይ ራሷን ስሳተች በቃሬዛ ለሕህምና እርዳታ ከፍርድ ቤቱ ወጥታለች፡፡

 

ፍርድ ቤቱም የፒተርን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎበታል፡፡ በትዳር ላይ እያሉ ገቢያቸውን ይቆጣጣር ስለነበር ለዚህ ክፍያ እንዲሆነውም ጆአን 1,180,000 ዶላር ከፍላዋለች፡፡

 

በሕይወቷ ውስጥ ያለፈ ወንዶች

ከሆልም በፊት ከነበሩት ሁለት ባሎቿ ጋር የገንዘብ ድርድር ማድረጓ የጆአን መጥፎ ዕድልን ያመለክታል፡፡ ያለፈ የጎደፈ በሚለው በ1978 በታተመው የራሷ የሕይወት ታሪክ ላይ ስለነዚህ ጋብቻዎች ስትግልጽ፣ ባል ቁጥር 1 ብሪታሪያዊው ተዋናይ ማክስዌል ሪድ በአደንዛዥ

 

ዕድ አድክሟት የግዳጅ ሩካቤ ፈጽሞባታል፡፡ የ17 ዓመት ነበረች፡፡ በኋላም ለአንድ አረብ ሼ ለአንድ ሌሊት ሊያከራያት ሞክሮ ነበር፡፡

 

የ36 ዓመት ሰው ያጣ የነጣ እንዴ እንደሚሆን ምክንያቱን አትወቀው እንጂ ከ5 ዓመታት በኋላ በ1957 ሲላያዩ ለሕይወቱ ትርጉም አጥቶለት ነበር፡፡

የዘፈን ደራሲና ዘፋኝ የሆነው ሁለተኛው ባሏ አንቶኒ ኒውላይ ታራና ሳቻ የሚባሉ ልጆቻቸውን መንከባከቢ ገንዘብ ከፍሏል፡፡ ነገር ግን የሶስተኛዋ ልጇ ካቲ አባት የሙዚቃ ሸክላ አዘጋጁ ሮን ካስ በ1984 ከጆአን ጋረ ሲፋቱ የገንዘብ ችግር ውስጥ ተዘፈቶ ነበር፡፡ በሞት ከዚህ ዓለም እስከተለየበትም ጊዜ ሁለት ዓመት ሙሉ ከካንሰር በሽታ ጋር ላደረገው ትንቅንቅ ጆአን በታማኝነተ ረድታዋለች፡፡

 

ጆአን ስለዚህ ሁኔታ ስትናገርም 4 /አራት/ ፍቼዎች አራት ስህተቶች አይደሉም፡፡ በትክክል ሁለት ብቻ ነበሩ ስህተቶች ማክሰዌል ጋር የነበረው ልጅ ስለነበርኩ ስህተት ነው፡፡ ከቶኒ ጋር ያልፈውን አንደስህተት አልቆጥረውም ምክንያቱም ሁለት ውብ የሆነ ልጆች ከሱ አፍር ቼአለሁ፡፡ ከረንም ጋር እንዲሁ ቢያንስ ለመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ዓመታት በአደንዛዥ ዕድ ልማድ ተለክፎ ፀባይ ሳይቀየር፣ ፒተር ግን ትልቅ በጣም ትለወቅ ስህተት ነው፡፡ በጣም ጥንቁቅ እንድሆን አድርጎኛል፡፡ የፍርድ ቤት ካሳ ከከፈልኳቸው ወንዶች ጋር ሁሉንም የወንድ ዘር የደመርጎ እንዳ ይመሰላቸው፡፡ ነገር ግን ካሁን በኋላ ወንዱ ከኔ የበለጠ ገንዘብ ያለው ካልሆነ በቀር በጋብቻ አልተሳሳርም አለች አንድ መልከመልካም አስተናጋጅ እየተመለከተች፡፡

 

እያቆጠቆጠ ያ የስነ-ጽሑፍ ሙያ

/ሁነኛ ጊዜ/ ከሚለው መጽሐፍ ሕትመት ጋር እሷም ወደ ከፍተኛ ግምት ያለው ደራሲነት እየታጨች ነው፡፡ የአሌክሲስን ገፀ ባሕርይ ለማግኝት ሶሪያ ሎሪንግ ከመሳሰሉ ዕውቅ ተዋንያን ጋር ተወዳድራ የማሸነፍ ልምዷን በመዋስ ጆአን 4 የልብ ወለድ ተዋንያን አንዷ ሌላዋን ለማጥመድ እና ልክ ሽብር ተኞችን መስለው የባሕርይ ድርሻ ለማግኝት መራኮታቸውን ትነግረናለች፡፡

 

የጆአን መጽሐፍ ብዙ አንባብያን ሊኖረው ይችላል፡፡ እነሱም በመጽሐፍ ውስጥ የተካተቱት ባሕርያት የትኞቹ በሕይወት ያሉትን ይመስላሉ በማለት ግምት መውሰዳቸው አይቀርም፣ በተለይ የአራቱ ተዋንያን ባሕርይ፣ አንደኛዋ ከጆአን ባሕርይ ጋር ተመሳስለ ይሆን የተቀረፀችው፡፡

 

ምናልባት አራቱም ከኔ በትንሹ የወረሱት በሕርይ አለ፡፡ ነገር ግን ስለእውነት ጭንቅላቱ ውስጥ የተፈጠሩ ናቸው፡፡ እህ ጃኪ ይህንኑ ጠይቃኝ ነበር ምክንያቱም እሷ የምትፈጥራቸው ባህርያት በእውነተኞች ሰዎች ላይ /እሳ በምታውቃቸው/ የተመረኮዙ ናቸው፡፡ ተላለች፡፡ ጆአን ኮሊንስ /እህቷ ጃኪ፣ ፍቅረኛሞችና ቁማርተኞች፣ በሆሊውድ ያሉ ሚስቶች በሚሉት መጽሐፎቿ ትታወቃለች፡፡/

 

ሃያሲያን የእህቷን የአጻጻፍ ስልት ወይም ደግሞ የጉስት ፀሐፊ እንዳላት ሊያወሱ ይችሉ ይሆናል፣ አሷ ግን የእህቷን መጽሐፍ ለሁለት ዓመታት ያህል እንዳ ሳነበበችና የጎስት ፀሐፊዎች እርዳታም እንደሌላት፣ ስለመጽሐፏም ከእህቷ ጋር ተነጋግራ እንደማታውቅ በመግለጽ ማንኛውንም ዓይነት ውንጀላ ለፍርድ እንደምታቀርብ ዝታለች፡፡ አንድ ሰው እንዳጭበርበረች ዓይነት ማረጋገጡን ስለተናገረ ለንደን ውስጥ ከ20,000 ፖውንድ በላይ አስቀጥታዋለች፡፡ ጃኪ የመጻፍ ተሰጥኦዋን የወረሰችው ከወላጆቼ ነው፡፡ እና እኔም ወርሻለሁ፡፡ ነው የምትለው ደራ ሴና ተዋናይዋ ጆአን ኮሊንስ፡፡

 

ጃኪ ስለታላቅ እህቷ ስትናገር፣ ማንም ሰው በህይወቱ አንድ ጊዜ መጽሐፍ መጻፍ ይፈልጋል፡፡ የጆአን ደራሲነግ ግን ለኔ አይታየኝም፡፡ ብላለች፡፡

 

ጆአን በአንግሊዝ አገር ያፈራት ጅግኒት ስትሆን ለባለሱቆችም የኞጆአሊ ናት፡፡ ዝናዋ ከአህጉር፣ በወንጆችም ሆነ በሴች ወገን በሁሉም የዕድሜ ክልል ታዋቂ ሆናለች፡፡ ይህ ሁሉ ምናልባትም በጥረቋ የተገኝ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ካለ የፊልም ሰራተኝነት ተገልላ ቤቷን ማደራጀት፣ ለየት ያሉ ስራዎችና፣ የቤትን ውስጥ ውበት በባለሙያነት ደረጃ ተያይዛው ነበር፡፡ በ70ዎች ዓመታት በደረሰባት የገንዘብ ችግርም ጎረምሳው በሚለው ሮነካሳ ባዘጋጀው የእህጸዋ ድርሰት ላይ ተካፍለች፡፡ ብዙ ገቢ አስገኝናም እሷም ሙያውን እንደገና ቀጠለች፡፡

 

በ1980 ግን ካቲ የጆአን ሴት ልጅ በመኪና አደጋ የአንጎል ሕመም ስላሰቃያት ለልጆ አልጋ አጠገብ ሳትለይ 47 ቀናት ያለእረፍት አስታማታለች፡፡ ካትተሸላት፡፡ ይህም ለሁለተኛው መጽሐፍ መነሻ ሆናትና ካቴ ለሕይወት ትግል የሚለው መጽሐፍም በ1981 ለሕትመት በቃ፡፡ ከዚያም ዳይናስቲ የሚለው ፊልምም በዛው ዓመተ ተጀምሮ ጆአንም ኮንትራቷን ትፈራረመች፡፡

 

ጆአን መልኳን ሲያዩት ከ40 የተለለች አትመስልም፡፡ ነገር ገን ወጣትነትን ማቆያ ቀመር ያላትም፡፡ ጥሩ ጂኖች፣ መልካም ዕድልና ደህና የአጥንት አቀማመጥና ቅርጽ እና አስተዳደጊ ይመስለኛል፡፡ ታዋቂ ባልሆንም እና ሰዎች ትኩረት ባይሰጡኝም እንኳን የትም ቦታ በደንብ ሳለብስና ሳልዘጋጅ ለመውጣት አላስብም፡፡ በማለት ስለገፀትዋ ትናገራለች፡፡

 

ረዳቴ የምትለው ሲጋራ ካነሳችም በኋላ ከ40 ዓመቴ በኋላ ያለውን ኃይሌ አልቀነሰም፡፡ በ28 ዓመቴ እሮ የነበረውን ዓይነት ዘይቤ ነው አሁንም የምከተለው፡፡ በወር ሁለት ጊዜ ከሎስ አጀለነስ ወደ ለንድን የአይሮፕላን ጉዞ አደርጋለሁ፡፡ መጣጣት አችላለሁ፡፡ ማኅበራዊ ሁኔታዎች ላይ አሳተፋለሁ፡፡ ስትል እርጅናዋን በግርማ ሞገስም ባይኞን በፍላጎት እንደተቀበለችው ጠቁማናለች፡፡

 

ስለ ዕድሜዎ የገል ሕይወቷ አስተያየቷን በማራዘ፣ እንዲህ ትላለች፡፡ ወጣት መምሰል እስከተነሰ ድረስ ለመናገር ቢብድም አንተ ነኝ ብላ የምታስበውን ያህል ነው አባቴ በቅርቡ ሲሞት የ85 ዓመት ዕድሜ ነበርው፡፡ አስቸጋሪ ሰው ነበር፡፡ ተንኩለኛ ሰው፣ እናም ማድረግ የሚፈለገውን ሁሉ አድርጓል፡፡ በ83 ዓመት ዕድሜው ታሞ እስኪተኛ ድረስ ደስተኛ ስለሆነ በጥሩ አቋም ላይ ነበር፡፡ በሕይወቴ እኔም ደስተኛ ነኝ፣ በምስራው ሥራ አደሰታለሁ፡፡ ልጆቼን እወዳለሁ፡፡ ጥሩ ልጆች ሆነዋል፡፡ አልፎ አልፎ ችግሮች አሉ፡፡ ልቼን እወዳለሁ፡፡ ጥሩ ልጆች ሆነዋል፡፡ አልፎ አልፎ ችግሮች አሉ፡፡ ባሁን ጊዜ ሰቻ ከኔ ጋር ነው የምትኖረው፡፡ የ15 ዓመት ካቲም ከኔው ጋር ነች ኮሌድ ለመግባት ዕቅድ አላት፡፡ ከዚህ በላይ ስለልጆቼ ባሌ ጀምሮ የግ ሕይወት አስቸጋሪ የሀነብኝ መጥቷል፡፡ ለምሳሌ ጋብቻን በሚስጥ እንዲሆን ተነጋግረን ነበር፡፡ ያም ሆኖ ፒተር የጋብቻ ፎቶአችንን ለጋዜጦኖች ሸጦታል፡፡

 

ባሏና ማናጀሯ ከሆነው ፒተር ጋር ከቀተፈታች በኋላ ጆአን ዋና ወሳኔዎችን አራሷ አያከናወነች ነው፡፡ ብዙ ሠራተኞች አሏት ለውሳኜ የሚረዷት አስቸጋሪዎን ግ የራሷ ናቸው፡፡ ጊዜ ያድናል፡፡ ስህተቶችም የራሷ መሆናቸውን ታምናለች፡፡ የምትፈልገውን ነገር ለምስራት ፍላጎቷ ነው፡፡

 

የምሳ ሰዓት አለቀ፡፡ ሪትዝም በዶውን ቀረ እናም ሁለታችንም የእርካታ ፈገግታ ተሰዋወጥን፡፡ አንዳንድ ዕቃዎች ቦርሳዋ ውስጥ እየከተተች የምኖረው ሕይወት  ይህ ብቻ ነው፡፡ እናም እነዚህን ቃላቶ ሁል ጊዜም አሰታወሳቸዋለሁ፡፡ ሕይወት ምኞት ብቻ መቋደስ የማይቸሉት የእራት ግብዣ ነው፡፡ እኔም በሕይወቴ ካሁን በኋላ እንደማልሞ ልግለጽልህ እንዲህ በማለት አጠቃለለች፡፡

 

ከሌፍ ጃህር

 

 

 

 

 

 

ለምለሟ ሜሪል

ይህንን ርዕስ የሰጣት በኬሪ ፊሸር ግማሽ የሕይወት ታሪክ ጠርዙ ላይ ካሎት ፖስት ካርዶች የሚለው ፊልም ላይ በምትጫወተው ባሕርይ ለ9ኛ ጊዜ ለአስካር የታጨችው ተዋናይ /ሁለት ጊዜ ማለት ከራመር በክራመር ላይ እና የሶፊ ምርጫ በሚሉት ፊልሞች ኦስካር ተሸልማለች፡፡/ ሜሪል ስትሪኝ በሎስ አንጀለስ ፎር ቢዝነስ ሆቴል ልዩ ክፍል ያለፈው ታህሳስ ወር ላይ አግቶ ያነጋገራት ካርሎ ቢዚዬ የተባለው ጋዜጠኛ ነበር፡፡

 

የማትረብሽ፣ ጥራትና፣ ጎዝና ለዚህች አሜሪካዊት ተዋናይ በግል ሕይወቷም ሆነ በፊልም ሥራ ሙያ ስኬትን ያስገኙላት ነገሮች ናቸው፡፡

 

ሜሪል ስለዚህ ሁኔታ ስትገልጽ ተዋናይ ነኝ ስለዚዘህም ፍራቻ አለብኝ፡፡ ይህ ፍራቻን ከተጠቀምኩት የሆነበውን ድርሻ ለመጫወት ያሰችለኛል፡፡ ድክመት የአንድ ተዋናይ ጠንካራ ጎኑ መሆን ይችላል፡፡ ብላም ቆም አረገች ንግግሯን፣ አየር ወደ ውጪ አስወጥታ ፈገግ አለች፡፡

 

ራሷን ለመቆጠብ ስትጥርም ትታያለች በቃል መጠይቃ ጊዜ ከተፈቀደው በላይ በመሄዷም ብዙ ያወራች እየመሰላት ደጋግሞ ይቅርታ ትይቃለች ይህም ግርማ ሞገስን ጨምሮላታል፡፡

 

ጠርዙ ላይ ካሉት ፖስት ካርዶች የሚለው ፊልም በጣሊያን ውስጥ መታየት የሚጀምረው ገና በየካቲት ነው፡፡ አሁን መችሎሎ ለምን አስፈለገ ተብላ ለተጠየቀችው ጥያቄም ስትመልስ ምክንያቱም አራተኛ ልጄን ስለምጠብቅ ነው፡፡ አሁን የሦስት ወር ቅሪት ነኝ፡፡ ካገና በኋላም ሙሉ በሙሉ ለእርግዝናዬ ጥንቃቄ ልወስድ አፈልጋለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ እንነጋገርበት የነበረውንና እኔም ለመስራት ጉጉት ያደረብኝን ካጃክ ኒኮለስሰን ጋር ሆኜ የምተውንበትን ፊልም እንኳን አሁን ፈቃደኝነቴን አልገልጽኩም፡፡ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እርግዝናዬ ያሰታውቃል፡፡ በሰኔ አካባቢም ልጁ ይመጣል፡፡ አሁን ለጊዜው ዕረፍት ትፈልጋለሁ፡፡ ስለምንም ነገር ሳላስብ ቢያንስ ለአንድ ዓመት አቆያለሁ፡፡ ብላለች በእምነቷ የፀናች ሆና፡፡

 

እንዲሁ በግንባር ፊት ለፊት ስትታይ ሜሪል ስክሪን ላይ ከምትታየው የበለጠ ቆንጆ ናት እናም ይህንኑ ሲነግራት ፈገግ በማለት ብዙ ጊዜ ሰዎች እንዲህ ይሉል፡፡ እኔም በእንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ እንዲት እንደምቀበለው ግን አላውቅም፡፡ ለነገሩ ምን ማለት ነው? በስክሪን ላይ አስቀያሚ ነኝ ማለት ይሆን?

 

እባክሽን ማለት የፈለኩት ይግባሽ፡፡ ነገር ግን አንዳች ዓይነት በአእምሮ የበለሰለች ተዋናይ በዚህ ሁኔታ ለምን ተጨነቃለች?

 

በእርግጥ እጨነቃለሁ፡፡ እኔም እንደማንኛውም ዓይነት ሴት ነኝ፡፡ አትቸገር፡፡ በጨለማ ውስጥ ጩኽጽ ለሚላ ፊልም 20 ፖውንድ ያህል ክብደት መጨመር ግድ ሆኖብኝ ነበር እናም የራሴን መልክ እንደነገሩ አድርጌዋለሁ፡፡ ለአንድ ተዋናይ ከባሕርዬ ጋር በደንብ መመሳሰል በጣም አስፈላጊ ነው በጠርዙ ላይ ካሉት ፖስት ካርዶች በሚለው ፊልም ላይ አስቀያሚ እንዳልንኩ ተስፋ አለኝ፡፡

 

በዚሁ ፊልም ላይ የምትጫወተው ባሕርይ ተዋናይዋ እንደዛዥ ፅድ ከወሰደች በኋለዳ መድረኩ ስትመለስ ዳይሬክተሩ መልኳን እንዳበላሻችው ሲያማርር ትሰማለች፡፡ እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች በግል ሕይወትሽ አጋጥሞሽ ያውቃል?

 

አዎ ፖስት ካርዶች የሚለው ፊልም የእውነተኛው ሆሊውድ ሕይወት ቅንጫቢ ነው፡፡ ሁለት ደህና ገቢ ያስገኙ ፊልሞችን እንደሰራሁ አንድ ወጣት የፊልም አቅራቢ ዝነኛ ከሆነው አባቱ ጋር ስለፊልም ለመወያየት አነጋገረኝ፡፡ ለመገመት አስቸጋሪ ላይን ይችላል ግን ስም አልጠቅስም፡፡ ጣሊያኖች ናቸው፡፡ በዝነኛውው አባት ምዳት ያለው ቢኖ ተገናኝንና ስለኔ ሁሉንም ነገር ማወቅ ፈለገ፡፡ ትህትና አልጎለውም ነገር ግን አንድ ወቅት ላይ ወደ ችል ዞሮ፣ ለዚህ ፊልም ብቁ አይደለችም፡፡ አስቀያሚ ናት፡፡ ትክክለኛ ቆንጆ ፈልገህ አምጣልኝ፡፡ ይለዋል፡፡ በዩኒቨርስቲ ውስጥ ትንሽ ጣሊያንኛ ተምሬያለሁ፡፡ ይህም ምን እንደሚያወሩ ለማወቅ አስችሎል፡፡ ታዲያ እኔም በጣሊያንኛ አሁን ስለኔ ያልከው ነገር በጣም የሚረብሽና የሚጋፋ ነገር ነው፡፡ ካልኩ በኋላ ተነስቼ ወጣሁ፡፡

 

ቀራጭ ስጋ እንደሆንኩ ያህል ነበር በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰማኝ፡፡ ቢያንስ ለአንድ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ያላለፈች የሆሊውድ ተዋናይ አትገኝም፡፡ ከአፍሪካ ውጪ የሚለው ፊልምም ላይ ይህን ዓይነት ገጥሞኛል፡፡ የፊልም አዘጋጁ ሲድኒ ፖላክ ለአይዛክ ዲኒስን ባይርይ ድርሻ በበቂ ሁኔታ ሴክሲ እንዳልሆንኩ አስቧል፡፡ እናም ተዋናይ መረጣ ሲካሄድ በስፖንጅ የተደረተ ጡት መያዣና ልዩ የሆነ ሚኒስከርት ለብሼ ተገኝሁ፡፡ ድርሻው ለኔ ተሰጠኝ፡፡ የዳኒቫ አነጋገር ችሎታዬም ከግምት ውስጥ ገብቷል፡፡ በዚህ ሙያ ውስጥ ግን አንድ ድርሻ የምትፈልግ ከሆነ ለአንዲህ ዓይነት ነገር መዘጋጀት አለብህ፡፡

 

ከአራት ዓመታት በፊት ሜሪል ስትሪኝ የድንቅ ተዋነይ ቨልማትን የቅርብ ጓደኛዋ ቬር ወስዳባታለች፡፡ በሁኔታው ብትገረምም የሼር ስኬት ሜሪልን አስደስቷታል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ነበር ሁለቱም ሴቶች ሲልክ ውድ በሚለው ፊልም ላይ ነበር የተሳተፉት፣ ሼርም በዚህ አጋጣሚ ነበር ሜሪልን ታማኝ ጓደኛ ያደረገቻትና ያቋረጥ ምክር ትጠይቅ የነበረው፡፡ የሽልመት ነገር ግን ተማሪ አሰተማሪውን መብለጡን አልነበረው የሚያሳየው፣ በቅርቡ ሜሪል ለመጫወት የምትመርጣቸው ባሕርያት ግምት ውስጥ ይገባሉ፡፡

 

በአንድ ወቅት በሙያዋ ለአንድ ፊልም ይከፍላት የነበረው ገንዘብ ወደ 4 ሚሊዬን ዶላር ነው የሚል ሪፖርተ ተዘግቷል፡፡ አሁን ግን እየቀነሰ መጥቷል፡፡ 7 ጊዜ የሚሆን ለአካዳሚ ሽልማት ታችታለች፣ ሁለት የኦስካር ሽልማጽ አግኝታለች፡፡ የኤሚና ቶኒ ሽልማቶችም ተጠቋሚ ነበረች፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን የሲኒማ አፍቃሪዎች አሁን ቤታቸው መቀመጡን እየመረጡት ነው፡፡

 

አስማተኛዋ ሜሪል ያሏት ሃያሲያን እንኳን በኮስታራ ባሕርያት አመራረጧ እየነቀፏት ነው፡፡ ፖውን ካኤል ጥሩ አርጋ እንዳሰፈረችው ሳቋ ቢጨምርና ስቃይዋ ቢቀንስ ኖሮ

 

የሜሪል ተከታዬ ፊልምም ለአደጋ ያጋለጣት ሲሆን በአውስትራሊያ የበዙ ሰዎችን ትኩረት የሳበ የፍርድ ቤት ጉዳይ ነበር፡፡ ፊልሙም ልጇን ገድላለች ተብላ ስለተወነጀለች እና ይተርካል፡፡ እና ሊንዳ ቻምበር ሌይን ከወንጀል ነጻ መሆኗንና የ9 ሳምንታት ዕድሜ ያላትን ልጅ የወሰዳትና የበላት በአውስትራሊያ ጫካ የሚኖር የዱር ውሻ እንደሆነ ተናግራለች፡፡

 

የፊልሙ ጽሁፍ የተወሰደለት መጽሐፍ ለሜሪል እንደተላከላት ማንበብ ጀምራ ለገፅ 60 በላይ አልዘለቀችም፡፡ በጣም ነው ያናደደኝ እንደውም ሆዴን በእርግጫ የተመታሁ ዓይነት ስሜት ነው የተሰማኝ ትላለች ሜሪል፡፡ በኋላም ድርሻዋን ወሰደች፣ ይህ ፊልም ግን በፊት ከሠራቻቸው የፈረንሳዩ ሳጅን ሚስት፣ የሶፊ ምርጫ እና ከአፍርካ ውጪ ከሚሉት ፊልሞች በጣም የራቀ ነው፡፡ እነዚህ ፊልሞ ነበሩ ኮከብ ተዋናይ ወደ ሞን ያቀረቧት፡፡ ኮከብ መሆን ግን የሜሪል ምኞት ሆኖ አያውቅም፡፡ ኮከብ? አለች ሜሪል በአንድ ቃለ መጠይቅ ላይ እኔ ኮከብ አይደለሁም፡፡ አንተ ከፈለከው ብቻ ነው ኮከብ መሆን የምትችለው፡፡ ባርባራ ስት ሬይሳንድ እና ሊዛ ሚኔሊ የፊልም ኮከቦች ናቸው፡፡ እኔ ግን ስለእውነት ያን አልፈልግም፡፡ በኔ የሙያ ይዞታም ልዩ የሆነው ይኽው ነው፡፡ ብላ መልሳለች፡፡

 

ሜሪል 43 ዓመት ዕድሜ ያላት ባለትዳር ስትሆን ቁጥብ ከሆነው ቀራጭ ባሏና ልጆቿ ጋር የቤተሰብ ይገህወት ደስታን እንደምትመርጥ ግልጽ አድርጋለች፡፡

 

ከሥራዋ ውጪ ኮኔክቲክት ነውስጥ 1.8. ሚሊን ዶላር በሚያወጣ ቤቷ ውስጥ ከቤተሰቧ ጋር አብዛኛውን ጊዜዋን ታሳልፋለች፡፡ በእርግጥ ለአንድ የፊልም ተዋናይ ወደ ገጠር ወጣ ብ ረጭ ባለ ቦታ መኖር ያልተለመደ ቢሆንም ሜሪልን እደንዛዥ ዕጾ፣ መጠጥ እና ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮች ይረብሻታል፡፡ የሆሊውድ ኑሮ ምንም ጊዜ ቢሆን ስቧት አያውቅም፡፡ ፖስት ካርዶች የሚለውን ፊልም ስትሰራ ለመጀመርያ ጊዜ ሎስ አንጀለስ ውስጥ ክሶስት ቀን በላይ ቆይታለች፡፡ ገንዘብ አፍ አውጥቶ የመናገርበትና በፊልም ሙያ ውስጥ ያለህ ደረጃ ነው አንተነትህን የሚያሳይህ፡፡ እዚህ ማለትም ሎስ አንጀለስ ቁመናህ፣ ዕድሜህ፣ መኪናህ ነው ግምት የሚያሰጥህ የሚል ዕምነት ስላላት ሜሪል እዚህ አካባቢ ስትሆን ከባሕር የወጣች አሳ የሆነች መስ ይሰማታል፡፡

 

የኔም ሆነ የልጆቼ የግል ሕይወት ለኔ ትል ትርጉም አለው፡፡ ስለኔ ቢያወሩ ወይም ማውራት ቢፈልጉ ምንም አይደለም፡፡ ነበር ገን ከቤተሰቤ አጠገብ አይድረሱሱ፡ እኛ የምንኖርባት ኮኔክቲከት ትንሽ ከተማ ስትሆን 5,000 ነዋሪዎች እንኳን አንሆንም፡፡ ዝና የሚያመጣው ገደብ የሌለው ደስታ ርቀው ልጆቼ ተገቢ ሕይወት መምሬት ይችላሉ፡፡ ዝነኛ ቤተሰቦች ስላላቸው ልጆቻችን ሳይሞላቀቁ በስርዓት እንዲያድጎ እኔና ባለቤቴ የተቻለንን ያህል እንጥራለን፡፡ በማለት ትገልጻለች ስለ ፍላጎቷ፡፡

ወደዚህ የገጠር ቦታ የተዛወሩት ጊው ዮርክ ከሚገኝው ሶሆ ዲስትሪክት በመልቀቅ ነው፡፡ ምክንቱን ስትዘረዝርም፣ ታዋቂ በመሆኔ በሕዝብ ትኩረት ሥር ፕኝ፡፡ ሰዎች ፀጉሬን ይዳብሱታል፡፡ ወይም ልብሌን ወይም ሌላ፡፡ እንዳንድ ሰዎች ምን ዓይነት ሳይዝ ልብስ እንደምገዛ ሳይመለከቱ ነጻ ሆኜ ገብቼ መመለስ አልችልም፡፡ 24 ሰዓት ሙሉ ስለራሴ ተጠንቅቄ ማሰብ ያስቸግረኛል፡፡ ስትል አስረድታለች፡፡

 

ሜሪል መሥራት የምትፈልገውን እንደምትሰራ ትናገራለች፡፡ የመወደደችውን ወይም በተወሰነ ደረጃ አስፈላጊ መስለው የታዩዋትን ምንም ያህል ለመሥራት አስቸጋሪም ሆነው ቢገኙ እነሱን ትመርጣለችች፡ ሠይጣን መለዕኪት የሚለውም ፊልም አስቸጋሪ ነው የሆነባት ይች በእንድ ወቅት የፊልሙ ሥራም በጋዜጠኞች ውክቢያ ሥርዓት ያላት ይህች ሴት ተዋናይ እንባዋ ፈንቅሏት ወጥቷል፡፡ የስትሪፕ ችግሮች ፊልሙ ከሚሰራበት ቦታ ጋር ብቻ የተያያዘም አይደለም፡፡ የዐውስትራሊያኖች የአነጋገር ዘይ ለማወጣትም ተችግራለች፡፡ የአነጋገር ዘዬዎችን በቁጥጥሯ ሥር ለማድረግ በምተነድፋቸው ስልቶች የምትደነቀው ሜሪል የሶፊ ምርጫ በሚለው ፊልም ላይ ላላት የባሕርይ ድርሻ ትክክለኛ የጉሮሮ አነጋገር ዘይቤ ለማጥናት ስትል የፖላንድና የጀርመን ቋንቋዎችን ለ3 ወራት ያህል በሳምንት 5 ቀን ተምራለች፡፡ የፊልም ቀረጻው ስራ ከመጀመሩ በፊት በተደረገ የጋዜጣዎች ጉባኤ ላይ ሜሪል የጋበዘቻቸው ሲናገሩ ለማድመጥ በመፈለግ እንደሆነ ነግራቸዋለች፡፡ በመቀጠልም የአውስተራሊኖች አነጋገር ዘዬ በጣም አስቸጋሪና ምናልባትም ካሁን በፊት ከሞከረቻቸው ሁሉ የበለጠ ከባድ እንደሆነባት ጠቅሳለች፡፡

 

የፊልሙ ቀረጻ ሲጀምር ግን ሜሪል ሁሉንም አስገርማለች፡፡ በቻምበርሌይን ጉዳይ እንድተከላከይ ጠበቃ እንደነተናገረው ሜሪል ስትናገር ዓይናችሁን ብትጨፍኑ ልክ ሊንዳ ስትናገር የምታዳምጡ ሆኖ ይሰማቸኋል፡፡ ብሏል፡፡

 

ሜሪል ያላት የሥራ ትኩረት በተጋፊዎች የአውስትራሊ ጋዜጠኞች ነጥብ አላሳጣትም፡፡ ከሪፖርተሮችና ከፎቶግራፍ እንሺዎች የሚብቋት ነጥብቅ አጃቢዎች አልተለይዋትም፡፡ በፊልም ቀረጻው ቦታ የነበረ የፎቶ አንሺዎች ጣልቃ ገብነት ነው ያስለቀሳትት፡ ለሜልቡርን የቀረበ ትልቅ ቤትም በመያዟ ቃለ ዘጋቢዎች ለሆሊውድ ልዕልት የሚበቃ ምሽግ ብላው ቀልደውባታል፡፡ በኋላ ላይ የከተማው ገበያ ቦታ አካባቢ ጊዜያዊ መኖሪያዋን ቀይረለች፡፡

 

ከጋዜጣ ሰዎች ጋር ያላት ችግርም ወደ አገሯ ከተመለሰችም በኋላ ቀጥሏል፡፡ በኒውዮርክ ቻትሃም ውስጥ ሜሪል ሄንሪና ሜሪ ዌላ ከሚባላት ልጆቿ ጋር ሆና ፎቶ ሊያነሳት ሲሞክር እንደመታቸውና ካሜራውን ልትበታትንበት እንደነበረ ነገር ግን በአቅራቢያው ሌላ ፎቶ አንቪ ስላየች እንደሳመችው በመናገር አንድ የፎቶ ግራፍ አንቪ ወንድሏቷል፡፡

 

ሜሪል አጋዜጦኛች በላይ የሥራ ባልደረቦቿ እጅግ በጣም የደንቋታል፡፡ ጃክ ጊኮልሰን አይረንዊድ እና ኽርትበርን በተባሉት ፊልሞች ላይ ከርሷ ጋር ከሰራ በኋላ ቸሎታዋን አድንቆላታል፡፡ ሲልክውድ በተሰኝው ፊልም ላይ አብሯት የሰራቸው ቪርም ቫርክ ገዳይ ማሽን የመሆኑን ያህል ሜሪልም የትወና መሽን ናት፡፡ የተፈጠረችው ለትወና ነው፡፡ ብላለች፡፡

የምትሰራባቸው ፊልሞች ላይ ሁሉ የምትወክለውን ባሕርይ የቻለችውን ያህል ታጠናዋለች፡፡ ግሬት ጋርቦን፣ ካተሪን ፔበርንን፣ ካሮል ሉምባርድን ስታደንቅ ማዶና በታዳጊዎች ላይ የምታሳድረው ተፅዕኖ ግን ጎጂ ነው ብላ ታስባለች፡፡

 

በአሁኑ ጊዜ የአራት ልጆች እናት ስትሆን ወደፊት ኮሜዲ ፊልሞችን ለመተወን ዕቅድ አላት ማይክ ሃመርም ሞክሪው ሜሪል እባክሽን ሞክሪው በማለት ጽሁፌን ደምድሟል፡፡

 

 

 

 

 

ስቲሽን ስፒልበርግ

የፊልም አዘጋጁን ስቲሽን በፒልበርግ ችሎታው በትክክለኛው መንገድ መመዘን አንችል ይሆን መደሰት እንደሚፈልግ አንድ ትልቅ ሕጻን ልጅ ፊል እየሰራም እንደማንኛውም የፊልም ተካታታይ የተለያዩ ስተቶች የተለያዩ ስሜቶች ይፈራረቁበታል፡፡ ያዘጋጃቸው ፊልሞ ብዙ ተቀባይነት አግኝተዋል፡፡ በሚሊዮን የሚቆሩ የሲኒማ ቤት ደንደኞች የሱን ፊልሞች በእርካታ ይመለከቷቸዋል፡፡

 

ወጣቶች ስቲሽን ስፒልበርግ የተባለውን የፊልም አዘጋጅ አላወቃችሁትም? ምድር ከምትባለው ፕሌት ውጪ /ኤክስትራ ቴሬስቲያል የሚለውን ከተካ/፣ ኢንዲያና ጆንስና የጠፋው ቅርስ ዘራፊዎች በመሳሰሉና ከ15 ዓመት ወዲህ ለአሜሪካ ሲኒማ ቁጥር አንድ የፊልም አዘጋጅ ነው፡፡

 

ወይን ጠጅ ቀለም የሚባለው ፊልም ለኦስካር ሽልማት ጥቆማ አግኝቶ ተሳትፏል፡፡ ስለዚህ ፊልምም ስቲሽን ሲናገር ከምድር ወጪ የሚለውን ፊልም ከሰራሁ በኋላ በቀጣዩ የዘር ልዩነትንና የኃይል አስገዳጅነትን በመቃወም ፊልሙን መስራቴ ምንም ጥርጥር የለውም ይላል፡፡

 

በሚሰራቸው ፊልሞች ላይ ሃያሲያን እንደ ተረባረቡበት ነው፡፡ አናም ይህን በማስመልከት ለማድፊቱ ሃያሲያንን ወዳጅ ለማድረግ ስላለው ስሜት ሲጠየቅም እንዲህ በማለት መልሷል፡፡

 

በሃያሲን ስለኔ የሚባለውን ነገር ብዙም ትኩረት ላለመስጠት የራሴ መርሆ አለኝ፡፡ ፈልሙን የማዘጋጅላቸው ተመልካቶች ያላቸውን አሰተያየት መስማት እመርጣለሁ፡፡ እስካሁን የሰራኋቸው ፊልሞች ሃያሲኑ ከዚህ በፊት የተመለከቷቸው፡፡ ዓይነት አይደሉም፡፡ በእርግ ተሳክቶልኛል፡፡ ነገር ግን ይህም ልክ እንደ ሳይንስ ሚስጥር ነው፡፡ ለማለት የፈለኩት ስኬት ብቃቴንና ሁኔታዎቹነም አላሟጠጥኩቸውም፡፡ አሁን ለምሳሌ የኢንዲያና ጆንስ ዓይነት ፊልም ካልሆነ በቀር ሌላ ዓይነት ፊልም አንድትሰራ አይፈቀድልም ብባል ወዲያውኑ የፊልም ሥራ ሙያዬን ወደ ሌላ አቀይረው ነበር፡፡ በሕይወት የምንኖው ወደፊት ለመጓዝ ብቻ እንጂ ባለንበት እንድንረግጥ አይደለም

 

ስቴሽን በ12 ዓመቱ ነበር አንድ ቀን አባቱ ባለ 8 ሚ.ሜ ካሜራ ይዞለት የመጣው፡፡ ፎቶ ማንሳትም ቆንጆ ነገር እንደሆነ ያኔውኑ አስበ፡፡ እንዳንድ ጉዞዎችን፡፡ የዕረፍት ጊዜዎችንና ትላልቅ በዓላትን በካሜራው መቅረጽ ጀመረ፡፡

 

ይህ የካሜራ ማንሳት ፍላጎት በዚህ ዕድሜው ይደርበት እንዲ የፊልም አዘጋጅ ለመሆን ምኞት ቆየት ብሎ በር የመጣለት፡፡ በሱ ዕድሜ ያሉት ትናንሽ ልጆች ማሸኒስት የመሆን ምኞት ነበራቸው፡፡ እሱም ልጅ ነበርና ይህንኑ ተመኝ፡፡ ካሜራዋ የበላጠ እየሳበቸው ስትመጣ ማሽኒስት መሆን ማሰቡን ተው፡፡ በፊልም ሌንስ ውስጥ የምትንፀባረቀው ዓለቻችን ልዩ ስሜት አሳደረችበት፡፡ እስካሁንም ያ ልዩ ስሜት አልቀነሰበትም፡፡

 

የፊልምን ጥበብ በመማር የሚኝውን እርካታ ፈጽሞ አላገኝውም፡፡ በዚያን ጊዜ አሁን እንዳሉት ዓይነት ት/ቤቶች አልነበሩምና እነዚያ ዓመታት ለስቲሽን በሕልም የበለፀጉ የምኞች ጊዜያት ነበሩ፡፡ ነገር ግን ጊዜያቱም ያልፈሉሉ፡

 

ስሚቀጥሉት ፊልሞች ምን እንደሚሆኑ ሰዎች ከምድር ውጪ የሚለው ፊልምን ተከታታይ እና ከ ኢንዲያና ጆንስ የሚቀጥለውን ለማየት ማጓጓታቸውን አንስቶ አንድ ጋዜጠኛ ለጠየቀው ጥያቄ ሲመልስ፡፡

 

ከምድር ውጪ ቀጣይ ከፍል ሲኖረው አይችልም እሱ ወደ ራሱ ፕላኔት ተመልሷል፡፡ ታሪኩም ሙሉ በሙሉ ተፈጽሟል፡፡ ይህንን ታሪክ እንደገና ልቀጥለው ማለት ንግድ ልነግድ የማለት ያህል ነው፡፡ ከምድር ውጪ የሚለው ፊልም በንፁህ የሰው ልጅ እቅድ ውስጥ ብዙ ነገር አምጥቶልኛል ሲል ገልጿል፡፡

 

ገንዘብ አያስደስትዎትም ማለት ነው? ተብሎ ለተጠየቀው ምንም ጊዜ ቢሆን ለንግድ ዓላማ ተነሳስቼ ፊልም የሰራሁበት ጊዜ የለም፡፡ ወደፊትም ቢሆን ለዚህ ብዬ አልሰራም፡፡ ለንግድ ሥራ ማንኛውም ሃሳብ ለኔ ቅዥት የመላበት አንቅልፍ ነው ላያምኑኝ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እውነቴን ነው፡፡ በማለት ተናግሯል፡፡

 

እንደስቲሽን አባባል ይችን ዓለም የሚመለከታት ተስፋ በሞላበት ዓይን ነው፡፡ በአሰቃቂ ፊልሞም ውስጥ ቢሆን ሰዎች የተስፋ ጭላንጭል ሊያዩ ይገባቸዋል ብሎ ያምናል፡፡ ሰለጠሩዎች የሰው ልጅ ባሕርያት መናገር ይፈልጋል፡፡ እንዲሁም ጥሩ ስለሆነው የሰው ልጅ መንፈስ፡፡ የጦርነትን ሰቆቃ የሚያስይ በሚሊዬን የሚቆጠሩ ተዋጊዜዎች ሲሞቱ ሌሎች ፊልሞች ላይ በሚታዩበት ዓይነት ሁነታ ሳይን በራሱ የፈጠራ ችሎታ ፊልም ሲሰራ ይፈልጋል፡፡ በነዚህ ጦርነቶች ውስጠ የታዩት የሰው ልጅ አሰቃቂ ሁኔታዎ አሁንም አሻራቻ አልደበዘዘም፡፡ የተሰሩት ወንጀሎችም አልተረሱም፡፡ የስቲሽን ፊልምም በነዚህም ጦርነቶች ውስጥ ስለወደቁት ታጋዬች ጎበዝናና ኃይል ማሳየት ይፈልጋል፡፡

 

ከ6 ዓመታት ወዲህ ለስቲሽን ብዙ ነገሮች ተለውጠዋል፡፡ ወንድ ልጅ ተወልዶለታል፡፡ እውነተኛ ቤተሰብ መስርቷል፡፡ እውነተኛ ቤተሰብ መስርቷል፡፡ ሆሊውድ በጣም የታወቀ ማህበረሰብ /የካምፕ ነዋሪዎች ዓይነት/ ስለሆነ ቤተሰብ ማፍራቱ ቆንጆ ሆኖለታል ሆሊውድ ውስጥ ለሚኖር ማንኛውም ሰው የሕይወት መሳካት ማንንም ይለውጣል፡፡ ራስን መጠበቅ አይቻልም፡፡ በባህላዊ ዓይነት ቤተሰብ መኖር ግን እውነተኛ ፍስሃን ያጎናጽፋል፡፡

 

በሥራውም በኩል ስፒልበርግ ሁሉም የሚያውቁት፣ ጥሩ ጥሩ ነገር የሚናገሩለት፣ ተስፋ ለጣሉበት በተቻለው ተስፋን ለመፈንጠቅ የሚጥር በመካከለኛ ዕድሜ የሚገኝ የተዋጣለት የፊልም አዘጋጅ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ያለመውን ሕልም በወጣትነት ዕውን ያደረገ የፊልም አዘጋጅ ስለሆነም ወጣቶች ብዙ ነሮችን ማበርከት እንደሚችሉ ጠቃሚ ምሳሌ ይሆናልና ብዬ አስቤያለሁ፡፡ እናንተስ?

 

ደምስ በቀለ

ከእርዳይታ

 

 

 

 

ትንሽ ስለሪቻርድ ቻምበርሌይን

ይህ አሜሪካዊ ተዋናይ ለፊልመ አፍቃሪያን አዲስ አይደለም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተመላካች በዓለማችን እሱ የሰራባቸውን ፊልሞች በመልክ መልካምነቱ ብቻ ሳይሆን በአሳማኝ ሁኔታ ራሱን ለውጦ በመጫወቱ ነው፡፡

 

በዶ/ር ኪልደር ጀምሮ በጁሊየስ ቄሳር ዘ ስራ ሙስኬተርስ የመሬት መንቀጥቀጥ ከተመስኑ ዓመታት ወዲህ ሪቻርድ ቻምበርሌይን የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልሞች ሽገን እና የእሾ ወፎችን ከስራ በኋላ ዝነኛነቱ /ኮከብነቱ/ ታዋቂ ሆነ፡፡ በኋላም ሻሰንበርግ የጀግና ተረት /በዚህ ፊልም ላይ ዋናውም ገፀ ባሕርዬ በሺ የሚቆጠሩትን ይሁዳውያን በጋዝ ከመታፈን ያድናቸዋል፡፡/ የንጉስ ሰለሞን ማዕድናት፣ ሕልም የሆነው ምዕራብ በተሰኝው አዲስ ፊልም ከ1830-1850 ባሉት ዓመታት ቻርሊስ ፍሬሞንት ወደ ሩቅ አገር በመሄድ ብዙ ችግሮችንና አደጋዎችን ማስወገዱን ያሳያል፡፡

 

ከሁሉም በፊተት ሪቻርድ ቻምበርሌይን እውነተኛ እሱነቱን ለማሳየት የሚልግ የሚሰማው ዓይነት ሰው ነው፡፡ ስለፊልም ሕይወት መጽሐፍ ለመጻፍ ያለበት ሁኔታ ባይፈቅድም አልፎ አልፎ ግን ሰዎ ወደ እኔ ኑ፣ ልቤ ለእናንተ ክፍት ነው፡፡ እኔ እንደማንኛውም ዓይት ተራ ሰው ነኝ እንጂ የማይደረስበት ዓይነት ኮከብ አይደለሁም በማለት ጮክ ብሎ እንዲናገር ስሜቱ ይገፋዋል፡፡ ከልጅነት ጊዜዬ አንስቶ ለረዥም ዓመታት ከኅፍረት ጋር ነው የኖርኩት ወላጆች ከሠራተኛው ወገን ናቸው፡፡ አባቴን የቀረፀው የንግዱ አካባቢ ስለነበር ሁልጊዜ ለቻበርሌይን ሰዎች ምንጊዜም ቢሆን ከእጃችን ሉያጡ አይገባም፡፡ ይለው ነበር፡፡ በቤት ውስጥ ጥብቅ የሆነ ስነስርዓት ይፈልግ ነበር፡፡ አሁን ግን የሕይወት ጎዳና አራርቋቸው ለረዥም ጊዜያት አባት የልጁን ድምጽ ሰምቶ የሚያውቅም አይመስለውም ቻምበርሌይን፡፡

 

ከዚያም በኋላ የት/ቤት ጊዜ ደረሰ፡፡ እዛም እንደዚሁ ነው፡፡ ከማፈሩ የተነሳ አብረው ከሚማሩት ልጆች አንዱንም እንኳን አነጋግሮ አያውቅም፡፡ ጥቁር ሰሌዳው አካባቢ ድምጽ የተሰማነት ጊዜ ትዝም አይለው፡፡ ሁሉም ልጅ ከጓደኛው ጋር ይቀመጣል፡፡ እሱ ግን ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ ብቻውን ነበር፡፡ ብቸኝነት ልክ ጓከኛው እንደሆነ ዓይነት፡፡ ከእርግጥ ይህ ሁኔታ አላስደሰተውም፡፡ በጣም ተጨንቆ ይሆን ሁኔታ እንዳይቀጥል ተጣጣሪ ገን አልተሳካለትም፡፡

 

ዛሬስ ለውጥ አለ? ከትወና ሙድ ጋር ሙያዬና ዕድሌ ነው በማለት ተያይዞታል፡፡ ለውጥ ከሙያው ጋር በተያያዘ ሁኔታ እንጂ ከሱነቱ ከውስጣዊ ስሜቱ አይደለም፡፡ ሽልማት ለመቀበል ወደ ሆነ ቦታ መሄድ ቢኖርበት በሰዎ ፊት የመታየት ዕፍረት ስለሚሰማው ሀሞቱ ፍስስ ይላል፡፡ ጩህ ጩህ ይላለዋል፡፡

 

ሪቻርድ ቻምበርሌይን በሙያው ትልቅ ደረጃ የነካው በእንግሊዞች መድረክ ላይ ሐምሌትን ሆኖ ሲተውን ነበር፡፡ ከሱ በፊት ማንኛውም አሜሪካዊ ይህን ገፀ ባሕርይ በእንግሊዝ መድረክ ላይ አልሞክረውም፡፡

የተውኔቱ አዘጋጅ ስለኔ ምን እንደተሰማውም ባለውቅ ስለምርጫ ከተነሳ ግን በስሜትና በመንፈስ ከተሞሉ ማለትም ለኔ ከሚቀርቡ ሰዎች ጋር ብጫወት አመርጣለሁ ብሏል፡፡ ቻምበርሌይን ከምን ዓይነት ተዋናዮች ጋር መጫወት እንደሚፈልግ ሲገልጽ፣

 

የእሾ ወፎች መደነቅን ካተረፈለት በኋላ ሆሊውድ ፊቱን ወደ ቻምበርሌይን የመለሰ ይመስላል፡፡ ተዋናዬም የልቡ ሳይሞላ አልቀረም፡፡ ባለፉት 10 ዓታት ቻምበርሌይን ለሁሉም ሰው መልከ መልካምና ጥሩ ቁመና ያለው ወጣት ብቻ ሳይሆን ተዋናይም እንደሆነ ለማሳየት ለራሱ ቃል ገባ፡፡ ማንም ሰው ቢሆን በመልክ መልካምነቱ ብቻ እንዲነቅ አይፈልግም ምክንያቱም ያ መልከ መለካምነት የመቆው እስከ ተወሰነ የዕድሜ ክልል ነውና፡፡ ይህ ችግር የቻምበርሌን ብቻ ሳይሆን የተዋናዮች ሁሉ ነው፡፡ ተዋናይ ችሎታው የተለየ መሆኑን በተግባር ማስመስከር አለበት፡፡ ብዙውን ጊዜ እውነተኛውን ሪቻርድ ቻምበርሌይንን ማንም አያውቀውም እያለ ያስባል፡፡

 

መደነቅ ያመጣለት የእሾ ወፎች ቻምበርሌይን አንዴ ሊሰራው እንደቻለ ለማወቅ ሳንጓጓ አንቀርም፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ለመጀመሪ ጊዜ መጽሑፍ ለሕትመት ሲበታ አነበበው፡፡ መጽሐፉ ከመጀመሪያ ገጾች ትኩረቱን ሳበው፡፡ በራልፍ ደብሪካሳር ባሕርይ ውስጥ ለሱ የሚቀርብ ንፁህና ልስላሴና ጥንካሬ ተጣምረው ቀርበዋል፡፡ የመጽሐፉን ባለመብትነት ገዝቶ ወደ ፊልምነት ለመቀየር ፈለገ፡፡ አቅራቢዎቹ ሌሎች ዕቅዶች ስነበራቸው አልተስማሙም፡፡ በዋናው ገፅ ባሕርይ ቦታ ሮበርት ሬድፎርድን አስቀምጠው ፊልም የማስራት ዕቅዱ ነበራቸው፡፡ በኋላ ላይ ነገሮች ተለውጠው ወደ ቻምበርሌይን ፊታቸውን መልሱ፡፡ እሱም የሚፈልገው ነበርና በደስታ ተቀበላቸው፡፡

 

የፊልም ተመልካቶች ስለሞን እንደሚያወራ ሲለምዱት እዚህ ላይ ታሪኩን መዘርዘሩ አስፈላጊ አይንም፡፡ ፊልሙ በእያንዳንዱ ሰው ነፍስ ውስጥ ስለመኖረው ፍቅር ደስታና ተስፋ ከሚያወራው የበለጠ ስለ ሃይማኖት ሰው ራልፍ ደብሪካሳር፣ ስበቴክርስቲያን አያወራም፡፡ ራፍል ሜጌን በመውለዱ እንዷንና እውነተኛዋን ዘፍን ዘፈን፡፡ በሙያው ወደፊት ገሰገስ፡፡ በዕልቅና ደረጃ ዕድገትም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍ ያለ ወጣ ነገር ገን ከሜጊ ጋር ያለው ፍቅር በአውስተራሊ አፈ ታሪክ በወፏ ልብ ውስጥ እንደሚሰነቀረው እሾ ዓይነት ነው፡፡

 

ቻምበርሌይን በኑሮው የሜይወደው ቃል አለ፡፡ ኮከብ የሚለው ነው፣ ሰዎችን እወዳለሁ፡፡ ስለዚህም በሚጠኝ የባሕርይ ድርሻ አማካኝነት ስ ሰዎችና ሰለሰዎች ስቀረቡ ነገሮች ልነግራቸው አፈልጋለሁ፡፡ ያንተ ኮከብ መሆን ማለት ከሰዎና ከነገሮ ሁሉ በጣም ርቀህ የምተገኝ ሊደረስብህ የማይችል ማለት ነው ይላል ስለሁኔታው ሲጠየቅ በሚመልሰው መልስ፡፡

 

ወጣት ተዋናዮች ሆሊውድ ውስጥ ይመጣሉ፡፡ ሁሉንም ነገር ማወቅ አለባቸው፡፡ በሥራ ለማደግ ብዙ መስራት አለባቸው፡፡ ኮከብ የሚለው ቅጥያ በቀላሉ ሊለጠፍብሕ ይችላል፡፡ በዚህም ጊዜ ሁሉንም ነገር እንደደረስክበት መስሎ ሲሰማህ የሚለው ቅጥያ በቀላሉ ሊለጠፍብሕ ይችላል፡፡ በዚህም ጊዜ ሁሉንም ነገር እንደደረስክበት መስ ሲሰማህ ይችላል፡፡ ስለዚህም ጥረትህ ይገታል፡፡ እናም ደፈቀህ ማለት ነው፡፡ እነሱሁና ደፈቁህ መጀመሪያሙው ውስጥ ሲገባ ለሱ ይህ ሁኔታ ግልጽ ነበር፡፡ ሁሉንም ዓይነት ሥራ መስራት ይፈልግ ነበር፡፡ በፊልም፣ በቴሊቪዥን፣ በሙዚቃዊ ኮሜዲ፣ በጥንታዊ /ክላሲክ/ እና በአሁን ጊዜ ያበት ቦታ ለመድረስ በጣም ብዙ ሰርቷል፡፡

 

ታዋቂነት በጣም ቆንጆ ነበር ነው፡፡ ተዋናይን ግን ይህ ሁኔታ እያሰፈነ ድቀውም፡፡ ከሁሉም በፊት ተዋናይ አንድ ሰው በመሆኑ 24 ሰዓት በሙሉ በካሜራ ተከቦ ሊኖ አይችልም፡፡ ቻምበርሌይን ለምሳሌ ብዙ ከሰራ በኋላ የራሱ የሆነ ጊዜ ይፈልጋል፡፡ በጣም መታወቅ ግን እንዲህ ዓይነቷን የዕረፍት ጊዜ ያሳጣል፡፡ በዚህ ዓይነት ጊዜ አድናቂዎች ሲከቡትና በጥያቄ ሲያዋክቡም፡፡ የሰውን ልጅ እወዳለሁ፡፡ ተመልካችን እወዳለሁ፡፡ ነገር ግን ልክ ፍቅር ላይ ያሉ ሁለት ሰዎች ሁሉንም ነገር እስከመጨረሻው መነጋገር እንደሌለባቸው ሳይነገር የሚታወቅ መኖር እንዳለበት ሁሉ በኔም በኩል እንዲሁ ነው፡፡ ይላቸዋል፡፡

 

ዝነኛ መሆን ቀላል ነገር ነው፡፡ ምን ይህል ጥረት እንደሚያስፈልገው ዝነኛው ሰው ታውቀዋል፡፡ ቻምበርሌይን በሙያው ተዋናይ ቢሆንም በእውነተኛው ሕይወቁም መተወን እንደሌለበት ያወቃል፡፡ ዝነኝነት ግን ይህንኑ ይፈልጋል፡፡ እራስህን እንዳት4ሆን ያደርጋል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ለራስህም ሆነ ለአድናቂዎህ ሐቀኝነት አይደለም፡፡

 

ቻምበርሌይን የራሱን ባሕርይ መናገር ቢችል ሪቻርድ ቻበርሌይን በስሜት የተሞላ ነገር ግን ደካማ ያልሆነ ሰው ነው ይል ነበር፡፡ ማንም ሰው ቢሆን በሆነ ምክንያት ዕንባውን ያፈሳል፡፡ ወንድም ቢሆን በ51 ዓመት ዕድሜ ላይ ቢገኝም፡፡

 

በዚህ ጽሁፍ የተካተቱት ሀሳቦች በሙሉ የቻምበርሌይን መሆናቸውን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ደግሞ በሌላ ጊዜ ሌላ ይዤ እስከምቀርብ የደህና እንሰንብት፡፡

 

ደምስ በቀለ

ከእርዳይታ

 

 

 

 

 

 

 

 

የአረቢን ሎውረንስ ፒተር ኦ ቶል

እኔና ሕይወቴ

ከሰላሳ ዓመታት በፊት የአይሪሽ ዘር ትውልድ ሃረግ ያለው፣ ንቁ ሰማያዊ አይኖች፣ ጥሬ ቁመና ይዞ በዲቪድ ሊን የተዘጋጀው ታሪካዊ ፊልም በረሃን እያቆራረጠ ተውኗል፡፡ ልዩ በሆነው አተዋወኑም በዘመናቸው ትል የሚባለውን በፊልም ሙያ ድንቅ ሁኔታን ላስመስከሩ ሰዎች የሚሰጣቸውን ኦስካር ሽልማት አግኝቷል፡፡

 

ከዚያም ጊዜ ጀምሮ የፒተር ኦ ቶል ሙያ በችግርና ሞገድ በበዛት ሀኔታ ከጥንካሬ ጥንካሬን እየተላበሰ ወደ ዓለም አቀፋዊ ገናናነት አምረቶታል፡፡ ልዩ የሆነው የተዋናይነት ስጦው ሲኒማን ከቴያትርና ከቴሌቪዥን እንዲለይ አስችሎል፡፡ የአመራረጥ ጣዕም ስብዕናውም በተለያዩ መሪ ባሕሪያት /ሎርድጂም/፣ /ማክቤዝ/፣ /የቫውሰውና ከሰው ተፈጥሮ በላይ ችሎታ ያለው ሰው/፣ /ፒግማሊየን/፣ /የጄኔራሎች ምሽት/፣ /ደህና ደዋሎ አቶ ቺፕስ/፣ /ዶ/ር ፈጣሪ/ እና በቅርቡም በቤርቶሎቼ /የመጨረሻው ንጉስ/ ተጫውቷል፡፡ የመጨረሻው ንጉ የተባለው ፊልም ባለፈው አራት ዓመትም የኦስካር ሽልማቶችን አስገኝቷል፡፡

 

ኦ ቶል ከቻይና ሲመለስ በኔይል ጆርዳን የተዘጋጀው ድንቅ አስቂኝ ፊልም /ከፍተኛ መንፈሶች/ ከዳሪል ሃናህ ጋር ተቻውቷል፡፡ ታሪኩ በአየርላንድ ውስጥ አንድ የፈሬረሰገዳም ባሌት የአሜሪካን ቱሪስቶችን ለማስተናገድ እንዲችል ገዳሙን ወደ ሆስፒልነት ለመቀየር ሲሞክር በተወሳሰበ ሁኔታ ከሙታን መንፈስ ታሪክ ጋር ሲላለፍ የሚያሳይ ነው፡፡

 

ሁልጊዜም ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ ክስተቶ ይሰቡኛል፡፡ በአያቶቻችንና በቅድም አያቶችን መንፈስ የተሞላ ከሕይወት በኋላ ሕይወት ይኖር ይሆን? ብዬ እደነቃለሁ፡፡ ይህም በየቀኑ የሚሰማኝን ውጤት አልባነት ስሜት ያስወግድልኛል፡፡ በተለይ ከዳሪል ሃናህ የስራ ባልደረባዬ ጋር እና የቅድመ አያቶቼን መኖሪያ እየርላንድ ውስጥ መስራቴ ያስደስተኛል፡፡ በኮኔማራ ጫካ ውስጥ በሰፈራሁበት የገጠር ሺላ ውስጥ አብዛኛውን ትርፍ ጊዜዬን አሳልፋለሁ፡፡ በዚህ የአለማችን ክፍል ላለው የጠፈጥሮ ውበት ምስጋና ይድረሰውና በማንኛውም ጊዜ ውስጣዊ ሰላም አገኝለሁ፡፡ በማለት በዚህ ፊልም ላይ በመሳተፍ የተሰማወን ስሜት ገልጿታል፡፡

 

ያለፈው አሁንም ገና አላለፈም፡፡ ያሁኑም እርገጠኝነት የለውም የወደፊቱ አይኖርም፡፡ ካለፉት ዓመታት የተማረው እያንዳንዷን በራሪ ደቂቃ የማትደገምና ሕይወትን ምታጎናጽፈን ስለሆነ ሳትባክን በትክክል ልንጠቀምባት ይገባል፡፡ በትዝታዎችና ቀስተ ደማናዎችን በመከተል ጊዜ ማጥፋት የለብንም፡፡ በዚህ ሁኔታ ሳንጠብቀው የሚጋረጥብንን መስናክል የምንጋፈጠውም በዚህ ሀኔታ ነው በማለት ያስባል፡፡

 

ባለፉት አስር አመታት ለሱ በዓለም ውስጥ ውድ የሀኑትን ሰዎች አጥቷል፡፡ እናቱን፣ አባቱን ሚስቱንና ተወዳጅ ውሻውን፡፡ በውጤቱም በበለጠ ለአደጋ ተገጋልጧል፡፡

 

ጆን ሄዬስተን እና ፔተር ዬትስን ለመሳሰሉ አብሯቸው ለሥራ ለተሰለፉአቸው የፊልም አዘጋጆች አድናቆት ቢኖረውም እንደ ዴቪድ ሌን የሚወደውና የሚደንቀው አዘጋጅ የለም፡፡ ለደረሰበት ስነጥባባዊ ውጤት ዴቪድ ሌን ባለውለታውና ጥሩ ጓደኛውና መካሪው እንደሆነ ይናገራል፡፡

 

በርናርዶ ቤርቶሎቼ ስለተባለው ጣልያናዊ የፊልም አዘጋጅም በርናርዶ እጅግ ልዩ የሆነ ሰው ነው፣ የማይደክም ሰራተኛ፣ እጅግ ትልቅ ተሰጥኦ ያለው የፊልም አዘጋጅ ራሱን በጣም የሚቆጣጠር እናም ሌሎችንም ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የሚችል ነው፡፡ በመቶ የሚቆጠሩ ቻይናውያን ተዋናይና የህዝብ መዓት ያለበትን ክፍል ሲያሰራ ትናንሿን ዝርዝር ሳይቀር ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑ በጣም የሚደነቅ ነው፡፡ ያም ፊልም እነኛን ሁሉ ኦስካሮች ማግኝቱ አስፈንድቆኛል፡፡ እጅግ ግሩም ለሆነው ስነጥበባዊ ችሎታቸውም ጥሩ እውቅና ነው ሲል አድናቆቱን ገልጾታል፡፡

 

ፊልም ሙያውማ ቢሆን በጣም ከሚወዳቸው ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ከፊልም ደግሞ አብልጦ ቴያትርን ያፈቅራል፡፡ ከሥራ ውጪ የሚያዝናኑት ነገሮች የክሪኬት ጨዋታ፣ የፈረስ ግልቢያና አትክልት /አበባዎችን/ መትከል ነው፡፡ ውሰኪውን እየተጎነጨም ግምት የሚሰጣቸውን እንደ ሼክስፒር፣ ሾው፣ ቢሮን፣ ዋይልድ፣ ቤኬት የጻፈዋቸውን መጻሕፍት ማንበብ ያዘናናዋል፡፡ ብዙዎ ከሚያስቡት በታቃራኒ ፒተር መጠጣቱን አቁሟል፡፡ ሲጋራ ማቆም ግን አልቻለም፡፡ ሻይ ፉት እያለ ሲጋር በላይ በላዩ ያቦናል፡፡ ስላለፈው ሞገድ ስለበዛበት ሕግን ብዙም ያልተከተለው ሕይወቱ አይቀጭም፡፡

 

ጥሬ ባሕርይ ያሰለቻል፡፡ ከዚህ ይልቅ ከስርዓት መውጣት ይሰበኛል፡፡ ስሜቶን እስከመጨረሻው ማስኬድ ያረካኛል፡፡ በሕይወት ውስጥ ያለ ሁሉንም ነገር ሞክሬለሁ፡፡ በእርግ መክፈል ያለብኝ ዋጋም ከፍያለሁ፡፡ ልኖረው የሚገባኝን ሕይወት ኖሬያለሁ፡፡ ይላል ስሕይወቱ ጨለፍ አድርጎ፡፡

 

አንድ ትልቅ መሳካት ያለበት ጉጉ አለው፡፡ ያ ጉጉትም በሼክስፒር ንጉስ ሊር በተባለው ድረሰት ውስጥ ንጉስሰ ሊርን ሆኖ መጫወት፣ ጊዜው ይቅረብም ወይም ይራቅም መጫወቱ ግን አይቀርም፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የኤልሳቤጥ ቴይለር የውድቀት ዓመት

የዘነኛዋ ተዋናይ ኤልሳቤጥ ቴይለር የውድቀት ዓመት መስከረም 1960 ዓ.ም ጀምሮ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ደብዝዟል፡፡ ይህ ዓመት በእሷ ትወና የተጀመረው ፊልም ሥራ ፈቅ ሳይል የብዙ ኢንሹራንስ ካምባኒዎን ኢኮኖሚና 5 ሚሊዮን ዶላር አደጋ ላይ የጣለ ነበር፡፡ ለኤልሳቤጥ ቴይለር ደግሞ ምን ያህል እንደጎዳት በወቅቱ ማንም አላወቀውም፡፡ ወደ ሞት የጠቃረበችበት፣ በውስጧ የእርዳታ ፍለጋ ድምጾች የሚሰሟት፣ ያልታወቁ እጆች እሷን ከነበረችበት አደገኛ ሁኔታ ለማወጣት የሚታገሉበት ጊዜ ነበር፡፡ ጦርነትን ረሃብንና ክሩስቼፍን ከጎኑ ይዞ መጓዝ የለመደው አለማችን በኤልሳቤጥ ቴይለር የሳንባ በሽታ ለመከፍ ብዙም የተደነቀ አልመሰለም፡፡

 

ከበሽታዋ አገግማም /ቁጥር ስምንቶ የቢራቢሮ ሜዳ/ የሚለው ፊልም የሆሊውድን በጣም ትልቅ የኦስካር ሽልማት ለመቀበል ስትመጣም ከግምት በላይ በሆነ የደስታ ስሜት ነበር፡፡

 

ትዊንቲ ሴንቸሪ ፎክስ ስላዘጋጀው ክሌፓትራ የተሰኝው ታሪካዊ ፊልመ ምንን ፊልም እንድሰራላቸው በጠመንጃ አስገድደውኛል ብላ ተናግራለች በሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ ለተሰበሰቡት ተመልካቶች፡፡

 

የክሌዎፓትራን ድርሻ ለማግኝት በጣም ብዙ ሴት ተዋንያን የአልዝና ዕንቁ ጉ ጭምር የማይፈነቅሉት ድንጋይ ባይኖረም የስቱዲዮው አለቆች ዓመቱን ሙሉ ያ ድርሻ ከኤልሳቤጥ ቴይለር በቀር ማንም እንማያስገኝወ በአቋማቸው ጸንተዋል፡፡ የመሪ ወንዶች ተዋንያን ፒተር ፊንችና ስቴፊን ቦይድ በሪቻርድ በርተንና በትሬሸር ሆዋርድ ተተክተዋል፡፡ ጥንታዊቷ አሌክሳንደሪያ ከዳመናዋ ለንደን ወደ አንዚዬ የባሕር ዳርቻ ስትሸጋገር ሊዝ ቴይለርም ከጠቅላላው ገቢ የ10 ገርሰንት ቀረጥ ከትርፍ 50 ገር ሰንትና የአንድ ሚሊዮን ዶላር በተጨማሪ የትርፍ ሰዓት ሥር በሳምንት 55 ሺ ዶላር ውል ተፈራርማለች፡፡ ከአራፈት ወራት በላይ ውጪ ሀገር ስትቆይም የመርቀበና የአይሮፕላን ጉዞ በግምት ውስጥ አልገባም፡፡

 

ሳም ስፒል ለንድን ውስጥ የበሽተኛ አልጋ ላይ ሲጠይቃት በተቻላት ጤንነቷን ከመለሰች ከባሏ ኤዲ ጋር ሁለተኛ ጫጉላ በሱ የሽርስር ጀልባ ላይ እንደሚያስልፉ ቃል የገባላትን በማስታወስ ነሐሴ ውስጥ ወደለላት መስከረም ላይ የክሌዎፓትራን ፊልም ሥራ ከመጀመሯ በፊት ኔፕልስ ውስጥ ሳም ቃል የገባላትን የጀልባ ሽርሽር ተጠቅማበታለች፡፡

 

ወደ ሞት የተቃረበችበት አሰቃቂው ሁኔታ ካለፈ ገና 6 ወሩ ነው፡፡ ለመርሳት አደገኛ የሆነ ማስታወሱ ደግሞ አላዋዊ የሚሰኝ ትዝታ ሊዝ ቴይለር በገዘፈው ጥረቷና ዝምታዋ በሆሊውድ ውስጥ በአዲስ ሁኔታ ስላገኝቸው ተቀባይነት፣ የተሰጥኦዋን እውቅናና የኃላፊነት ጭማሪ ብቻ ማሰታወስ ከመረጠች አጠገቧ ያሉት ሰዎች ወደዱም ጠሉ ሊጠብቁ የሚገባቸው ነገር እመዚህኑ ድንቅ ነገሮች መሆን አለበት፡፡

 

የሊዝን የበሽታ ታሪክ አንድ ስሙን ሊገልጽ ያልፈለገ መጽሔት ኢንፍሎኤንዛ፣ የሻይረስ በሽታዎ፣ የተሰበረ ግን እግር፣ የአይን ሕመም ቦታውን የሳተ አጥንት፣ የአከራካሪ አደገኛ ሕክምና /5 ሰዓት የፈጀ ቀዶ ጥገና/ የተሰነጠረ ቅልቅም፣ ብሮንካይትስ፣ ሜኒንጃይትስ እና ሁለት ጊዜ የተከሰተ የሳንባ በሽታ በማለት አትቶታል፡፡

 

ሲልቨር ማስክ የተባለው የጣሊን ኦስካረን ለመቀበል ስትመጣም ወደ 2,000 የሚጠጉ ጣሊናዊ አድናቂዎቿ ሉናጠቋት እንዳሰፈሰሩ ባለቤቷ ኤዲ አጠገባቸው የነበርው መኪና ውስጥ አስገብቷት ድናለች፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ስለሮማ የባሮች አመጽ የማያሳየው /ስፖርታክስ/ የተባለው ፊልም የመጀመሪያ ትዕይንቱን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀችው የልደት ቀን ግብዣ ላይ ዋናውን ገፀ ባሕርይ ሆኖ የሠራው ኪርክ ዳግላስ ትልቁን ኬክ እንድትቆርስ ረድቷታል፡፡ የፊልም አዘጋጁ ጆሴፍ ማንኪዊዝ የዳስ መድረኩ በላ ሲያሸከረክራትም በሕልም ዓም ያለች ነጭ ላባ የመሰለ የምሽት ጋወን የለበሰች ሰጎን ትመስል ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ብዙ ሳትቆ ከክብሪት ቀፎ ውሰጥ በወደቀ እሳት ልብሷ በእሳት ተያይዞ ሲጨስ አንድ የቫዬሊን ተጫዋች በቅጽበጽ በእጅ እሳቱን በማጥፋት ሲደናት አመሰግናው ሊዝ ሳትረበሽ የሩምባ ጨዋታዋን ቀጥላለች፡፡

 

ወደ ሮም ሲሄድ የራሳቸው አይሮፕላን ቢሆን ኖሮ ወጪው ይቀንስ እንደነበር የዚያን ጊዜ ባሏ ኤዲ ይናገራል፡፡ ሻንጣዎቹን መቁጠር ያስቸግራል ግን አራት የዩርክሽየር ፈጣሪ ውሾች፣ በነሐሴ ውስጥ የባሏን ልደት ምክንያት በማድረግ በታዋቂው ቢክስሀኛ ስም የሰየመችውን ሮኪ ማርሲያኖ የሚባለውን ቡችላ፣ ሁለት ከታይላንድ የመጡ ድቶች እና ዝንጀዎች በጉዞው ላይ ተጨምረዋል፡፡ ከዚህ ሌላ የሊዝ ሶስት ልጆች /እንደኛዋን ኤዲ በማደጎ የሚያሳድጋት ነች/ አንድ ነርስ፣ አንድ ሪፖርተር እንመለከተው 27 ክፍሎች ያሉትና 22 ሰዎች በምግብ ጠረጴዛ የሚሰበሰቡት ማረፊያ እንዲያዙ የሚገልጽ ሲሆን ሎዌላ ፖርሰን ደግሞ እንደዘገበችው 14 ክፍሎች፣ አንድ የመዋኛ ገንዳ፣ የቴሊስ ሜዳና አንድ ሮልስ ሮይስ መኪና ከደጃፍ የቆመ ቪላ እንደሆነ አስነብባለች፡፡ የፈረንሳይ አምባሳደር ጌታውን የከዳና ሌዝ ቴይለርን እንግሊዝኛ ጣሊያንኛና ግሪካዊን የማያቀላጥፍ የቤት ጠባቂ እንድታፈላልግ ያስገደዳት አንድ ግሪካዊ የምግብ /የወጥ/ ቤት ኃላፊም አብሮ ይገኛል፡፡

 

በዚህ ሁኔታ ነበር ድንቅ የታሪክ ፊልም የሆነውን ክሌዎፓትራን ለመስራት የተዘጋጅን፣ ያ ዓመት በእርግጥም የርሷ ነበር፡፡ በማንኛውም ሰው ሁኔታ ፈጽሞ ሊሆን የማይችል፣ ነገር ግን እሷ ትቋቋመው ይሆን? እንደሌዝ እወሳሰድ ያለጥርጥር፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ጄኒፈር ቢልስ

ወድ የቅዳሜ ወጣቶች ፕሮግራም አዘገጆች ሰላም ለናንተ ይሁን እላለሁ፡፡ የእስከዛሬ ፕሮግራማችን በማዳመጥ ብቋደስውም ተሳትፎ አላደርኩም፡፡ እስኪ በስነ-ጥበቡ ዓለም የፊልም ዘርፍ ውስጥ ከተዋናዮችም ሆነ ታዋቂ ድርሻ ካላቸው ሰዎች ከሰበሰብኳቸው ጽሁፎች ውስጥ በተለያየ ጊዜ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡ ለይህ እንግዲህ ተግባራው ሀነው ቤት ለእንግዳ ካላችሁኝ ነው፡፡ ለዛሬ የፍላሽ ዳንስ ፊልም ዋና ባሕርይ ሆና ስለተጫወተችው ጄኔራል ቢልስ በጥቂቱ ይኽውላችሁ፡፡

 

የአሜሪካን ስነ-ጽሁፍ በ30ዎቹ ጊዜ የነበሩትን ይስላሺ ፕላትንና የፍራነ4ሲስ ስት ፊትዝጌራልድ የፍቅር ታሪክ ልብወለዶችን ትወዳለች፡፡ ከእንቅልፏ እንደነቃች የስፕሪንግስቲንን ካሴት እያጠናች ከሆነ ደግም የሺሻልዲን ካሴት ትመርጣለች፡፡ ልክ 21 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ካርዶችን ያህል እሷም በዚህ ዕድሜዋ በጣም የዋህና ጥሩ ናት፡፡

 

በፍላሽ ዳንስ ላይ ስትተውን ያየናት ጄኒፈር ቢልስ /አሁን ከቦሪስ ካርሎስ ጋር/ በ1935 ዓ.ም የተጻፈውን የፍራንሰኮንሽታይን እጮ በሚለው ፊልም ላይ ተጫውታለች፡፡ በፊልሙ ውስጥ ከሷ ሌላ ፖሊ በሚባለው የሚዚቃ ባንድ ተጫዋች ወጣቱ ስቲንግም ተሳትፏል፡፡

 

ጥያቄ፡- ፍላሽ ዳንስ የተባለው ፊልም የተዋጣለት ነው፡፡ ነገር ገን ስጄኒፈር ቢልስ በጣም ጥቂት ወይንም ምንም አይታወቅም፡፡

ጄኒፈር፡- ግሪጎሪና ቦቢ የሚባሉ ወንድሞች አሉኝ፡፡ ተማሪዎች ናቸው፡፡ እናቴ አስተማሪ ናት ነገር ገን አንድ ኦርኬስትራ ውስጥ ኮንትራ ባዝ /በገና/ ትጫወታለች፡፡ አባቴ የምግብ ሸቀጣሽቀጥ ሱቅ ነበረው፡፡ የእንጀራ አባቴ ደግሞ ሃኪም ነው፡፡ ገና ልጅ ሳለሁ ጨዋታ እወድ ነበር፡፡ ለዚህም የሚከፍለኝ ሰው አግኛለሁ ሚል ሃሳብ አልነበረኝም፡፡ በዬል ዩኒቨርስቲ ውስጠ መማር እንድችል ለማስታወቂያ የፎቶ ሞዴል በመሆን ሥራ ጀመርኩ፡፡ እናም አንድ ቀን የስራ ኃላፊዬ ስልክ ደወለችልኝ፡፡ ለፍላሽ ዳንስ ፊልም የሙከራ ጥያቄ ነበርር፡

ጥያቄ፡- አስቸጋሪ ባሕርይ አለሽ የሚባለው እውነት ነው?

ጂኒፈር፡- አይደለም፡፡ ነገር ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች ይወሰናል፡፡ በተቃዋሚነት ከቀረቡ አናደዳለሁ፡፡ ከፊልም ዳይሬክተሩ ጋር ከሆነ ብናደድም ጮኬ አላማርርም፡፡

ጥያቄ፡- ፍላሽ ዳንስ ላይ ባትሳተፊ ኖሮ ፊልሙን ለመመልከት ትሄጂ ነበር?

ጄኒፈር፡- በዬል ዩኒቨርስቲ ተማሪነቴና የአሜሪካን ስነጽሑፍና ተከታይ በመሆኔ ሰዎች ገንዘባቸውን ለምን እንደሚያወጡ ማየት ያስደስተኛል፡፡

ጥያቄ፡- የፍራንክንሽታይን እጮ በሚለው ፊልምና በፍላሽ ዳንሽ መካከል የ3 ዓት ልዩነት አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ ምን እየሰራሽ ነበር?

ጄኒፈር፡- የትምሀርቴን በሙሉ ልቤ እመር ነበር፡፡ ከዚህ ሌለ በአንድ የቴሌቪዥን ተከታታይ ፊልም ተሳትፌያለሁ፡፡ በዚህ ተከታታይ ፊልም ጄሲካላንዥን የመሳሰሉ ዕውቅ ተዋንያን ተካፍለውበታል፡፡

ጥያቄ፡- ለዚህ አለም የፍቅር ልብወለድ ይስብሻል?

ጄኒፈር፡- ለፊልም የሚዘጋጁትን ጽሁፎች እኔ ብጽፋቸው የሴቶችን ገፀ-ባሕርይ ፈጽሞ ባል እንዲያገቡ አላደርጋቸውም ነበር፡፡

ጥያቄ፡- በአሜሪካ ውስጥ ፍላሽ ዳንስ የሚባለው ፊልም ተቀባይነት ብዙም አላገኝም፡፡ የሁለት ሰው ገላ ያላት እመቤት ይሉኛል፡፡ ስለዚህ ሁኔታ ምን አስተያየት አለሽ?

ጂኒፈር፡- ምንም ዓይነት ቅጽል ቢሰጠኝ ግድ የለኝም፡፡ በፈረንሳይና በጣሊን ፊልሙ በአርኪ ሁኔታ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ በፍላሽ ዳንስ ላይ ከኔ ጋር የኔውን ባሕርይ ይዛ የምትሰራ ፕሮፌሽናል ዳንሰኛ አለች፡፡ ሌላም አንዲት ልጅ ነበረች፡፡ ልክ የፍራንከንሽታይን እጮኛ በሚለው ፊልም ላይ ራቁቷን የምትታይበት እንዳለችው ልጅ የኔ ፍላጎት ያለ ልብስ መጫወት አይደለም፡፡

ጥያቄ፡- በፍላሽ ዳንስ ፊልም ተደስተሸል?

ጄኒፈር፡- አንድ ጊዜ ብቻ አይቼዋለሁ፡፡ እንደጋ ላየው ይጋባኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ፊልሙ ከጽሑፈ በዛ ያለ ልዩነት አለው፡፡ ሁል ጊዜም እንደዚህ እንደሆነ ከባለሙያዎች ይሰማራል፡፡

 

የፊልም ዜናዎች ከሚል መጽሔት

ከውጪ አገር ህትመት

 

 

ፍላሽ ዳንስ

በዚህ ፊልም ታሪክ ውስጥ በጣም አስደናቂው ነገር በታየበት አካባቢ ሁሌ ዝናን ማትረፉ ነው፡፡ በምዕራብ አውሮፓ ባሉ የፊልም አዳራሾ ውስጥ የበዙ ተመልካቶችን ዓይን ስቧል፡፡

 

የተዋጣለት ለመሆኑም ምክንያት ስንሻ ፊልሙ ከስነ-ጥበባዊ ውበት ይልቅ ማኅበራዊ ባሕርይ እንዳለው እንረዳለን፡፡ በ80ዎቹ መጀመሪያ ዓመታት ላይ ስላለው የጊዜው መንፈስና አንዳነድ ማኅበራዊ ሁኔታዎች እንድንዳኝ ያስገደድናል፡፡

 

ፍላሽ ዳንስ ለተመልካቶች ምን ነገሮችን ያቀርባል? ለፊልም ተከታታዮች የመሳብ ኃይሉ በምን የተሸፈነ ነው? በዚህ የፊልም ሥራ ባሕርይና ስኬቱን ለመመርመር ስንሞክር ሁለት ደረጃዎችን መርሳት የለብንም፡፡ የመጀመሪያው የታሪኩን ቅደም ተከተል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ጥልቀት ያላቸውና የተያያዙ ስዕላዊ አንቀጾች መኖሪቸውን ነው፡፡

 

በመጀመሪ እይታ ፍላሽ ዳንስ የዋናወ ገፀ-ባኽርኽልመዋን /ምኞቷን/ እና ጥራቷን ከሚገልፀው ምልስየበለጠ ማየጥ ያስቸግራል፡፡ ነገር ገን የገፀ ባሕርይዋ ምኞቶች ምንድን ናቸው? ምኞቶቿ ከባሌት ዳንስ ባለሙያ የሥራ ውጤት ጋር ሙሉ በሙሉ የተገናኙ ናቸው፡፡ ለዳንስ ጉልበቷንም ሆነ ጊዜዋን ሰውታለች፡፡ እነዚህን ሕልሞች ዕውን ለማድረግ ግን የማይፈታ ዓይነት ችግር ይገጥማታል፡፡ ባሕርይዋ በዘልማድ አነጋገር ለዳንስ የተፈጠረች ናት ብትባልም /የተፈጥሮ ስጦታ አላት ለማለት ነው/ ይህም በጥቁር አሜሪካኖች መኖሪያ የተወለደ በዓለም የታወቀ የዳንስ ምቾቶች ከጥንታዊው ባሌት የተለየ መሀኑ ነው፡፡

 

ዋናዋ ገፀ ባሕርይ ከዜሮ ትጀምራለች፣ ፈተናዎቿን ታልፋለች፡፡ የምኞቷ ስኬት ላይ ትደር4ሳለች ሌሎችም ብዙ ፊልሞች በዚሁ ሁኔታ ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ገፀ ባሕርይ ምን ላይ ያተኩር የሚለው አይደለም ዋናው ነጥብ፣ ከምኞቶች ውስጥ ሊሰመርባቸው የሚገባ ነገሮች፣ ሐብታምነት፣ ዝናን ማግኝት እና የጋብቻ እውን መሆን ሊካተቱ ይችላሉሉ፡ ዋናው ነገር ግን ባሕርዬ ዓላማዬ ነው ላለው ጉዳይ ለጥረቱ ምስጋና ይድረሰውና ከብዙ መሰናክሎች በኋላ ዓላማውን ማሳካቱ ነው፡፡

 

የዚህ ፊልም ቅንብር ታዋቂነት ያተረፈው በዓለም ማኅበረሰብ ውስጥ የተለመዱትን፣ ምኞቱ ተሳካለት፣ ለዓለማዬ ራሴን ሰጥቼለሁ፣ የሕይወቱን መንግድ አመቻችቷል፣ ለጥረቱ ዕድሜ ይችረውና ያለመውን አግኝቷል የሚሉ የዘልማድ ንግግሮችን ስለዳሰሰምነው የሚል ሃሳብ ግንዛቤ ተሰጥቶታል፡፡

 

የፍላሽ ዳንስ ዋና ገፀ ባሕርይ ምኞትና ጥረት ሕይወት ጥርጉም የለሽ አለመሆኑን ያስግነዝበናል፡፡ የኛስ ወጣቶች የሚወዷቸው ተዋናዮች፣ ዘፈኞች፣ ደደራሲዎች እውነተኛ ሕይወት ብዙ መሰናክል አልፈው እንደሆነ ሳትረዱት ትቀራለችሁ? ለዓላማ መሳካት ቀጠሮ የሚሰጠው ጉዳይ ሳይሆን ዛሬውኑ ካሁኗ ደቂቃ ጀምሮ ብትጥሩ ምን ይመስሏቸኋል? በሌላ ጊዜ ደግሞ የሌላ ተዋናይ ሕይወት ከመጽሔቶች ቀንጭቤ አቀርባለሁ እስከዛው በቸር ይግጠመን፡፡

 

ደምስ በቀለ

ከእርዳይታ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ሜላኔ ግሪፈትዝ የስሜቴ ከፍታዎች

ከፍላ ካላ ጫማ ጋር ግራሚ ኮፔና ቀሚስ ለብሳ ሜላኔ ስቴራመድ እንግቷ ላይ በሰንሰለት ያንጠለጠለቸው ዲያመንድ ወዲያ ወዲሕ እያለ ያጫውታል፡፡

ወደድከው? አለችኝ /አንደገባኝ ከሆነ በቅርቡ የተካፈለችበትን የፖስፊክ ከፍታዎቼ የሚለውን ፊልሟን ነው፡፡/

በሁኔታህ የወድከው አይመስልም ሳቅ ያለች መሰለኝ የአሳሳቋ ድምጽ በማናቸውም ሰው ላይ ሲታይ የተረበሽ ሳቅ አይነት ሲሆን በሷ ላይ ግን ከእንበሳ ማዘጋቴ ጋር ይቀራረባል፡፡

በዚህ ፊልም ላይ የወንዱ ገፀ ባሕር የሚወክለው ማቲው ሞዲን ሲሆን በሆሊውድ ውስጥ ስሙ እየገነነ ቢመታም ትህትናውን አልቀነሰበትም፡፡

ለዶን ጆንሰን /የሚላኔ ባለቤት ነው፡፡/ ሚስቱ በስክሪን ላይ ሌላ ሰው አፍቅራ ስተደባብሰው ማየቱ የሚያሳፍር ሆኖነታል፡፡ የዶን ጆንሰንና የሚላኔ ግሪፊትዝ ግንኙነት በሆሊድ ውስጥ በተለየ ሁኔታ ይወራል፡፡ ሜላን በ15 ዓመቷ ከ22 ዓመት ዕድሜ ከነበረው ዶን ጆንሰን ጋር አሰቃቂ ሙከራ በሚለው ፊልም ውስጥ ተካፋይ ነበር፡፡ ሜላኔ ከቤተሰቦቿ ከብልላ ከዶን ጋር ከህግ ውጪ አብረው መኖር ጀመሩ፡፡ 18 ዓመት ሲሞላቼም ጋብቻቸውን ፈፀሙ፡፡

 

ዶን ጆንሰን በወቅቱ የዓለም የቁንጅና ውድድር አሸናፊ ከሆናቸው ማርጆኒዋላስ ጋር እንደነበር ያስታውሳል ሜላኔ ማለዳ ጡት 11 ሰዓት ላይ ቀስቅሳው የማይሞት ፍቅራቸውን ከተገላለፁ በኋላ ወደ ላስ ቬጋስ በአይሮፕን በረውተጋቡ፡፡ ጓደኝነት ለኛ አልሞቀልም ቢሆንም አልተለያየንም፡፡ ምንአልባት ብንጋባ ዘትሩ ሊሆን ይችላል በማለቴ አስብን፡፡ ተጋባችንም አልሆነም እንደውም እኔ ያገባሁት የግንኙነታችንን መጨረሻ ለማቃረብ ፈልጌ ነበር ቴላለቴ ማላፄግሪፊቴዝ፡፡ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ተለያዩ፡፡

 

ሚያሚ ቫይረስ የሚባለው ፊልም ጆንሰነን ምድር ላይ በጣም ታዋቂ ፊቲኒ እንደ ነው አአደረገው በሙያው ዝናን እያተረፈ መጣ፡፡ በሜላኔ በኩል ግን ያን ያህል አልነበረም፡፡ ነገረ ገን ድምጼ መልኳ ቁመናዋና ችሎታዋ የብዙ ፊልም ሰሪዎች ትኩረት ስቧል ሠራተኛዋ ልጃገረድ በሚለው ፊልሟ መጥሩ ተዋናይነቷ ወርቃማው ዓለም የሊውን ሽልማት ስታገኝ ለከፍተኛ ደረጃ ሽልማትም ዕጩ አድርጓታል፡፡

 

ጊዜው ገን በጣም ትጨንቅበት የነበረው ነው፡፡ ስራ ስትሰራ መጠጥ አትጠጣም ነበር ምሽቴ ላይገን ለመዝናናት ትቀምሳለች፡፡ በኋላ ላይ ግን ፈጽሞ ልትገላግለው የማትችል ሱሰኛ ወደ መሆን ተቃርባች ነገር ከባርባራ ስትራይሳንድ ጋር ጥሩ ጓደኝነቴ የመሰረተው ዶንም የጉዳይ አካሄድ ገባው፡፡

በመሀላቸው ያለው ያልተበጠሠው የፍቅር ገመድ ግን እንዲደርስላት ገፋፋው ሜኒስታ ወደሚገኝው የዘልደን ተቋም ወደሚባለው የሱስ ማረቂያ ቦታ አንድ

 

ትገባ ግፋፋቱ ሰኔ 1989 ዓ.ም ላይም አንደገና ተጋቡቡ፡ በጥቅምት ላይ ዳኩታ የምትባለው ሰኔ ልጃቸውን ተወለደቼ፡፡

በኩሎራይ እስፔን ውስጥ ያለውን የከብት ማርቢያ ለብዙ ዓመታት ቤተሰቡ ይኖርበታል ብላ በማሰብ የገዝቸውንም ቦታ የአንድ ዓመት ፈቃድ ወሰዳ ጊዜዋን አሳልፋታለች፡፡

ይህወት በእርግጥ ቆንጆ ነው የግል ህይወት ከሌለህ ጥሩ ተዋናይ መሆን አትችልም፡፡ የምትተውነው ባሕርይ ከጀርባ ይህወት ከሌላ አይወጣልህም በማለቴ ገልጼለት ስለ ስኬቷ ስትናገር፡፡

 

ከላይ እሷ ያለችውን ስለሜሌኔ የሚናገር ሰው ግን አይኖርም፡፡ ስፖሲፊክ ከፍታወች ላይ ለሷም በአደጋ ላይ የወደቀባት ገፀ ባሕርይን ነው ወክላ የተጫወቶችው፡፡

 

ሜላኔ ያለፈው ይበቃል ብላ ጠትወስን በሌላ የሰራችው ፊልም ላይ የሚያስታውሰን የተናደደ ባህርይ አለ፡፡ እራሷን እንደ ጠንካራና ወሳኝ ስብዕና እንዴላት አድርጋ ይሆን የምታስበው? ራሷን በዚህ መልክ ማሰብ ባትለምድም አሁን ያ ዓይነት ስሜት ይሰማታል፡፡ ከቤተሰቧ ጋር እና ለምታገኛቸው የባሕሪያት ድርሻዎቼ በጣም ዕድለኛና ምን ጊዜም አመሰጋኝ እንደሆነ አድርጋ ታስባለች፡፡

 

 

 

 

 

Bibliography

  1. Andreikov todor Marlon Brando, film News

March, 1985, P.20

  1. Bizio carlo, meryl streep, ULISSe 2000, 1991               

P. 124

  1. Bizio sylria, Julie Andrews, ULISSEE 2000, February

1987, P. 120

  1. Fantazia, Maria Grazia, Peter o Toole, ULISSE 2000,

August, 19888, P. 110

  1. Hammer Mike, Meryl Streep, Ladies Home

Journal, October 19888, p. 60

  1. Jahr cliff, Joan collins, ladies Home

Journal, October, 1988 P. 34

  1. Paul Dougherty, Death of the Don,

Heghts of Passion

Bock road, the Australizn Womenes Weekly, December 1990

  1. Bils Jennifere, Film News Novebmer, 1985, P. 22
  2. Brando Marlon, Film News Decomeber, 1986, P. 23
  3. Chamberlain Brichared Film News, July 1986, P. 24
  4. Chandler jeff. Holly wood Year book, 1961, P. 68
  5. Chaplin Charlie, Encyclopedia Britannica,

                        16th edition, 1986, P. 93

  1. Couburn Charles, Holly wood year book, 1996, P. 74
  2. Couburn Charles, Jbid, P. 73
  3. De Niro, Bobert Film news, March, 1985, P. 24
  4. Jema Julizno, Film News, December, 1986, P. 24
  5. Macari Lea, Film News, October, 1986, P. 24
  6. Nero Franko Film News, September, 1986, P. 15
  7. Pacino Al, Film News, May, 1986, P. 11
  8. Spielberg Steven, Film News, June, 1986, P. 19
  9. Stallone Sylvester, Encyclopedia Britannica, 16the edition, 1986, P. 961
  10. Taylor Elizabeth, Hollywood Year book, 1961, P. 2
  11. Welles (George) Orsom, Encyclopedia Britannica, 16th ed, 1986m XII, P. 571

 

The sign shown here is to indicate that the magazines are written in Bulgarian languages.